ንቄሻለሁና.......!
ካንቺ ጋር እያለሁ - ባንቺ እቅፍ ሆኜ
እንዳላከበርኩሽ - ያልሽኝን አምኜ
አይንሽ አይኔ ሆኖ - ታውረሽ ታውሬ
በጭፍን ተጉዤ - ሄጄ ባንቺ ወሬ
በጨለማ ሳለሁ - ብርሀን ነው እያልሽኝ
ሞትን ልትሸልሚኝ - እያወዳደርሽኝ
እያፎካከርሽኝ - በእልህ በቅናት
ስጋዬን ደልበሽ - ነፍሴን ልታጠፊያት
መጓጓትሽን ሳውቅ - ለሞቴ ቀጠሮ
በድንገት ሲያነቃኝ - ሞቴን በሞት ሰብሮ
የናቀሽ ሲያድነኝ - ንቄሻለሁና
አንቺ አለም አትልፊ -
ዳግም በኮተትሽ አልማልልምና።
.
.
.
.
አሁን ምንሽ ያምራል - ምንሽ ነው ሚስበው
ማዕድሽ ሻጋታ - ጌጥሽም እሾህ ነው
አክብሮትሽ ውርደት - ስድብ እና ነቀፋ
ሽልማትሽ ውሸት - ካባሽም አዳፋ
ኧረ እንደው ከንቱ ነሽ
ኧረ እንደው ኦና ነሽ
እኔስ ንቄሻለሁ - ይብላኝ ለሚያከብርሽ!
.
.
.
.
መክበር ያለበትን - መወደስ መደነቅ
እውነት የሞላበት - ውሸትን የሚያስንቅ
ሞታችንን ሞቶ - ህይወትን የቸረን
በደሙ ቀድሶን - በክብሩ ያከበረን
ያንቺ እና የህልምሽ - የምኞትሽ ገዳይ
ኢየሡስ ብቻ ነው - በምድር በሰማይ
.
.
.
እንጂማ አንቺ አለም
ላላወቀሽ ሁሉ ክቡር ብትመስይም
እንዳንቺ የተናቀ የወደቀም የለም
እኔም ንቄሻለው ዞሬ አላይሽ ዳግም !
ንቄሻለው አለም!
Like👍❤ share React
----------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem
@gitim_alem
----------------------------------------------------
SHARE
ካንቺ ጋር እያለሁ - ባንቺ እቅፍ ሆኜ
እንዳላከበርኩሽ - ያልሽኝን አምኜ
አይንሽ አይኔ ሆኖ - ታውረሽ ታውሬ
በጭፍን ተጉዤ - ሄጄ ባንቺ ወሬ
በጨለማ ሳለሁ - ብርሀን ነው እያልሽኝ
ሞትን ልትሸልሚኝ - እያወዳደርሽኝ
እያፎካከርሽኝ - በእልህ በቅናት
ስጋዬን ደልበሽ - ነፍሴን ልታጠፊያት
መጓጓትሽን ሳውቅ - ለሞቴ ቀጠሮ
በድንገት ሲያነቃኝ - ሞቴን በሞት ሰብሮ
የናቀሽ ሲያድነኝ - ንቄሻለሁና
አንቺ አለም አትልፊ -
ዳግም በኮተትሽ አልማልልምና።
.
.
.
.
አሁን ምንሽ ያምራል - ምንሽ ነው ሚስበው
ማዕድሽ ሻጋታ - ጌጥሽም እሾህ ነው
አክብሮትሽ ውርደት - ስድብ እና ነቀፋ
ሽልማትሽ ውሸት - ካባሽም አዳፋ
ኧረ እንደው ከንቱ ነሽ
ኧረ እንደው ኦና ነሽ
እኔስ ንቄሻለሁ - ይብላኝ ለሚያከብርሽ!
.
.
.
.
መክበር ያለበትን - መወደስ መደነቅ
እውነት የሞላበት - ውሸትን የሚያስንቅ
ሞታችንን ሞቶ - ህይወትን የቸረን
በደሙ ቀድሶን - በክብሩ ያከበረን
ያንቺ እና የህልምሽ - የምኞትሽ ገዳይ
ኢየሡስ ብቻ ነው - በምድር በሰማይ
.
.
.
እንጂማ አንቺ አለም
ላላወቀሽ ሁሉ ክቡር ብትመስይም
እንዳንቺ የተናቀ የወደቀም የለም
እኔም ንቄሻለው ዞሬ አላይሽ ዳግም !
ንቄሻለው አለም!
Like👍❤ share React
----------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem
@gitim_alem
----------------------------------------------------
SHARE