ቋጠሮሽ
ዞሮ ዞሮ ከሀገር ዞሬ ዞሬ ካንቺ
ካንቺ ሚስበኝን ቋጠሮሽን ፍቺ
ከተሰደዱበት ሀገር ቢመለሱ
እንደው ተጓዙ እንጂ ድሮስ መች ደረሱ
እንደ አፈሯ ሽታ እትብቴ ከተቀበረባት እኩል
እረቄ ከሄድኩት ትጎትተኛለች በትዝታ በኩል
ሀገርስ እናት ነች ብወድቅ ባላገግም
አልጋ ባትሰጠኝ በረንዳን አትነፍግም
ያንቺ ግን ጥላ ነው ወደ ፀሀይ ስዞር
ከኋላ ይወድቃል
ተፈጥሮው ነውና ስርቀው ይቀርባል
ስቀርበው ይርቃል
የኔ ፍላጎቴ መራቅ ብቻ ካንቺ
በቃ ልሂድበት ቋጠሮሽን ፍቺ
የታመመን ትናንት ዛሬ ባማርርም
መድረስ ከሌለበት ነገን አልገብርም
ዞሮ ዞሮ ከሀገር ዞሬ ዞሬ ካንቺ
ካንቺ ሚስበኝን ቋጠሮሽን ፍቺ
ከተሰደዱበት ሀገር ቢመለሱ
እንደው ተጓዙ እንጂ ድሮስ መች ደረሱ
እንደ አፈሯ ሽታ እትብቴ ከተቀበረባት እኩል
እረቄ ከሄድኩት ትጎትተኛለች በትዝታ በኩል
ሀገርስ እናት ነች ብወድቅ ባላገግም
አልጋ ባትሰጠኝ በረንዳን አትነፍግም
ያንቺ ግን ጥላ ነው ወደ ፀሀይ ስዞር
ከኋላ ይወድቃል
ተፈጥሮው ነውና ስርቀው ይቀርባል
ስቀርበው ይርቃል
የኔ ፍላጎቴ መራቅ ብቻ ካንቺ
በቃ ልሂድበት ቋጠሮሽን ፍቺ
የታመመን ትናንት ዛሬ ባማርርም
መድረስ ከሌለበት ነገን አልገብርም
by kerim