ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din

በዚህ ቻናሌ ላይ የኦርዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ። ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri

❗#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ አባታችን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::

🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን #ንስኢ_ወልደ_ዘይትሌአል_ቀርኑ_እምኑኀ_ሰማይ " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::

❗ በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ ❗

🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ  ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ።

🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

🔷👉 በገድለህ  በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው  ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::

🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ  አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።

🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር ::

🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከአልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ  ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::

✅👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትክል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል ::

🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው።

❗የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን ❗

    ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
     ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
     መጋቢት 5/2017 ዓ.ም
               ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

❗እንደተለመደው የ100 ብር ቻሌንጃችን ተጀምሯል❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እኛም እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናል ! የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ደግሞ የታመሙ ወገኖቻችንን ከእናንተ በተሰበሰበው ገንዘብ ለመድኃኒት መግዣ እንዲሆናቸው ሰጥተናል። ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል።

🔷👉 በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ።

🔴👉 አሁንም የዛሬ ዓመት እንዳደረግነው እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ተርቤ አላበላችሁኝም ይላልና ቃሉ በዓሉን በየደብሩ ያሉ ነዳያንን አንድ ቦታ ሰብስበን በመመገብ እንዲሁም የሰው አይን ፈርተው በየቤታቸው ካሉ ከተቸገሩ እህት ወንድሞቻችን ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል !

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የተራቡ የተጠሙ የተቸገሩ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል !

🔴👉 ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ170 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል። ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇

አካውንት ቁጥር :- 1000614809683
ስም :- ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

❗በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ❗

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የታሰሩ መጠየቅ
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የተራቡ ማብላት

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
መጋቢት 2 /2017 ዓ.ም

❗❗#ምኩራብ_ምንድን_ነው ?❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 የአብይ ፆም ሦስተኛ ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡

❗👉 በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ ፤ ሕዝቡንም ወደባቢሎን አፈለሰ፡፡

🔴👉 ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡

🔵👉 ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች
(የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡

🔴👉 ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡ በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡

🔴👉 በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡

❗👉 በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡

❗❗👉 በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን
ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ)የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡

🔵 ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16

🔴 ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52

🔵 ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1

🔴👉 በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ
ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ
እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡

🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 30/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

❗❗🔷#በዓለ_ወልድ ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉"በዓለ ወልድ ማለት ወር በገባ በ29ኛው ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን የስሙ ትረጓሜም የወልድ በዓል ማለት ነው ።

🔷👉 ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስና የሰውን ልጅ ነጻ ለማውጣት ሲል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መጋቢት 29 የተጸነሰበትና ታኅሣሥ 29 የተወለደበት ቅዱስ እለት ስለሆነ በየ ወሩ ይታሰባል።

❗እግዚአብሔር ወልድ ከክፋ ነገር ❗
❗ሁሉ ይጠብቀን❗

🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 29/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

❗❗#መድኃኔዓለም❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉እንኳን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሰን

🔴👉 #መድኃኔ_ዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።

🔶👉 ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው "ምን ዓይነት ፍቅር ነው ።

🔵👉 እራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁት መሰቀልን ናቀው እርሱ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት ።

🔴👉 እኛን ትህግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትህትና ያያቸው ነበር ።

🔷👉 ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር ተብለን እንጠራለን ።

🔴👉 በ5ቱ ቅንዋት (ችንካሮች) ነበር የቸነከሩት, በመስቀሉ ስር የተገኙት ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ እኛም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግን ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል ።

🔴👉 አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባኸዉ በኃጢአት የወደቅነዉን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን ❗

🔴👉 መድኃኔዓለም ሆይ እኛን ለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው ራስህ ሰላም እላለሁ

🔵👉 የቅዱሳንን ጥሪ ለሚሰማ እዝንህና ድሆችን ለሚመለከቱ አይኖችህ ሰላም እላለሁ

🔷👉 ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህንም በጦር በወጉህ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ

❗አቤቱ አምላኬ መድኅኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኛ ልጆህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነብስ ጠብቀን ❗

❗አቤቱ ጌታ ሆይ, እንደ በደላችን ሳይሆን እንቸርነትህ ኢትዮጵያን አስባት፣ ማራት፣ ይቅር በላት ስለድንግል ብለህ, ሠላምህን፣ ፍቅርህን፣በረከትህን አትንፈጋት ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 27 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

❗እንደተለመደው የ100 ብር ቻሌንጃችን ተጀምሯል❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እኛም እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናል ! የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ደግሞ የታመሙ ወገኖቻችንን ከእናንተ በተሰበሰበው ገንዘብ ለመድኃኒት መግዣ እንዲሆናቸው ሰጥተናል። ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል።

🔷👉 በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ።

🔴👉 አሁንም የዛሬ ዓመት እንዳደረግነው እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ተርቤ አላበላችሁኝም ይላልና ቃሉ በዓሉን በየደብሩ ያሉ ነዳያንን አንድ ቦታ ሰብስበን በመመገብ እንዲሁም የሰው አይን ፈርተው በየቤታቸው ካሉ ከተቸገሩ እህት ወንድሞቻችን ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል !

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የተራቡ የተጠሙ የተቸገሩ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል !

🔴👉 ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ170 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል። ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇

አካውንት ቁጥር :- 1000614809683
ስም :- ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

❗በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ❗

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የታሰሩ መጠየቅ
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የተራቡ ማብላት

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 26 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

🔷ዛሬ 9 ሰዓት ይለቀቃል
❗ዘንግቼው እንጂ ጌታ ዉለታህን❗
   🔷👉 አዲስ የንስሃ ዝማሬ
      🔴 በዘማሪ አበራ ኪዳኑ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

#አብይ_ፆም

❗ፃዲቁ አባታችን አቡነ ተክለኃይማኖት ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉❗ተክለሃይማኖት ማለት የሐይማኖት ተክል ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈሰ ቅዱስ ማለት ነው።

🔵👉 እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቅ ናቸው።

🔵👉 አባታችን ተክለ ሐይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀርያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ/ም ተወለዱ።

🔴👉 ጻዲቁ በተወለዱ በሦሥተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱሰ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ማለትም አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱሰ ነው አንዱ መንፈሰ ቅዱስ ነው በማለት የፈጠራቸው አምላካቸውን አመሰግነወታል።

🔵👉 አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔷👉 ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔴👉 ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር
ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል። ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።

🔷👉 በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።

❗የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን❗

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድር❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 24/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.