💎كن سلفیه ኩን ሰለፊያ💎


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


->እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ ለእናንተ፣አይፈቀድም።(አን ኒሳእ19)
አላህ ሴትን ተወራሽ ሳትሆን ወራሽ በማድረግ ራሷን የቻለች ስብዓዊ ሰው መሆኗን አወጀላት።ለሷም ከቅርብ ዘመዷ የሃብት ውርስ ድርሻ እንዲኖራት አደረገላት።
->እናንተ ሰዎች ሆይ!ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ(አል ሑጁራት)

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


እረኛው በጎችን ይዞ ወደ ማደሪያቸው አስገብቶ በሮችን ሁሉ በሚገባ ዘጋው።
የተራቡ ቀበሮዎች በጎቹን ሊበሉ ሲመጡ በሮች ሁሉ በሚገባ ተዘግተው አገኙት።
በሮችን አልፈው መግባትን ተስፋ የቆረጡት ቀበሮዎችም፤ በጎቹን ከበሮች
ቁጥጥር ውጭ ለማድረግ ሴራቸውን ይጠነስሱ ጀመር።
በመጨረሻም ቀበሮዎቹ (የበጎች ነፃነት ይከበር) የሚል መፍክር ይዘው የበጎቹን
ማደርያ ዙርያ ለመዞር ወሰኑ።
በጎችም ለነሱ ነፃነት እንዲከበር ቀበሮዎች ትልቅ አብዮት እንዳቋቋሙ ሲሰሙ
ልባቸው ወደ ቀበሮዎቹ ይሸፍት ጀመር።
የነፃነት አብዮቱን ለመቀላቀል በርካታ በጎችም የግቢያቸውን አጥር በቀንዶቻቸው
ይነቀንቁ ጀመር። ከረጅም ግዜ ረብሻ እና ትርምስ በኋላ በጎቹ ማደሪያቸውን
አፍርሰው አብዮቱን ለመቀላቀል ወደ ጫካዎች ፈረጠጡ።
ቀበሮዎችም ከበጎቹ ኋላ ይሮጡ ጀመር፤ እረኛውም ከኋላ ኋላ እየሮጠ አንዴ
በድምፁ አንዴ በብትሩ ሊመልሳቸው ቢሞክርም ሊሳካለት አልቻለም።
አብዮታዊ ሩጫው ቀጥሏል፤ በጎች ከፊት ቀበሮዎች ከኋላ....ብዙም ሳይርቁ
ቀበሮዎች እና በጎች ያለ እረኛ ያለ ከልካይ ሰፊ በረሃ ላይ ተፋጠጡ።
ያች ቀን የነፃነት አብዮትን ፍለጋ ለወጡት በጎች ጨለማ ስትሆንባቸው፤ ሴራን
ላሴሩት ቀበሮዎች ግን የደስታ እና የፈንጠዝያ ቀን ነበረች።
በማግስቱ እረኛው ተነስቶ ወደ አብዮት የወጡትን በጎች ፍለጋ ወደ በረሃው
ሲያቀና፤ የነፃነት መገለጫ የሆኑ ቀበሮዎች ነፃነትን ፍለጋ የወጡትን በጎች
ስጋዎቻቸውን በልተው፣ አጥንቶቻቸውን በመሰባበር ሜዳው ላይ በትነዋቸው
አገኘው።
_________________________
ድሮ የሰማናት ተረት ናት አይደል!!!
ግን በአለማችን የሚገኙ የሴቶች የነፃነት አብዮትን እና ቀበሮዎችን ምን ያህል
እንደሚመሳሰሉ አስተውላችሁታል!!!?
የሴቶች ነፃነት አብዮት የሙስሊም ቁጥብ፣ ጨዋ እና እንቁ ሴቶችን በቀላሉ
ሊያገኝ አይችልም።
ምክንያቱም፦ አባቶቻቸው ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል።
ምክንያቱም፦ቤታቸውን ጠበቅ አድርገው ይዘዋል።
ምክንያቱም፦ ሂጃብ አድርገዋል።
ለዝያም ነው የሰው ቀበሮዎች የሚል መፈክር ይዘው
ሚስተዋሉት። አላማው ግን ሳይሆን ነው።

#መልካም_ቀን

@sule_habibi
@Sule_habibi
join my channal👆




‏العقول العظيمة تنشغل بالأفكار الإيجابية
والعقول العادية تنشغل بالأحداث
والعقول الصغيرة تنشغل بالناس
የሰው ልጅ ዐቅል ወይም አ 'ዕምሮ በሶስት ይመስሏቸዋል
1 ትልቅ አዕምሮ ፡- በሚጠቅም ሀሳብ እና አዎንታዊ በሆኑ ነገሮች ይጠመዳል
2 መካከለኛ አዕምሮ ፡- በነገራቶች ይጠመዳል
3 ትንሽ አዕምሮ፡- በሰዎች ይጠመዳል
እኛን አሏህ ጥሩ አስበን መልካም በመስራት እንዲሁም ሰውን የምንጠቅበት አቅል (አዕምሮ) ይስጠን
አሚን አሏሁ'መ አሚን

@HAYAttuna

JOIN


◾️አስተውል‼️
〰〰〰〰〰
🔻ረመዷን በፍጥነት መሄዱና ማለቁ ብቻ ሳይሆን በዛው ልክ አንተም በፍጥነት ወደ ቀብር እየቀረብክ መሆኑንም ጭምር አስታውስ‼️

🔻እያንዳንዱ ቀን ማለት እድሜህ ነው። አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ከድሜህ አንድ ቀን ተቀንሶ አንድ እርምጃ ወደ ሞት እየገሰገስክ መሆኑን እወቅ።


«በሙዚቃ መሳሪያ የታጀቡ ነሺዳዎችና መንዙማዎች ረመዿን ሊመጣ ሲል መሠራታቸው ጉዳታቸውን ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል።»
የአላህን ቁርኣን ከማንበብ ለአንድ ሰው መዘናጋት ሰበብ መሆን በራሱ ትልቅ ጉዳት ነው።


🌼 ቫለንታይንስ ደይ
(የፍቅረኛሞች) ቀንን ማክበር
በሸሪዓ እይታ!

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻧﺤﻤﺪﻩ ﻭﻧﺴﺘﻌﻴﻨﻪ ﻭﻧﺴﺘﻐﻔﺮﻩ، ﻭ ﻧﻌﻮﺫ ﺑﺎﻟﻠﻪ ﻣﻦ ﺷﺮﻭﺭ ﺃﻧﻔﺴﻨﺎ ﻭﻣﻦ ﺳﻴﺌﺎﺕ ﺃﻋﻤﺎﻟﻨﺎ، ﻣﻦ ﻳﻬﺪﻩ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻼ ﻣﻀﻞ ﻟﻪ ﻭ ﺃﺷﻬﺪ ﺃﻥ ﻻ ﺍﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻻ ﺷﺮﻳﻚ ﻟﻪ ﻭﺃﺷﻬﺪ ﺃﻥ ﻣﺤﻤﺪ ﻋﺒﺪﻩ ﻭﺭﺳﻮﻟﻪ .

ብዙዎቻችችን እንደምናውቀው (በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር 2ኛው ወር) February "የፍቅር ወር" በመባል መከበር ከጀመረ ረጅም ዘመናትን አስቆጥሯል:: "የቅዱስ ቫለንታይን" ቀን በመባልም ይታወቃል::

ዛሬ ላይም የምናየው የበዓሉ ስርአት የጥንት ሮማኖችን እና የክርስትያኖችን ባህል ቅሪት ይዞ እናገኛለን::

ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር ደግሞ ለሙስሊሞች ይህንን በዓል ማክበር ክልክል ይሆናል።

1 በመጀመሪያ ይህ በዓል በሸሪዓ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለው የፈጠራ ተግባር ነው:: በሸሪዓ መሰረት የሌለውን ተግባር መፈጸም ደግሞ በሀይማኖታችን የተወገዘ ክልክል ነው:: በመሆኑም ይህ በዓል እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ ዓንሀ) ካስተላለፈችው ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ተከታዩን ተናግረዋል፦

‹‹በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)››

[ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።]

ማለትም ውድቅ ተግባር በመሆኑ ወደ ሰሪው አካል ተመላሽ ይሆናል።

2 ይህ በዓል መሰረቱ ሙስሊም ካልሆኑ አካላት ነው። ስለዚህም በዚህ ተግባር መሳተፍ ለእነርሱ እውቅና መስጠት ስራቸውን አድናቂ መሆን እንዲሁም በሚያደርጉት ተግባርም ላይ መተባበር እና ከነርሱ ጋር መመሳሰል ነው። ይህን ተግባር መፈጸም ደግሞ የመልዕክተኛው ﷺ ትዕዛዝ ለመዳፈርና ወደዛቱበት ቀይ መስመር ውስጥ ለመግባት ይዳረጋል። ከከሃዲያን ጋር መመሳሰልን እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፦

‹‹ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡››

[አቡ ዳውድ ዘግበውታል]

3 በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ሸሪዓ የከለከላቸው ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናሉ ከብዙ በጥቂቱ ፓርቲዎች ይዘጋጃሉ ፣ ሙዚቃዎች ፣ የተለያዩ የብልግና ተግባራት ፣ ስርአት አጥነት እንዲሁም ልቅ የሆነ የወንዶችና የሴቶች መቀላቀል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

እነዚህ ተግባራት ደግሞ ሸሪዓ አምርሮ የሚቃወማቸው መጥፎ ተግባራት ናቸው። በመሆኑም ስለ ራሱ የሚጨነቅ ማንኛውም ሰው ከነዚህ ስርአት አጥነት ከሚስተዋልባቸው ዋልጌነት ከተንሰራፋባቸው መጥፎ ተግባራት ራሱን ሊቆጥብ ይገባል።

4 ይህ ተግባር የሰዎችን አዕምሮና ልብ በውሸት ነገሮች ቢዚ እንዲሆን የሚያደርግ እንዲሁም ከነዛ ምርጥ እና መልካም ጻድቅ የነበሩ አርአያ ትውልዶችን ፋናን የሚጻረር በመሆኑ ዛሬም ላይ ቢሆን ከዚህ በዓል ጋር ተያያዢነት ያላቸውን ልማዳዊ ተግባር መፈጸም ክልክል ይሆናል::

ማለትም ምግቦች፣ መጠጦች ፣ ልብሶች እንዲሁም የስጦታ ልውውጦችን እና መሰል ተገባራትን ያጠቃልላል።

ሙስሊሞች ሆይ!

በሀይማኖታችን ልንኮራ ይገባል። ደካማዎችና የጮሃን ሁሉ ተከታይ መሆን የለብንም።

ማሳሰቢያ!

በዚህ በዓልም ይሁን በሌሎች ክልክል በሆኑ በዓላት ላይ በማንኛውም መንገድ እነርሱን መተባበር ለሙስሊሞች የተከለከለ ነው። ምግብና መጠጥ የስጦታ እቃዎች በመግዛት ፣ በመሸጥ ፣ በማዘጋጀት ፣ በማከፋፈል ፣ በማስተዋወቅ እንዲሁም በሌሎች ማንኛውም መንገዶች መርዳት ክልክል ነው።

ምክንያቱም እንዚህ ሁሉ በመጥፎ ተግባራት አንዱ ለሌላው ደጋፊ እንደሆኑ ይቆጠራሉና ነው። የአላህና የመልዕክተኛውን ህግ ለመጣስና ለመተላለፍ ተባባሪ መሆን አይገባ አላህ እንዲህ ብሏል፦

ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ :
‏«ﻭَﺗَﻌَﺎﻭَﻧُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺒِﺮِّ ﻭَﺍﻟﺘَّﻘْﻮَﻯ ﻭَﻻ ﺗَﻌَﺎﻭَﻧُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻹﺛﻢ ﻭَﺍﻟْﻌُﺪْﻭَﺍﻥِ ﻭَﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺷَﺪِﻳﺪُ ﺍﻟْﻌِﻘَﺎﺏِ ‏»
ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ ﻣﻦ ﺍﻵﻳﺔ 2

«በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡»

[አል ማዒዳ :2]

በመሆኑ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን ከዚህና መሰል በሸሪዓ መሰረት ከሌላቸው ተግባራት በመቆጠብ የራሳችንንም ክብር እንዲሁም በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ያለንን ብቸኛ አንጡራ ሀብታችን የሆነውን ዲናችንን ከብክለት ልንጠብቅ ይገባል።

የመዕልክተኛውን ﷺ ሱናህ አጥብቀን በመከተል የከሃዲያንን መንገድ ልንርቅ ይገባናል፡፡ ሙስሊሞችን በጠቅላላ ከውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ከሆኑ መጥፎ ተግባራት እንዲጠብቀንና በእምታችን ላይ ጽናት እና ብርታት እንዲሰጠን አላህን እለምነዋለሁ።

ማስታወሻ!

ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት የቫለንታይንስ (የፍቅረኛሞች) ቀን ማክበርን አስመልክቶ የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ስለዚህ በዓል ተጠይቀው የሰጡትን ፈትዋዎች መሰረት አድርጌ ሲሆን ። የመልእክት መደጋገም እንዳይኖርና ለንባብ አሰልቺ እንዳይሆን ፍሬ ነጥቦችን አሳጥሬ ለማውጣት ሞክርያለሁ።

ባለማወቅም ይሁን በመዘንጋት የተሳሳቱ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን ማረሚያና መገሰጫ እንዲሆን ጌታዬን በመልካም ስሞቹና በሙሉ ባህሪዎቹ እማጸነዋለሁ።

ﻭﺃﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﺃﻥ ﻳُﻮﻓﻘﻨﻲ ﻭﺟَﻤِﻴﻊَ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦَ ﻟِﻤﺎ ﻳﺤﺒﻪ ﻭﻳﺮﺿﻰ .

ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺃﻋﻠﻢ ﻭﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋﻠﻰ ﻧﺒﻴﻨﺎ ﻣﺤﻤﺪ !

@tenbihat


قناة القران الكريمـ dan repost
{ ۗ قُلْ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرًّا ۚ .. }

[| «የጀሀነም እሳት ተኳሳነቱ በጣም የበረታ ነው» በላቸው፡፡ .. (አትተውባህ ፥ 81) አሏህ ይጠብቀን

🔮http://t.me/tilawatulkuran


☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA dan repost
𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ

ቴሌግራም 👇
t.me/huda4eth

ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth

ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ዉድ አንባቢ ቤተሰቦቻችን ዛሬ በጣም ጠቃሚ እና እዉቀት አስጨባጭ የሆነ መፅሀፍ በክፍል በክፍል ሁኖ የሚቀርብበት ቻናል ልጠቁማችሁ።

እና ኢሻ አላህ በአላህ ፍቃድ ،،#ኒካህ #ሰርግ #ኹልእ እና #ፍችን #የተመለከቱ #ሸሪዓዊ #ድንጋጌዎች ،،
የሚለዉን መፅሀፍ #በኡስታዝ #ኻሊድ #መሀመድ (አቡ ሱለይማን) ያዘጋጀዉን መፅሀፍ እያቀረብን ስለሆነ እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ ።በጣም ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች እና እዉቀቶችን ታገኙበታላችሁ ።
የመፅሀፉ መገኛ ቻናል ከታች ያለዉን ሊንክ ጠቅ እያደረጋችሁ ግቡ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@shebabelmuslimin
@shebabelmuslimin
☝️☝️☝️☝️☝️☝️👆👆በዚህ ታገኛላችሁ።

#ወላሂ #የዉሸት #ማስታወቂያ #አይደለም #ሳይጠፋ #ገባ ገባ #በሉ!!


*ህፃን ነበርን አሳደገን
*ጠማሞች ነበርን መራን
*መሀይማኖች ነበርን አስተማረን
*ስንቴ ለምነነው ሰጠን
*ስንቴ ጠይቀነው ረዳን

*ስንቴ ወደሱ ጩኸን ደረሰልን
*ስንቴ በድለን ታገሰን
*ስንቴ ራሳችን አዋርደን ሰተረልን
*ስንቴ ራሳችን ጥለን አነሳን

በእርግጥ አምላካችን አላህ የምናመሰግንበት ቃላት የለንም ፀጋውን ከፍለን የማንጨርስ ባለእዳዎች ነን።።

አልሀምዱሊላህ ረበል አለሚን
💞💞💞💞

@shebabelmuslimin
@shebabelmuslimin


የኡስታዝ ነስረዲን ደርስ ማስተላለፊያ dan repost
ሚን ዑሲሊ ዓቂደቲል ሱነቲል ወልጀመዓ የሼይኽ ፈውዛን ኪታብ ማብራሪያ በወንድማችን ነስረዲን ሀፊዘሁሏህ ክፍል 1⃣📚👆@ustaznesredin


የዚህች ጽሑፍ ጭብጥ ስለተመቸኝ ላክፍላችሁ‼️
=============================
"በአጋጣሚ አግኝቸ ሳነባት የመጨረሻ መልዕክቷን ስለወደድኩት እናንተም ትጠቀሙባት ዘንድ እነሆ አጋራኋችሁ!"
*
✍ ልጁና አያትየው እየተጫወቱ ሳለ፤

አያትየው :-
"ልጄ ሆይ! #ጀነት የሚገባው በነፃ ሲሆን #ጀሀነም ግን በገንዘብ ነው የሚገባው"
ልጅየው :-
"ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል አያቴ?"
አያትየው :-
"ቁማር የሚጫወት ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣መጠጥ የሚጠጣ ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣ለፋሂሻ (ሃራም ተግባር) ለመፈፀም ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ የሚጓጓዘው ሰው ገንዘብ ይከፍላል፣ሙዚቃ ለማዳመጥ የሚፈልግ ሰው ገንዘብ ያወጣል፣ነገር ግን ከዚህ በተገላቢጦሽ #ጀነት አንዲትም ወጪ አታስወጣም፡ ምክንያቱም ሰጋጁ ሲሰግድ ገንዘብ አይከፍልም፣ጿሚውም ሲፆም ወጪ አያወጣም፣እስቲግፋር የሚያደርገውም በኢስቲግፋሩ ወቅት ወጪ አያወጣም፣ዓይኑን ከአላስፈላጊ ዕይታ ላይ የሚቅብ ገንዘብ አይከፍልበትም ፣…"
"ስለሆነም ልጄ #ጀሀነም ለመግባት ወጪ ማውጣት ነው የሚሻልህ ወይስ ወደ #ጀነት በነፃ ነው መጓዝ የሚያዋጣህ ! ? "
የዕድሜ ባለፀጋዎች ምክራቸውና ማስተንተናቸው ምን ያህል ያማረ ነው?
••••••••••••••••••••••°•••••••••••••••••
#እህቴ _ሆይ ይህች መልዕክት ስትደርስሽ በነፃ ነው የደረሰችሽ አይደል?
ስለሆነም ላልደረሳቸው ሰዎች ላለምንም ወጪ ሳትዳረጊ መልዕክቷን አስተላልፊላቸው። አንተም እንደዛው!
👇👇👇👇👇
t.me/shebabelmuslimin
👆👆👆👆ይቀላቀሉን




የህልሜ ደራሲ እራሴው ነኝ! dan repost
🌹 እዚህች ዱንያ ላይም ሆነ
አኺራ ላይ ከቁርአን የበለጠ
ጓደኛ በፍፁም አታገኝም‥
๏ አላህን ከቤተሰቦቹ እንዲያደርግህ
ደጋግመህ ለምነው ።
✍የህልሜ ደራሲ እራሴው ነኝ!
https://t.me/yehlmederasi




በወንድማችን አቡ ሀመዊያ {[حفظه الله تعالى]} ተቀርትው ያለቁ እንዲሁም ሴቶችን የሚመለከቱ እህግጋት የሚተላለፍበት የሴቶች ግሩፕ እውቀት ብርሃን ነው!!ጅህልና ድቅድቅ ጨለማ ነው📚📖📝
https://chat.whatsapp.com/D53Ox4aK7Jt8IAWrV5WMnI


ጥንቃቄ ያስፈልጋል‼️
===============
«በአስቸኳይ ሼር ይደረግ! »
||
✍ በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጸጥታ አካላት አገኘሁት ብሎ በገጹ ላይ ይህን አስፍሯል፦
«የኦርቶዶክስ አልባሳት ለብሶ መስጅድ፣ እንዲሁም የሙስሊም አልባሳት ለብሶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ የያዙ አካላት ወደ ክልሉ ገብተዋል።»
በመሆኑም በክልሉ ያሉ ሁሉም አማኞች ቤተ እምነታቸውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡




«በየ ጊዜው የምለቃቸውን ጽሑፎች በቀላሉ ለማግኘት ይህን የቴሌግራም ቻነሌን ተቀላቀሉት።»
👇👇👇
Join:
@shebabelmuslimin
@shebabelmuslimin




#የዛሬዋ_ቀን 🍂

ምድር እንደዛሬ ቀን ታላቅ ሰው አታ አታውቅም ረሱለላህ ወደ ማይቀረው ሞት የሄዱበት ቀን ነው ረቢዓል አወል አስራ ሁለት ሰሃባዋች ትልቅ ዱብዳ ደረሰባቸው ረሱል ሞተዋል መሸከም የማይችሉት መዓት ተደንቅሮባቸዋል የእንባ ጎርፍ በሰሃባዋች ላይ ይፈሳል የዛሬዋ ቀን ከባድ ሀዘን ከባድ ፍራቻ ከባድ ነገር ሰሃባዋች ላይ ተከሰተ

ረቢዐል አወል በ አስራ ሀለተኛው
ሰሃባዋች ሁሉ ቀን ጨልሞባቸው
የአለማቱን ብርሃን ከምድራቸው ሄደው
መግቢያ መውጫ አጡ ተሰብሮ ልባቸው
ከምር አለቀሱ አሽረፈል ኸልቅን አተው !!!

በዚ ሁኔታ ነበር ያሳለፉት እንቁ ማይደገሙ ትውልዶች ረሱልን እንደነሱ ማንም ማፍቀር ማይችል ስለ ፍቅራቸው አላህ የመሰከረላቸው ረሱለላህ ስለ ታማኝ አፍቃሪነታቸው የመሰከሩላቸው ምርጥ እንቁ ውብ ትውልዶች ስለነሱ ሲታሰብ ልብ ይርዳል እንደነሱ የምር አፍቃሪ ብኖን ኢስላም በተጠበቀ ነበር !!

የሌላው አለም የዛረዋ ቀን ሰዋችም አሉ በዚ ከባድ ቀን ልደት ብለው ነሳራዋች ኢሳን በመውድድ ስም ገና ኪርስማስ ብለው ከኢስላም መርሆ ውጭ እንደሆኑት እነዚም ሰዋች በመውደድ ስም በሞት ቀን ላይ ልደት አርገው በመጨፈር በመዝለል የሚያሳልፉ በከባድ ቀን ከባድ ጥፋት ላይ የወደቁ ሰዋች አሉ

ዛሬ ተገረምን ነገር ተገልብጦ
በሀዘን ቀን ዝላይ ጭፈራው አግጦ
ፍቅር ነው አትበለኝ በለቅሶ እየሳቅክ
ጥላቻህ ጫፍ ወጥቶ ሀዘኑን ያስረሳክ

የምር የረሱለላህ አፍቃሪዋች የነበሩት ሰሃባዋች በዛሬ ቀን ከባድ ሀዘን ላይ ነበሩ የፍቅራቸው ጥግ እስኪሞቱ ከረሱለላህ ትእዛዝ ሳይወጡ ሩሃቸው ወጥታለች ! ከነሱ በላይ አፍቃሪ የለም በፍቅር ስም ስሜታዊነት አያጥቃህ ሞቅታ አይሸውድህ እልሀኝነት አትላበስ በረሱል ፍቅር ቀጥ ብለህ በትእዛዛቸው ፅና !!

قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

" በላቸው (አንተ የአላህ መለክተኛ ) አላህን ምትወዱ ከሆነ እኔን ተከተሉኝ አላህ እናንተን ይወዳቹሃል ወንጀሎቻቹህንም ይምርላቹሃል አላህ መሀሪና አዛኝ ነው "
📝...zizu nur

#we_love_mohammad_ﷺ_challenge
ካነበቡ በኋላ ሼር ማድረጋችሁን እንዳዘነጉ
#share and #join my telegram chanal
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@shebabelmuslimin
@shebabelmuslimin
@shebabelmuslimin
👆👆👆👆👆👆join


💎🎀سيرة امهات المؤمنين❄️🌷 dan repost
ربي لا تجعل نعيمك يشغلنا عن حمدك ، ولا تجعل بلاءك يشغلنا عن إستغفارك ..

‏اللهم لك الحمد في ڪل وقت وڪل حين وعلى ڪل حال
https://t.me/misalaallahisone

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

155

obunachilar
Kanal statistikasi