ግጥም ለኢየሱስ ️️️📖✍


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


እንኳን ወደ ግጥም ቤታችሁ በደህና መጣችሁ ይህ የገጣሚ #አማኑኤል ነጋሽ እና የለሎች ገጣሚያን ግጥም የሚቀርብበት ነው
አዘጋጅ✍️AMANUEL NEGASH(Abu)
ግጥሜን ለኢየሱስ
10,000 members 🏃🏃‍♂️
ለአስተያየት👇
@AbuGitimBot
@abu_ND8
🛑YOUTUBE🛑
https://www.youtube.com/@gitim_alem
Telegram
@gitim_alem

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri








💗ሁል ጊዜ ከልባቹ የማይጠፋ ስለ መዝሙር ሲወራ ቀድሞ የሚመጣላቹ

መንገድ ላይ🛣 ቤታቹ🏘 ውስጥ ታክሲ🚖 ውስጥ ብቻ የትም ቦታ የምትዘምሩት የማንን መዝሙር ነው❓

በመረጣቹሁት ዘማሪ ስም አሪፍ መንፈሳዊ ቻናል እጋብዛቹሃለው ተቀላቀሉ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻


የማለዳ መልዕክት


ማቴዎስ 6 : 25፤ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
.
.
.
33፤ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።

የኔ ጌታ ሁሉ ነገሬ በአንተ እጅ ነው ታዲያ እኔ ለምን ሊጨነቅ
አንተ ነገዬን ታውቃለህ በኢየሱስ ስም

🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
ነገሬ ያለው በእርሱ እጅ ነው 2*
የሚያስፈራኝ የሚያሰጋኝ እስት ማነው

react ❤ 🙏 👍 😍 🥰


የዘገየው ነገሬ🚶‍♂‍➡️

ድሮ ድሮ ገና ያኔ በጥዋቱ
ሲሰግዱልኝ ያየሁ ፀሀይ ከዋክብቱ
ደግመው ሲሰግዱልኝ ጨረቃና ነዶ
ራዕይን ሰነቀ ልቤ በነጋታው ማልዶ
ቀኑ እየገፋ አመታት ነጎዱ
ታዲያ የታል ያኔ ለኔ የሰገዱ
ከህልሜ ልጣላ ወይስ ልክ አልነበረም
የዘገየው ነገሬ ገና አልተፈጠረም
የት ጋ ነው ስህተቴ ያጨለመው ተስፋ
ደስታን ስጠብቅ ሌተቀን ልከፋ

እያልኩ ሳጉረመርም ከብዶኝ መንዱ
ያላሰብኩት ሆነ ዘመናት ነጎዱ
.........ታዲያ
ቀን ይማይለውጥው ቃሉን የማይበላ
ከበደኝ አቃተኝ ብሎ ማይመለስ ኋላ
ለመልካም አድርጎ ጎርባጣ መንገዴን
በእሳት ፈትኖ አዳናት ህይወቴን
ልክ ነበር ህልሜ ያየሁት ትላንት
ለመፍተሄ ሰዶኝ ለክፉ ቀናት
ማዳኑን አሳየኝ ጥብቃውን አብዝቶ
ምሽቴ አማረ ጌታ ቤቴ መጥቶ
እንኳንም ዘገየ የዘገየው ነገሬ
በረከት ሆኖልኛል ሁሉ አልፎ ዛሬ

ማንበባችሁን በreaction ግለጹ
❤ 👍 🙏 😍 🥰

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


ሰላም ቤተሰብ እንደምን አመሻችሁ
እኔ ሰላም ነኝ አባታችን ጌታ ኢየሱስ ስሙ ለዘላለም ይባረክ አንድ ግጥም ሊለቅ ነው።
እስት
በ reaction

ሞቅ አድርጉኝ

👍 ❤ 😍 🙏 🥰


የዛሬ አምልኮ እንደት ነበር
እግዚአብሔርን በቃሉ ተገናኛችሁት?
በ reaction ግለጹልኝ
❤ 🙏 👍 😍


እንዳትወደኝ በመልካምነቴ
ይህ አይደለም ማንነቴ
እንዳትጠላኝ ደግሞ በጥፋቴ
ፍቅር ነህ አያስችልህም አባቴ

ያለ ምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም
ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም
የአንተ ፍቅር መነሺያው ከራስህ
የመውደድ ልብ የማያልቅብህ
የእኔ ጌታ

ያለምክንያት ወዶ ጌታ በኃጢአታችን ምክንያት አይተወንም
አሜን🤦‍♀️


መልካም ምሽት ይሁንላችሁ ❤️‍🩹


የወደድከኝ ሰሞን!

ከቤቴ ደጃፍ ላይ
ሲመላለስ አይተው የታዘቡት ሁሉ
'የፍቅር ደብዳቤ
በልጁ አስይዞ ልኮ ነበር አሉ'

እርሱ ግን!
ዘወትር ተመላልሶ ፥ ባያገኘኝ ላፍታ
ተስፈኛዋ ልቡ ፥ አጥታኝ ብትሄድ ለፍታ

ሰነባብቼ ግን
ከበሬ በስተ ሥር ፥ የታየኝ ወረቀት
እኔን ለማፍቀርህ ፥ የሄድክበት 'ርቀት
ምን ያህል እንደሆን ፥ በቅጡ ያስረዳል
የእውነት መውደድህ ፥ እንዲሁ ይወደዳል፤

እንዲህ ተገረምኩኝ!
በደም የከተብከው ፥ የመዳፍህ ጽሕፈት
እርማት ማያሻው ፥ ያልታየበት ግድፈት
የተጠቀምከው ቃል ፥ ብዛት ያላወቀው
አንድ እሱኑ ነው ፥ ይህ ነው ሚደንቀው

እናልህ ወዳጄ...
'ላስብበት' ብዬህ ፥ እንዳትቆም ከደጄ
እንደ ትላንትናው ፥ ላላመላልስህ
አንድ እድል ብትሰጠኝ ፥ እንዴት ልከልስህ ?
:
የእኔንስ ደብዳቤ ፥ በማን ልላክልህ
ማነው አንተን ደራሽ  ፥ የሚያካልልህ ?

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


ለዛሬ ጻፍልኝ


አታቋርጥ አታቁም ጻፍልኝ ለዛሬ
ቀለምህ አይለቅ ለነገም ብዕሬ
አልረካሁምና መዳኔን መስክሬ
አልጠገብኩምና አዳኙን አብስሬ
የመስቀል ላይ ሞቱ
የፍቅሩ ጥልቀቱ
የሰማይ ክህነቱ
አማላጅነቱ
የኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን
በመስቀሉ ስራ አባት ማግኘታችን
መች ተነግሮ ያልቅና
ይልቅስ ብዕሬ ልፃፍብህና
ለትውልድ ልናገር
በደም እንደዳንኩኝ ባንተ አሳልፌ ወረቀት ላይ ላስፍር
አደራ ብዕሬ
ጻፍልኝ ለዛሬ
አትለቅ ለነገም
ስለ እየሱሴ ፅፌብህ አልጨርስም።


#SHARE     #SHARE

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


እንደምን አመሻችሁ family እስት online ያላችሁ
በ reaction አሳዩኝ አንድ ግጥም ሊለቅ ነው
react👍 ❤ 😍 🙏 አድርጉ


ሰው የማይጠራበት ቦታ ላይ ስንቴ እግዚአብሔር ደረሰልን❤️‍🩹
አይ እግዚአብሔር 😭❤🙏


"የገነትን በር"

ግልፅ ቃል ይዣለሁ ትርጉሙ አንድ ነው
ሰምቶ ላደመጠው አንዳች በር አለው
በሬ በሌለበት እህል እንደሌለው
ፍሬን አቀርባለሁ ግንዱ በሽታው ነው

ማወቅ መቅመስ ነው የህይወትን ሽታ
የገነትን በር ከመታገድ ስለቱም ቢበረታ
ያንገት ማቀርቀር ዝምታው በዋዛ
ቢቆልፍብንም በሲኦል ያለ ታዛ

በኢየሱስ ይገባል የያዘ ቁልፉን
ወደ ኋላ የማያይ ይዞ እርፉን
ይህች ናት ሕይወት ከሕይወት
ጨረር ተናክታ ከሞት ወደ እውነት
ነፍስ ትጠግባለች ከእውቀቱ ሰምታ
መንፈስ ትረጋለች ሰክና በፍቅሩ ሰላምታ
ፈጣሪ አይሆንም ገዳይ
ፍርድ በእጁ ለእኛ ጉዳይ
ሊያኖር ፈጥሮ በፈቃዱ
ሟችስ ሰው ነው ከመንገዱ
ሩጫ ሩጫ ትንግርት ተጠናውቶ
ተቀባይ ከሁሉ አይሰማ አጥርቶ
ተላላ አንደበት ቂልነትን እንዲያመነዥግ
ሁከት እና ጩኸት ጥልን እንዲያንዠረግግ
አለማወቅ አይሆንም ጽድቅ
መቀመጥ ኩራዝ ይዞ በድቅድቅ
ያለ ድሪም ለግዢ ሩጫ
ካለ ፍለጋ አይኖርም መውጫ
እንቅብ ስር ተቀብሮ ያለ አፈር
ከጨለማው ፅልመት መዳከር
ጋዝ ያለ እሳት እንደማይፈራ
ሰው ያለ አምላክ ምነኛ ለከንቱ ተገራ
መጣ ያለ የስንፍናው ክፍያ
እጅግ አብቅሎ ሊያሳጣው ማረፊያ
ብዙ ያሸልላል ያስቀረራል ቀረርቶ
ባዶ ነገርን ማጮህ ይመቻል አኩርቶ
አለማውቅን ሲያወሩት ቢገጥሙ
ማወቅን ቀበራ ነው ያለቀባሪው
ግን የመጣውን ደመና ያየ አርበኛ
በወንዙ መድረቅ እንቅልፉን ያልተኛ
ስጦታ መጣ ብሎ ቦይን የቀደደ
ውሃው ይጎበኘዋል እረፍቱን ለወደደ

                       ገጣሚ አሳፍ

@YE_KIDAN_KALI

#SHARE     #SHARE

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8


እንደምን አመሻችሁ ቤተሰብ

እስት ሰላሙን ለሰጠን፣በእጆቹ መዳፍ ላዋለን፣ ከመቶ መቶ የሚያጠፉን ነገሮች እያሉ ፣ ዛሬም በምሕረቱ ሕያዋን ያደረገንን ጌታ እስት ሞቅ አድጋችሁ ከነፍሳችሁ አክብሩት

ሃለሉያ🙏🙏🙏🙏የኔ ጌታ ኢየሱስ ❤😍😘🥰
እንወድሃለን


YouTube
ጀምረናል ቤተሰብ
አሁኑኑ👉 Subscribe 👈አድርጉት
Video መልቀቅ ጀምሬያለሁ


የዘላለም አባት እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ ማለዳ ስምህ ቡሩክ ይሁን

     አቤቱ ከቀኑ ክፋት ጠብቀን። መንገዳችን ሁሉ አንተ የቀደምክበት፣ በውሏችን ሁሉ አንተ የምትውልበት ቀን አድርገው። ተመስገን! አሜን

🥰መልካም ቀን ይሁንላችሁ ቤተሰብ 🙏
  


ኢየሱስ 😍
የተወደደ ስም


💒 መሲሁ ይመጣል...💒

      እነሆ ጌታችን ይመጣል
     ልናየው ዘመኑ ቀርቧል
     በክብር በታላቅ ደመና
     ልንመለከት የክብር ገናና
     ሊወስደን ሊያኖረን ከእርሱ ጋራ
     ልናርፍ ተራ ደርሶን እኛም ከመከራ
     አዎን መሲሀችን ኢየሱስ ይመጣል
     የወጉት ሳይቀሩ አይን ሁሉ ያዩታል
     በታላቅ ግርማ በመላእክት እጃቤ
     አደለም እንደ ስጋ ልንል እንደልቤ
     ሲነፋ መለከቱ ሲበሰር መምጣቱ
     አቤት ድምቀቱ የጌታችን ውበቱ
      ተስፋ ያደረጉት ሊያዩት  ሲነሱ
       በታላቅ ህብር ሲወሳ ስለሱ
       ምድር ተሞልታ በእርሱ ግርማ
      በበጉ ፊት ልንቆም በክብር ዜማ
      ሲጠበቅ ሲሰበክ የነበረው ጌታ
     በመምጣቱ ሊሆን ተድላና ደስታ
     በዛች በክብር ቀን በጋራ ልንወጣ
     ሲለይ እውነት ከሀሰቱ ገሀድ ሲወጣ
     ተስፋ ያደረጉት በፊቱ አያፍሩምና
     ለበጉ ልንሰጥ ክብርና ምስጋና
     በፊቱ ቅዱሳን ነውር የሌለብን
     አድርጎ በሾመን በመሲሁ ቀን
     እንዲህ ሲልም ተስፋ በሰጠን
     እነሆ እኔ የዳዊት ስርና ዘር ነኝ
      የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ
      ብሎም , ባለው በአብ ቀኝ
      እኛም እንቀመጣለን በእርሱ ቀኝ
      በበጉ ፊት ለክብሩ በምስጋና ልንሰግድ
      የልባችን ሀሴት በእኛ ውስጥ ሲነድ
      ማራናታ ብለን ባልነው በክብር አለቃ
      እነሆ እኛም አርፈን ሁሉ ነገር ሊያበቃ
      ዛሬም እንላለን ደግመህ እስክትመጣ
      የሁሌ ተስፋችን ጌታ ኢየሱስ በቶሎ ይምጣ ዛሬም ወደፊትም ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ በቶሎ ና..

       ✍️by Gésúítá

#SHARE     #SHARE

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8

576 0 12 2 18

እኔ ጋሽህ ነኝ

ከማህጸን ስትወጣ አወኩህ
ደምና ስጋ ሳትለብስ ሰየምኩህ

መልኬን ስጤቼ በኔ አምሳል
ላትጠፋ በመዳፌ ተስለሀል

መስሎህ እንዳትኖር ከበርቴ
ለቀህ ሂድ ተለይ ሳትል ቤቴ

መንገድህን ምመራህ እኔ እያለሁ
ከቶ አትፍራ አትስጋ አይሀለሁ

አባትና እናት ሆኜ ስወልድህ
ኪዳኔ ይህኔ ፍጹም ላልተውህ

አይዞህ ጽና በርታ ፊቴ ተመላለስ
የዘመንህ ቁጥር እኔ ነኝ አስታውስ

ጎዳናህ ይጠበቃል ከቶ እንዳትሰናከል
ወላጅ ሆኜ ልሀለሁ ይህ ነው የኔ ቃል

ብቻህን አይደለህ ሺ ትውልድ አለህ
ከባህር አሸዋ ይልቅ ትበዛለህ

ቁጠር ከዋክብቱን የቤትህን ብዛት
ለብቻህ አልተውህም የትውልድ አባት

ስምህ ተጠርቷል ከስሜ ቀጥሎ
ልጅ ተበረለህልኝ ወርሽ ነህ ጠቅልሎ

የገባሁልህ ኪዳን አለና አትፍራ
እኔ ጋሽህ ነኝ አለሁ ከአንተ ጋራ

እኔ...ጋሻህ ..ነኝ

አለሁ ....ከአንተ ጋራራራ


📡📡  በ ጌታሁን አናሞ📡📡


“ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።”
  — ዘፍጥረት 15፥1

https://t.me/reiseneh


#SHARE     #SHARE

ግጥሜን  ለኢየሱስ
   💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
   Contact me  @abu_ND8

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.