ፋና ብሮድካስቲንግ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሰላም ስምምነት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ በሚባል መልኩ የኤርትራዉን ፕሬዚዳንት የሚያጣጥል ዘገባ ሰራ
ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበዉ ረዘም ያለ ቃለምልልስን ሰጥተዉ ነበር።
በወቅቱ በጎረቤት ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ጉዳይ ላይ ፕሬዚደንቱ አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ስለ ህገመንግስት ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሀገራቸዉ ከሶማሊያ እና ግብጽ ጋር የገባችዉ ስምምነት ኢትዮጵያን የማያሰጋ ነዉ ብለዉ አስተያየት ሰጥተዉባቸዉ ነበር።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም ለመፍጠር የተደረጉ ሂደቶች ተቀዛቅዘዋል ተብሎ መረጃ መናፈስ ከጀመረበት አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚመስል መልኩ ታድያ በትናንትናው እለት በመንግስታዊ ሚዲያ ፋና በኩል "የአስመራው መንግስት ነገር-የራሷ አሮባት" በሚል ርዕስ ፕሬዚዳንቱን የሚያጣጥል ዘገባ ሰርቷል።