👆👆👆👆👆
📚🔊ተከታታይ የሙሐደራ ግብዣ ቁ.1⃣3⃣🔊📚
📖ርእስ ፦ አቡልሐሰን አልአሽዓሪይ ማነው?
👤አቅራቢ ፦ ኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ
🌂በሙሐደራው ውስጥ የተካተቱ ነጥቦች▶️
♦️በአሁኑ ጊዜ በጣም ሰፊ ስርጨት ያላቸው እንደዚሁም ህዝቡ ዘንድ በጥሩ ምልከታ የሚታዩ ነገር ግን ከሱና የራቁ ጀመዓዎች ከሆኑት መካከል አሽዓሪያዎች ይገኙበታል።
°
♦️አሽዓሪያዎች ስያሜያቸው እንደሚያመለክተው ወደአልሸዓሪይ የሚባል ግለሰብ የተጠጉ እና በሱ መሪነት ስር የሚታሰቡ ናቸው። በመሆኑም ስለአሽዓሪያዎች ለማወቅ ስለዚህ ግለሰብ ማወቅ ያሰፈልጋል።
°
♦️ሙሉ ስሙ አቡልሐሰን ዓሊ ኢብን ኢስማዒል አልአሽዓሪይ ሲሆን ብዙዎች እንደሚሉት የተወለደው በ260ሂ. ሲሆን የሞተው ደግሞ 324ሂ. ነው። ዝርያውም ከታዋቂው ሶሓባ አቡሙሰልአሽዓሪይ ይመዘዛል።
°
♦️መጀመሪያ የነበረበት አቋም የሙዕተዚላ አቋም ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ቤተሰቦቹ እና በዙሪያው የከበቡት ሰዎች ይህን አቋም ስለሚያራምዱ ነው። ይህንንም አቋም ለ40 አመት እንደቆየበት ይነገራል። በኋላም ላይ የሙዕተዚላን አቋም የለበሰውን ካባ በማውለቅ ልክ እንደዚህ ይህን አቋም ትቼያለው በማለት ተናግሯል።
°
♦️ከሙዕተዚሊ አቋም በኋላ ወደሱና ለመለወጥ የተወሰኑ እርከኖች አልፏል። በዚህም መሰረት የሙዕተዚላን አቋም ሙሉበሙሉ ከተወ በኋላ ወደሱና ለመመለስ ሲያስብ በፊት ከለመደው የእምነት አያያዝ እና ከሱና በጣም የራቁ ሙዕተዚላዎችን እና የመሳሰሉትን የቢድዓ ቡድኖች የሚያጋልጥ እና አዕምሯዊ በሆነ መልኩ መልስ የሚሰጥ መንገድ የኩላቢይ መንገድ ነው ብሎ ስላሰበ ወደዛ አካሄድ ሊሄድ ችሏል።
°
♦️ኩላቢያዎች ራሳቸውን ወደሱና ያስጠጉ ነበር። ስማቸውንም እኛ አህሉስ-ሱንና ነን ይሉ ነበር። ነገር ግን አካሄዳቸው ከሱና ጋር የተፃረረ ነበር። መስራቻቸውም ዓብደሏህ ኢቢሰዒድ ኢብንኩላብ ሲሆን የሞተውም 243ሂ. አከባቢ ነው። በአሁንም ጊዜ የአቡልሐሰን አልአሽዓሪይ እምነት ተብሎ የሚታሰቡ ነገሮች ጥንስሱ እዚህ ግለሰብ ላይ ነበር።
°
♦️አቡልሐሰን አልዓሽዓሪይ የተወሰኑ ጊዜያትን በዚህ አስተሳሰብ ላይ ከቆየ በኋላ ወደህይወቱ መገባደጃ ላይ ነገራቶች እየተገለፁለት ሲመጡ በተለይም ወደበስራ ሂዶ በሰአቱ ከነበረው ትልቁ ሙሐዲስ ሼይኽ ዘከሪያ ቢን ያሕያ አስ-ሳጂ ጋር ከተገናኘ እና የሰለፎችን መንሀጅ ከተማረ በኋላ አቋሙ ሊቀየር ችሏል።
°
♦️ከዚህ በኋላ ምንም እንኳን የተወሰኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ጥቃቅን ስሕትቶች ቢታዩበትም የአህሉስ-ሱናን አቋም የሚደገፉ መፅሐፎችን ፅፏል። ከፃፋቸው መካከል "አል-ሉምዓህ ፊ አር-ረድ ዓላ አህሊል-ቢድዓህ" ፣ "ሪሳላ ፊ አህሊ አስ-ሰውር" ፣ "መቃላቱል ኢስላሚዪን" ይገኙበታል። መፅሐፎቹ ላይም የአህሉ-ሱንናን አቋም ጥቅል በሆነ መልኩ ያሰፈረ ሲሆን የሙዕተዚላ እና የአህሉል-ቢድዓ አቋሞችን ግን ዘርዘር ባለ መልኩ አስፍሯል።
°
♦️ከፃፋቸው ፅሑፎች መካከል የተሻለ የሚባለው ፣ ብዙ ክርክርን ያስነሳው እና በህይወቱ መጨረሻ አከባቢ የፃፈው "አልኢባናህ ፊኡሱሊ አድ-ዲያናህ" የሚለው መፅሐፍ ይገኝበታል። ክርክር ሊነሳበት የቻለው የሱ ተከታዮች ("አሽዓሪያዎች") እሱ ተመልሷል እና ይህን መንገድ አትከተሉ ሲባሉ የሱ ንግግር አይደለም ብለው የተለያዩ መከራከሪያ ሀሳቦችን ስለሚያነሱ ነው። ነገር ግን ይህ ኪታብ የሱ ንግግር ለመሆኑ መጀመሪያ አከባቢ በተወሰነ መልኩ የተከተሉት ታላላቅ የመዝሐቡ መሪ የሚባሉት ተከታዮቹ ለምሳሌ እነ አልሓፊዝ አልበይሀቂ ፣ እነ አቡበክር አልባቂላኒ ፣ እነአልሓፊዝ ኢብኑል ዓሳኪር ይመሰክራሉ።
°
♦️እንደውም አልሓፊዝ ኢብኑልዓሳኪር ኪታቡ የሱ ንግግር ለመሆኑ እና ዓቂዳው በሰለፎች ጎዳና ላይ እንደነበረ ከኪታቡ በመጥቀስ ራሱን የቻለ ኪታብ አዘጋጅቷል። ነገር ግን የኢብኑልዓሳኪር ስሕተት ተከታዮቹን ራሳቸውን በመሰረታዊ የዐቂዳ ርእሶች ላይ አሽዓሪያ ብለው መጥራታቸውን አለመንቀፉ ነው። ይህም ስሕተት ለመሆኑ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑተይሚያ ይጠቅሳል።
°
♦️በመሆኑም የ"አሽዓሪይ" መዝሐብ በተለይም በተወሰኑ የአስማኡ-ሲፋት ርእሶች ላይ እስከአሁንም ድረስ የአቡልሐሰን አልአሽዓሪይ መዝሐብ ተደርጎ ይቆጠራል። ወደ መጨረሻ አከባቢ የመጡት አሽዓሪያዎች ከመጀመሪያዎቹ አንፃር የከፉ ናቸው። ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያት አቡልሐሰን ከተመለሰም በኋላ ኪታቡ ላይ ጥቅል በሆነ መልኩ የበፊቱን የኩላብ መዝሀብ ሙሉበሙሉ በሚያወግዝ መልኩ የተጠቀመውን ንግግር ስላላገኙ ነው።
°
♦️እንደዚሁም እነዚህን ክፍተቶች በመጠቀም እነኢብኑ ፉረክ ፣ እነ አቡልመዓሊ አልጁወሊይ መዝሐቡን ስላስፋፉት እና ከዛም ለመዝሐቡ እንደመመላሻ እና እንደኢማም ተደርጎ የሚቆጥረው እና መዝሐቡን በስፋት ያሰራጨው ሙሐመድ ዑመር ፈኽሩ-ራዚ የተባለው ግለሰብ በተለይም አስማኡ-ሲፋት ላይ የተለያዩ ማምታቻዎች በማስፈር ኪታብ በመፃፍ ስላስፋፋው ነው። ነገር ግን ሼይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ በዚህ ኪታቡ ላይ አስገራሚ መፅሐፍ ፅፎ ምላሽ ሰጥቶበታል።
°
👉ጥቅል የሆነ ዓቂዳቸውን በአላህ ፍቃድ ሳምንት ይጠብቁን
_________________________
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ "አቡልሐሰን አልአሽዓሪይ ማነው?" ከሚለው ሙሐደራ ላይ የተወሰደ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
📆ሐምሌ 1 /2010
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📜ሙሉውን ከኦዲዮው ያዳምጡ። እርሶ ጋር ብቻ እንዲቀር ካልፈለጉ ለወዳጅ ዘመድም ያስተላልፉ።
🔊 ዳውንሎድ ሊንክ
⏬⏬⏬⏬⏬
https://goo.gl/96f5AE
Size : 8.38 mb ብቻ
የድምፁ እርዝመት ፦ 36 ደቂቃ ከ36 ሴኮንድ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣ለሌሎች ሙሀደራዎች ፣ ደርሶች ፣ አጠር አጠር ያሉ የነቢዩ - ﷺ - ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግር ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻናል ጆይን ያድርጉ ፦
https://telegram.me/ibnyahya7
✅የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777