የወተቱ ነገር ……
መቼም ስለዛ ወተት ታሪክ ሳትሰማ የቀረህ አይስለኝም። ስለዛ እሳት ላይ ተጥዶ ፣ጠባቂ አጥቶ፣ ገንፍሎ ፣ራሱን አቆሽሾ በዙሪያው ያለውን እንዳቆሸሸውና ወደ ነበረበት የወተትነት ማእረጉ ለመመለስ አዳጋች ወደነበረው የወተት ታሪክ ዳግም ላስታውስህ ወደድኩ ።
አንድ ሰው ወተት መጠጣት አሰኘውና ከሱቅ ገዝቶ መጥቶ እሳት አንድዶ ይጥደውና ወደ ሌላ የቤት ወስጥ ስራ ያመራል። በዛም ይጠመድና ወተቱን ይዘነጋዋል
ድንገት ትዝ ይለውና ወደ ጣደው ወተት ሲያመራ ወተቱ ገንፍሎና ዙሪየው ያለውን ሁሉ አበላሽቶ ይጠብቀዋል ። በዚህም ነገር የተበሳጨው ይህ ሰው በቁጭትና በንዴት ውስጥ ሆኖ አንገቱን አቀርቅሮ በትካዜ ተዋጠ ።
አይገርምም? ?
አው አይገርምም
ምክንያቱም ምንም የሚገርም ነገር የለውማ
ወተቱን ገዝቶ ያመጣውኮ እስኪፈላ ጠብቆ ሊጠጣው ነበር ።
ነገር ግን ቸል በማለቱ የዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገባ።
የማወራህ ስለ ወተቱ አይደለም ወዳጄ
ነገር ግን ይህን ምሳሌ አርጌ ላስጨብጥህ የምፈልገው አንድ ቁም ነገር ስላለ ነው ።
እሱም ምን መሰለህ
የአንድ ትውልድ መሰረቱ ህዝብ ነው የህዝብ ምሰሶው ደግሞ ቤተሰብ ነው ።
አንድ ቤት ሲገነባ መሰረቱ ጥልቅና ጠንካራ ከሆነ የሚገነባው ቤትም የዛን ያክል ዘላቂና ጠንካራ ይሆናል ።
መሰረቱ ያልተስተካከለ ቤት ዘላቂነት ስለማይኖረው ወድቆ ጉዳት ማድረሱ አይቀሬ ነው ።
ልክ እንደዚው ቤተሰብም የአንድ ትውልድ መሰረት ነው ።
ልጅ ቤተሰብን ሆና ያድጋል አናትን አባትን እህትን ወንድምን በዙሪያው ያለውን ከባቢ አየቃኘ ያድጋል። ኃላም ያየውን የቃኘውን ይኖራል ትውልድም የሆናል።
አሁን ወደመሰረቱ ለመልስህ
ለዚህ ትውልድ መበላሸትም ይሁን መስተካከል ዋናውን ድርሻ የሚወስደው ወላጅ ነው።
አንድ ወላጅ ልጅን ሲወልድ ከመውለድ ባለፈ ትልቅ ሀላፊነት ይጠብቀዋል ። ሊጠብቀው ሊንከባከበው ይገባል። ልጁ በዲኑ ጠንካራ እንዲሆን ሰላት አሰጋገድን እየሰገደ ሊያሳየው ይገባል ። ፆምን ፣ሰደቃን፣ በጎ ተግባራትን ሁሉ ከትእዛዝ ባለፈ እየተገበረ ሊያሳየው ግድ ነው።
በዋናነት አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ መፍራት ሊያስተምረው ይገባል። የአላህ ቃል እንዲወድ ቀርቶ በማስቀራት ከተከለከሉ ክልከላዎች ነፍሲያን በማቀብ የአላህን ምንዳ መከጀልን ማሰተማር ይገባዋል ።
ሴት ልጅ የወለዱ እንደሆነ ደሞ እሷን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትልቅ ደረጃ ማብቃት ሌላ ራሱን የቻለ ትልቅ ምንዳ አለው ። ሀያእ (አይናፋርነት፣ጥብቅነት)ን እንድትላበስ በማድረግ ሰላት መስገድን፣ ቁርአን መቅራትን፣
ሂጃብ በስርአት ማድረግን ከመናገርና ከማዘዝ ባለፈ እናት ተግብራ ለልጇ ልታሰያት ግድ ነው ።
ያ ሲሆን ትውልድ መሰረቱ ጠንካራ ይሆንና ጥሩ ከባቢ ይፈጠራል።
ያ ካልሆነ ግን ቀደም ሲል ያነሳሁልክ የባለ ወተቱ ሰውዬ ታሪክ ይሆንና በወላጅ የተጀመረው ስህተት ለትውልድ ኪሳራ ይሆናል።
መሞትን ፣ወደ ቀብር መግባትን፣ (በርዘኽ) ወደ ሚባለው አለም መሄድን፣ እዛም ወስጥ ከነኪር እና ሙንከር ጋር መፋጠጥን ፣ከዛም ፍጡራን ሁሉ ወደ አላህ ፊት ቀርቦ ሂሳብ መደረግን ፣ ዱንያ ላይ እንደነበረው ቆይታ ሂሳብ ተደርጎ ዘውታሪ የሆነ አለም መኖርን ።ይሄ ሁሉ ለነገር የሰው ልጅ እንደሚጠብቀው ያላስተማረ ወላጅ በርግጥም ልጁን ችላ እንዳለው ይታሰባል ።
ወላጅ ልጁን ከመመገብ ከማልበስ አካዳሚክ እውቀትን ብቻ ከማስተማር ባለፈ ይህን የህይወት ስንቅ ሊያስተምረው ይገባል።
ያ ሲሆን ቤተሰብ ትልቁን ሚና ተጣ ይባላል ።
ትውልድም ከኪሳራ ይድናል ።
ሴት ልጅ ሂጃብ ግዴታዋ ነው መሰተሪያዋ መጠበቂያዋ ነው ። ጠንቅቃ የተገበረቸው እንደሆነ በዚህም በዚያኛውም አለም ትርፋማ ያድርጋታል ።
ከሁሉም የሚበልጠው ደግሞ አላህን መፍራቷ ነው።
ወንድ ልጅም እንደዛው ነው ።ዝንባሌውን መከተል ሲያቆም ፣ አላህን በልቡ ማላቅን ሲያዘወትር ምድር ላይ የሚኖረው ቆይታ ያማረ ይሆናል ።
ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ ፣ዙሪያችንን እንቃኝ።
ከምን ጎዜውም በላይ ወደ አላህ እንመለስ ዱኣ እናድርግ ።
አላህ ከተፀፃቾች ያድርገን
አሚን
@HAYAttunaJOIN