" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጨረታና በዕጣ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባልገቡት ባለንብረቶች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋቃ።
የኮርፖሬሽንኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
- ከታኅሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ወደ ቤታቸው የገቡና ያልገቡትን የመለየት ሥራ ተጀምሯል።
- ከመስከረም 20 ቀን እስከ በጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የቤት ባለንብረቶች እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ነበር በድጋሚ ቀነ ገደቡን በማራዘም እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለንብረቶች እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር።
- ባደረገው ምልከታ ወደ ቤታቸው የገቡ፣ ያከራዩና በዕድሳት ላይ የሚገኙ አሉ።
- የተቀመጠው ቀነ ገደብ በመጠናቀቁ በሁሉም ሳይቶች የመለየት ሥራ ይጀመራል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዕጣ ተላልፎባቸው ቤታቸው ያልገቡትን ባለንብረቶች፣ ቤቶቹን ምን ለማድረግ ታስቧል ? ለሚለው ጥያቄ " ቀነ ገደቡ በቅርቡ በመጠናቀቁና ወደ ቤታቸው ያልገቡበትን ማለትም ፦
° በሕይወት አለመኖር፣
° መግባት አለመፈለግ፣
° በአገር ውስጥ አለመኖር፣
° በሕግ በተያዙ ጉዳዮችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መሆኑን ማጣራት ይደረጋል " ብለዋል፡፡
በዕጣና በጨረታ ተላልፈው ባለቤቶቻቸው ያልገቡባቸው ቤቶች ምን ያህል ናቸው ? ለሚለው ጥያቄ " መጠናቸው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሳይቶች እንደሚገኙ፣ ቁጥራቸውን ግን ይህን ያህል ነው ለማለት ያስቸግራል " ሲሉ መልሰዋል።
" ዋናው ነገር የቁጥር ጉዳይ አይደለም፤ ክፍት በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውንና ከተለያዩ ሳይቶች በርካታ አቤቱታዎች ለኮርፖሬሽኑ እየደረሱ በመሆኑ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " ያሉ ሲሆን " ባለቤቶቹ ያልገቡባቸው ቤቶች ከተለዩ በኋላ በቅርቡ ውሳኔ ይሰጣል " ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ፣ በሕግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው ከማቋረጥ ባለፈ በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ሕገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ አይዘነጋም፡፡
መረጃውን ከሪፖርተር ጋዜጣ ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia