የሠራተኞች የዕውቅናና የምስጋና የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሲያካሂድ የቆየው የሠራተኞች የዕውቅናና የምስጋና የማጠቃለያ መርሃ ግብር መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል አካሂዷል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሪቴል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ውብሸት ዘገየ፣ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን፣ ቺፍ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ተስፋዬ ሳልለው እንዲሁም የባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የዕውቅና መርሃ ግብሩ የምስራቅ እና ምዕራብ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ስር ለሚገኙ ቅርንጫፎችና ሰራተኞች የተዘጋጀ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ያለፉት ስምንት ወራት የስራ እንቅስቃሴ በበርካታ መመዘኛዎች የሚያበረታታ ዉጤት መገኘቱ ተገልጿል፡፡ የሂሳብ ዓመቱ ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ብቻ በመቅረቱ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት እና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅ ተገልፃል፡፡
ባንኩ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
የሠራተኞች የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር በሀዋሳ፣ በአዳማ እና በድሬዳዋ ከተሞች መከናወኑ ይታወቃል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #GBE