ለአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ሴት አመራሮች በስራ ፈጠራ(Entrepreneurship) ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ
ስልጠና ተሰጠ፡፡
---------
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከብሄረሰብ አስተዳደሩ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ሴት አመራሮች ከአመራርነት ባለፈ በኢኮኖሚ የበቁ ሆነው ጎን ለጎን ስራ ፈጥረው መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ የአቅም ማልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መልካም አባተ
እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ምርምር ባሻገር ማህበረሰብ አግልግሎት በርካታ የአቅም ግንባታ
ስልጠናዎች መስጠቱን ገልጸው ይህ ስልጠና በዩኒቨርሲቲው አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው ቱሪዝም፣ ስራ ፈጠራ እና ልማት ዙሪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር መልካም አያይዘውም ስልጠናው ሴት አመራሮች ለሚመሯቸው መስሪያ ቤቶች በስራ ፈጠራ የተሻለ ግንዘቤ ኖሯቸው ከአመራርነት ባለፈ በስራ ፈጠራም ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው ነው ብለዋል፡፡
የስልጠናው አስተባበሪ እና ኮር አመራር የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ነጋ እንደተናገሩት ስልጠናው ለአዊ ብሄረሰብ
አስተደዳር ሴት አመራሮች የመሪነት እና ስራ ፈጠራ አቅማቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረው
ዩኒቨርሲቲው ሴቶች በሁሉም መስክ እንዲበቁ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ወ/ሮ ወይንሸት አያይዘውም ብሄረሰብ አስተዳደሩ በቀጣይ በርካታ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02kn1HV3KCbFZgXiphevhWF5YgYSwSX3CkfcWwSfBzkiWGRJ8VeYPXHRpK7DA6TNX2l/