ኢትዮጵያ መድን መሪነቱን ሲያጠናክር ሀዋሳ ከተማ ወሳኝ ድል አሳክቷል - ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐግብር በዛሬው ዕለት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጠናቋል። በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመሐመድ አበራ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል። በአበቡከር ሳኒ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት በ75ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው መሐመድ አበራ በ86ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ያሬድ ካሳዬ ያሻገረለትን ኳስ በግንባር በመግጨት ከመረብ አሳርፏል። ውጤቱንም ተከትሎ