በእስር ላይ የሚገኘው ጆን ዳንኤል የሚባለው ድምጻዊና ቲክቶከር፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ ከሌሎች እስረኞች ጋር በስልክ የተነሳቸው ፎቶ ግራፎች በማህበራዊ ሚዲያ መሠራጨቱን ተከትሎ፣ የማረሚያ ፖሊስ ፎቶውን የተነሱበትና የተለቀቀበትን ስልክ አግኝቻለሁ፣ በእስረኞቹ ላይም እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት "ቅጣት የሚሰጠውን" መመሪያ ዛሬ እንደገና ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ለግንዛቤ እንዲረዳ ይኸው፦
⚫ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕግ ታራሚዎችና የቀጠሮ እስረኞች በተሻሻለ የሥነ ስርዓት ጥፋት ቅጣት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2009 በክፍል 02 አንቀጽ 11 ቁጥር 35 የተከለከሉ ነገሮችን ማለትም (ጫት፣ ተቀጣጣይ ነገሮች፣ ስልክ፣ ሲም ካርድ ፣ ሲጃራ፣ ጋንጃ፣ ቡሪ፣ አንጋዳ፣ አልኮል መጠጥና …ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤትና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም የገባውን መጠቀም የሚያስከትላቸው የቅጣት አይነት፡-
⚫ ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
⚫ ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
⚫ ከ5 ወር ከ1 ቀን አስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ በማረሚያ ቤት ሆኖ ሥራ በመስራት ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡
🔴ቁጥር 36 የተከለከሉ ነገሮች (አደንዛዥ እጽ፣ ጦር መሳሪያ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም አስገብቶ መገኘት ወይም ሌሎች እንዲያስገቡ መተባበር፣ ወይም ጉዳት ማድረስ (በወንጀል ያለው ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚያስከትለው የቅጣት አይነት፡-
🔴 ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም ፣
🔴 ለ3 ወር ለብቻ ተለይቶ መታሰር ወይም፣
🔴ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡
🔵ቁጥር 37 የተከለከሉ ነገሮች (ሀሺሽ፣ ፈንጂ፣ እና ተቀጣጣይ ነገሮች…ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም ማስገባት ወይም የገባውን መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት፡-
🔵ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም ፣
🔵ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም፣
🔵ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ በማረሚያ ቤት ሆኖ ከሚሰራው እና ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፣ የሚሉት ይገኙበታል፡፡(ዘ-ሐበሻ መረጃ)