✍
እነ ኸድር ከሚሴ፣ የሙነወር ልጅ እና አምሳዮቻቸው የሚከላከሉለት የፈተናው መንስኤ የሆነው ኤሊያስ አህመድ በመንሀጀ ሰለፍ ላይ ምን ምን አጠፋ? እንደሚታወቀው በኢትዮጲያ ላይ የተምዪዕ ፈተናን ያመጣው እና ያሰራጨው የመርከዙ ሰዎች በዋነኝ ነት ደግሞ ኢልያስ አህመድ ነው። ይህ ሁሉም የሚያውቀው ነጭ እውነታ ነው። እንደውም መጀመሪያ አካባቢ እነ ኸድር ኬሚሴ፣ የሙነወር ልጅ፣ ሳዳት ከማል፣ ሙሀመድ ስራጅ እና ሌሎች በአሁኑ ሰአት ተገልብጠው ሰለፍዮችን እየተዋጉ ያሉ የተመዩዕ ቫይረስ ተጠቂዎች ይህን የመርከዙ ሰዎች መቀልበስ እና የኢልያስ መርዛማነትን ይቃወሙ እንዲሁም ያጋልጡ ነበር። ምን ታደርገዋለህ ሰውየው ሶላት ለሀምሳ አመት ቢሰግድ እና ሀምሳ አንድኛውን አመት ቢቻ ቢተው ካፊር ነው።
(እንደውም በዛ ሰአት የሙነውር ልጅ እና ሳዳት ከመርከዙ ሱዎች ጋር አብረው ለዳዕዋ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ወሬ በጣም ጦዞ ስለ ነበር ኸድር ከሚሴ ሁለቱ ላይ ረድ ሊጀምርባቸው ለማጣራ የሙነወርን ልጅ ያናገረበት ኦዲዮ ማዳመጤን አልረሳሁም።)
በጣም የሚርመው ግን በዚህ ልክ ሲኮንኗቸው የነበሩ የመርከዙ ሰዎች በባሰባቸው እና ኢኽዋን በሆኑ ሰአት ደግሞ ተገልብጠው በየትኛው ፓራሹት እንደወረዱ ባላውቅም ወርደው ዘቅጠው ከመርከዙ ሰዎች እና ከኤሊያስ አህመድ መከላከል እና ግትር ድርቅ ማለት ጀመሩ። እንደውም የሙነወር ልጅ በመርከዙ ሰዎች ላይ የተለያዩ ማጋለጦችን ካደረገ ቡሀላ ነጭ ነጩን እንናገራለን ብሎ ቀጠሮ ሰቶ ነው በዛው የቀረው። ይባስ ብለው ከኛ ጋር ለምን አብረው አልወረዱም ብለው መሻይኾች ላይ መባለግ ጀመሩ።
ቆይ ወራጅ! ምነው? ኢሊያስ ስትተቹት ከነበረው ሰላሳ መከራዎች እና ሌሎች ኢንሒራፎቹ ተመልሶ ነው? ወይስ እናንተ ድሮ ታደርጉት ከነበረው ረድ ተመልሳችሁ ነው? ከሁለት አንዱ አይቀሬ ነው።
አሁን ግን እኔ ኢሊያስ አህመድ በመንሀጀ ሰለፍ ምን ምን አጠፋ? የሚለውን ነገር የተወሰነውን ልዘረዝርላችሁ ነው። ስለማታውቋቸው ሳይሆን ለማስታወስ ያህል ነው።
1,
በውስጣዊ አሰራሩ ሱሩርይ እና በውጫዊ ማንነቱ ሱፍይ የሆነው ዶክተር ጀይላንን ማወደሱ፦ እና መፅሀፍቶቹን እንድንቀራ ማነሳሳቱ፣ ጠንካራ (ጠንጋራ) አቋሞች አሉት ብሎ ማለቱ፣ የሱን ስህተት ከነወዊ ስህተት ጋር ማወዳደሩ እና ባጠቃላይ በሱ ዙሪያ ሙዋዘና የሚባለውን የኢኽዋን ስራ መዳፈሩ።
2,
ሙመይዕ የሆነው ዑለማኦች ሙብተዲእነቱን የገለፁት ሸይኹን ኢብራሒም አር’ሩሀይሊን ማወደሱ፦ ብዙ የዐቂዳ ኪታቦችን አስቀርቷል። ማለቱ! በዚሁ ንግግሩ ደግሞ ሸይኽ ረቢዕን ከሰማይ አልወረዱም ብሎ በሸይኹ ላይ የሰጡት ተብዲዕ እና ንግግራቸውን ማጣጣሉ።
3,
ማንቃት፣ ግልፀኝነት እና ዝርዝር ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው በሆኑ ጉዳዩች ላይ ኢጅማል ማድረጉ (በደፈና መናገሩ)፦ ከነዛ መሀል ስለ ሀሚት በምናወራ ግዜ የሚፈቀዱበት ቦታዎችን ማንሳት አይጠበቅብንም። ማለቱ፣ ስለ አንድነት ስናወራ ተገቢውን አንድነት ለይተን ማውራት አይጠበቅብንም። ማለቱ የመሳሰሉት። እንደውም ይህን ተግባሩ መንገድ አድርጎ ይዞታል።
4,
የቢድዓ ባለቤቶችን በስማቸው ማወቅ አይጠበቅብንም፦ ምክንያቱም አላህ ለመልእክተኛው የሙናፊቆችን ስም አላሳወቃቸውምና ብሎ በአላህ እና በመልእክተኛው ላይ መቅጠፉ እና አጨብጫቢዎቹን ማሞኘቱ።
5,
ሰለፎች በሙብተዲዖች ላይ የነበራቸውን አቋም ወይም በነሱ ዙሪያ የተናገሩትን ንግግር፦ አሁን አይሰራበትም ልንሰራበት የሚቻልበት ዘመን አይደለም ማለቱ፣ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያም ሙሉ በሙሉ አልሰራበትም ብሎ በሳቸው ላይ መቅጠፉ እና እንደሱ ሙመይዕ ናቸው ብለው ሰዎች እንዲያስቡ ማጭበርበሩ፣ እንደውም በዋና ጀህምያዎች ላይ ነው የተናገሩት ሌሎችን አይወክልም ማለቱ።
6,
ከቢድዓ ባልተቤት ጋር ያለው የወደቀ ሙዐመላ፦ ከአህባሽ፣ ከኢኽዋን፣ ከሀይማኖት መቀራረብ ተጣሪዎች ጋር መቀማመጡ፣ እዚህም አዛም ቅርብ ጓዶች እስኪመስሉ ድረሰረ ከነሱ ጋር መታየቱ፣ አብሮ ከነሱ ጋር ወደተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች መጓዙ፣ አብሮ ከነሱ ጋር የሺርክ፣ ኹራፋት እና ቢድዓ መናሀሪያ የሆነው መጅሊስ አባል መሆኑ፣ ከሙብተዲዕ ጋር ለመስለሀ መተባበር ይቻላል ብሎ እራሱን እና አካሔዱን ለማጥራት ማጭበርበሩ።
7,
ጀርህ እና ታዕዲል ኢጅቲሀዲይ ነው፦ የጀርህ እና ታዕዲል ጉዳይን እንደ መዝሀቡ ኡለማኦች በኢጅቲሀድ የሚሰጥ ጉዳይ ነው። እኔ እና አንተን ሊያጋጭ አይገባም። አንዱ ባአንዱ ጀርህ መረጂያ የተሟላ ቢሆንም መገደድ የለበትም። አንዱ ሙብተዲዕ ያለውን እኔ ሙብተዲዕ ስላልኩት ሰውዬው ጋር ብቀማመጥ፣ አብሬው ብጓዝ፣ አብሬው ብበላ፣ አብሬው ብጠጣ ወዘተ ችግር የለውም ማለቱ።
8,
በታማኝ ሰው ወሬ እና በታማኝ ሰው ፍርድ መሀል ልዩነት አለ ማለቱ።
ወዘተ … የሰውዬው ጣጣዎች እና ችግሮች በዚህ የቆሙ ሆኖ አይደለም። ለመጠቆም ያህል ነው። እና አዲሶቹ ሙመይዖች እሱን ለማጥራት ቢሞክሩም የማይረሱ ጠባሳዎችን ነው በሰለፊያ ላይ ያሳረፈው። እስቲ እንደው እውነቱን አንካድ ስንቱን ሰለፊይ ኡስታዞች፣ ዳዒዎች እና ወጣቶችን ወደ ኢኽዋን ቀይሯል?! ይህ የሚካድ ነው? ሰውዬው ከነዚህ ስህተቶቹ ተመልሷል? አልተመለሰም! ግን የሙነወር ልጅ እና አምሳዮቹ ተገልብጠው፣ ወርደው፣ ዘቅጠው ነው ከሱ የሚከላከሉት እና የሰለፊያ የሱና መሻይኾች ላይ የሚባልጉት። ይህን አትጠራጠሩ።
✍
በወንድማችሁ፦ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ
https://t.me/abuzekeryamuhamed