ከመጽሐፍት መንደር💠


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና
🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨
🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥
ለማንኛውም አስተያየት
@manbabemuluyadergal_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


…አስቴርን ከአነልጇ ያገባታል ..የልቡም የቤቱም ንገስት ያደርጋታል››ሰው ምን ያላል እቤተሰብ ምን ይላሉ አሁን አይሰራም ..እስከዛሬ እሷ እንደምክንያት የምታቀርባቸው እናትና አባቱም እሷን በዳሩ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነው ተከታትለው የሞቱባቸው……‹‹አሁን ምክንያት አይኖራትም››ብሎ ወስኗል፡፡
ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው፡፡

ይቀጥላል....

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️


ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡ "አይ አንተማ ምንም አላጠፋህ …እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው..ነው ወይስ እናቴ የቤታችሁ አገልጋይ ስለሆነች አትመጥነኝም ብለህ አስበህ ነው?"አለቸው።እና እየተመናጨቀች ተለይታው ወደቤቷ አመራች።
ሰለሞንም ደንዝዞ ወደቤቱ ገባና በመጨረሻ ስትለየው የተናገረችውን ዓ.ነገር ሲያሰላስል አደረ።"....እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው... ‹‹ምን ለማለት ፈልጋ ነው?ታፈቅረኛለች ማለት ነው?እኔስ አፈቅራታለሁ እንዴ? መስፋን የፃፈላትን ደብዳቤ ሳነብ ለምን ቅር አለኝ,,,?ቀንቼ ነው እንዴ?ፍቅር ሲይዝ እንዴት ነው የሚያደርገው?ስምንተኛ ክፍል ሆኖ ፍቅረኛ መያዝ ይቻላል እንዴ?››እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች ባልጠና እና ለጋ ጭንቅላቱ ሲያወርድና ሲያወጣ እንዲሁ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ...፡፡ከዛን በኃላ በማግስቱ አናገራት ….እንደሚያፈቅራትና እሷ ፍቃደኛ ከሆነች ፍቅረኛው እንድትሆን እንደሚፈልግ ነገራት..እሷም በደስታ ፈንጥዛ እላዩ ላይ ተጠመጠመችበት….ከዛ የታዳጊነት ፍቅራቸው እስከ አስረኛ ክፍል ቀጠሉ…የበለጠ ጊዜ በሄደ መጠን በእነሱም መካከል ያለ ፍቅር እየደረጀና ስር እየሰደደ መጣ፡፡አስረኛ ክፍል በጀመሩ በሶስተኛው ወር አንድ ቀን ጥዋት የትምህርት ቤት ሰዓት ደርሶ ቀድሞ ወጥቶ ቢጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም...ተማሪ ሁሉ ሄዶ ማለቁንና ሰዓቱ መርፈድንም ከግንዛቤ በማስገባት በለሊት ቀድማ መሄዶን ጠረጠረና በሩጫ ወደትምህርት ቤት...በረፍት ሰዓት ክፍሏ ሄዶ ቢያያት እንዳልመጣች ጓደኞቾ ነገሩት።ግራ ተገባ።
አስቴር ከትምህርት ቤት በቀላሉ የምትቀር አይነት ልጅ አይደለችም። ለትምህርቷ የምትሰጠው ትኩረት ቀላል የሚባል አንዳልሆነ ያውቃል…ታዲያ እንዴት?።እናም ያለ መምጣቷ ዜና አልተዋጠለትምና እሱም እንዳመመው በመናገር አስፈቅዶ ወደቤት ሄደ…ወደቤት የሄደበት ዋና ምክንያት የአስቴር እናት እንጀራ ልትጋግር ወይም ሌላ ስራ
ለመስራት ወደእነሱ ቤት የምትመጣበት ቀን ስለሆነ አስቴር ለምን እንደቀረች ሊጠይቃት ነበር እቅዱ፡፡እቤት ሲደርስ ግን ማንም አልነበረም..የአስቴር እናትም እንዳልመጣች በኩሽናው መቆለፍ አረጋገጠና ደብተሩን አስቀምጦ ወጣና ወደ እነአስቴር ቤት አመራ… ሰፈራቸው ሲደርስ እቤታቸው ፊት ለፊት ድንኳን ተተክሎ ነጠላ ያዘቀዘቁ ሴቶችና ጋቢ የደረብ ወንዶች ሲተረማመሱ ከሩቅ አየ...ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ ነው የደነገጠው፡፡
‹‹አስቱካ ምን ሆነች?››በሩጫ ነበር ተንደርድሮ ድንኳኑ መሀከል የተገኘው...አስቴር በአራት በሚበልጡ ሴቶች ግራና ቀኝ ተደግፋ ‹‹ወይኔ እናቴ እያለች›› ስትንፈራፈር ተመለከታት"ተመስገን"አለና ትንፋሹን ወደውስጥ እየሳበ ለመረጋጋት ሞከረ።‹‹ተመስገን
››ያለው እናቷ ስለሞቱ አይደለም...በፍፁም ።ይልቅ እሷ በህይወት ስላለችልለት ተደስቶ ነው።እንጂማ እናቷ ከህፃንነቱ ጀመሮ ከገዛ እናቱ በመቀጠል ያሳደጉት ያዘሉትና የመገብት ሴት ናቸው…….የእሳቸውም ሞት በጣም አስደንግጦታልም አሳዝኖታልም…
ከዛ ከሀዘን ቤት እስክትወጣም ሆነ ከዛ በኃላ ከስሯ አልተለየም።ግን እሷን ማፅናናት እና ወደ ህይወቷ እንድትመለስ ለማድረግ ቀላል አልሆነለትም።ምክንያቱም ለአስቴር እናቷን ማጣት እናትን ብቻ ሳይሆን መላ ዘር ማንዘሯን ማጣት ማለት ነበር።ምክንያቱም አባቷን ጭራሹኑ እሷ እንደተፀነሰች የሞተ እና ዘመዶቹንም የማታውቅ ሲሆን በተመሳሳይ እናቷም የረባ የቅርብ ዘመድ ያልነበራት ብቻዋን ወልዳ ብቻዋን ያሳደገቻት ነበረች እና እሷም ስትሞትባት ሌላ አይዞሽ የሚላትና የሚያፅናናት አንድም የቅርብ ዘመድ አልነበራትም።በኃላ የእናትና አባቱ ተማከሩና አስቴርን እንደልጃቸው አድረገው ወደቤታቸው አመጧት፡፡
ትዝ ይለዋል የአስራ አምስት አመት ልጅ እና የአስረኛ ክፍል ተማሪ እያለ ነበር…አስቴር የቤተሰቡ አባል ሆና የተቀላቀለች፡፡አዎ እሷ ስትመጣ እሱ ከእህቱ ጋር ከሚጋራው ክፍል ተፈናቀለና ሌላ ትልቁ ወንድሙ ለቆ ዩኒቨርሲቲ በገባበት ክፍል ከአመፀኛው ወንድሙ ጋር ደባል ሆኖ ገባ…
እድሜውን ሙሉ የኖረበትን ክፍልና የተኛበትን አልጋ እንዳለ ለአስቴር አስረከበ….እንደዛ በመሆኑ አልከፋውም….፡፡ለሌላ ሰው ልቀቅ የተባለ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ አብዬት ያስነሳ እንደነበር እርግጠኛ ነው….ለአስቴር ስለሆነ ግን እንደውም ደስ ያለው ይመስላል…እርግጥ እሱ ከመኝታው ሳይፈናቀል በእሱ ምትክ እህቱ እንድትለቅላት ቢደረግ ወይንም ሌላ ሶስተኛ አልጋ ወደክፍሉ እንዲገባ ተደርጎ እሷ እንድትተኛ ቢደረግ በጣም ደስተኛ ይሆን እንደነበር እርግጠኛ ነው..ግን ለምን ተብሎ ሊጠየቅ የማይችለው አባቱ ኮስተር ብሎ የወሰነው ውሳኔ ስለሆነ ያለምንም ማቅማማት ነው ተግባራዊ የሆነው፡፡
አስቴር ከእሱ በአንድ አመት ስትበልጥ ከእህቱ ስህን ደግሞ በሁለት አመት ታንሳለች…..ስለዚህ የሁለቱንም ጓደኛ ነች፡፡
ይሄ ውሳኔ በደስታ እንዲፈነጥዝ እና በወላጆቹም እንዲኮራ አደረገው።እና እህቱም ጓደኛውም ሆነች...።የነካኩት የፍቅር ጉዳይ ግን እንደተዳፈነ ቀረ...።
አስቴር ‹‹ እቤታቸውንም ልባቸውንም ከፍተው እንደገዛ ልጃቸው የተቀበሉኝን ሰዎች ልጃቸው ጋር ባልጌ አላሳዝናቸውም…እኔ እና አንተ ከአሁን በኃላ እህትና ወንድም እንጂ ፍቅረኛሞች መሆን አንችልም›› ብላ ቁርጥ ያለ ውሳኔዋን ነገረችው፡፡እሱ በቀላሉ ውሳኔውን ሊቀበል አልቻለም፡፡ይበልጥ ሊያጣት እንደሆነ ባወቀ ቁጥር ውስጡ የንዴት እሳት እየነደደ ይለበልበው ጀመር፡፡
እና ውሳኔዋን እንድትቀይርና እንድታስተካክል በወጣች በገባች ቁጥር ሲያስቸግራት እሷም እሱን ተስፋ ለማስቆረጥ እርምጃ ወሰደች…ስምንተኛ ክፍል ሆነው ደብዳቤ የፀፈላትን መስፍንን 11 ክፍል ፍቅረኛ አድርጋ ተቀበለችው፡፡
ከዛሬ ነገ እሱን ትታ ወደእኔ ትመለሳለች ብሎ በትእግስ ሲጠብቅ ሁለቱም 12ተኛ ክፍል ማትሪክ ተቀበሉና ዩኒቨርሲቲ ገቡ…ልክ በተመረቁ በ3ተኛ ወሯ መስፍን እነ ሰለሞን ቤተሰቦች ጋር አስቴርን ለማግባት ሽማጊሌ ላከ…ወዲያው ቀለበት አሰሩና ከሶስት ወር በኃላ ተጋቡ፡፡
በዚህን ጊዜ ሰለሞን ሁሉ ነገር አስጠላው…ሁሉን ነገር ጣጥሎ በትምህርት አሳቦ ወደውጭ የተሰደደበት ዋና ምክንያት የእሷ ማግባት ነበር…ለአመስት አመት እዛው ኖረና ድንገት ለመመለስ ወሰነ…ይሄንን ወደሀገር የመመለሱን ውሳኔ የወሰነበት ዋናው ምክንያትም  አስቴር ከ5 አመት የጋብቻ ቆይታ እና አንድ ልጅ ከወለዱ በኃላ ተፋተው እሱም ልክ እንደእሱ አገር ጥሎ እንደተሰደዱ ስለሰማ ምን አልባት ከአመት በፊት የተነጠቅኩትን ፍቅሬን መልሼ የማግኘት እድል ይኖራኛል በሚል ተስፋ ነበር የተመለሰው፡፡ከልጅነት እስከጎልማሳነት የዘለቀ እንቅፋት የበዛበት ውስብስብ ፍቅር…እና ሁሉ ጊዜ ስለራሱና ስለፍቅሩ ሲያስብ ‹‹ጠንቆይ ለራሱ አያውቅም እያለ ››ይተርታል..፡፡
እሱ ለላፉት ሶስትና አራት አመታት ለብዙ ሺ ጥንዶች እንዴት ያፈቀሩትን ሰው ማሳመንና የራሳቸው ማድረግ እንዳለባቸው..ፍቅራቸውን እንዴት መንከባከብ እንደሚገባቸው ውጤታማ ምክር እየሰጠ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ሲጫናቸውና ደከም ያሉትንም ሲበሳጭባቸው ከርሞል..ግን የራሱን ከልጅነቱ ጀምሮ ሲያበቅለውና እየተንከባከበ ሲያሳድገው የነበረውን ፍቅር የሆነ ዘዴ ፈጥሮ ፍሬውን ለመብላት ፈፅሞ አልቻለም፣አሁን ግን ቆርጦ ነው የመጣው አዎ


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሰባት

/
ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም አዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኃላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡
ሰለሞን ወደሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት  ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና  ፊት ለፊቷ  ወለሉ  ላይ  ይቆልላል፣ለእሱ  የሰለቹትን  መጫወቻዎች  ለእሷ  ብርቆ
ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኃላ በስንት ጭቅጭቅ ከባርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።
አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ
።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።


አቦ.. እግዜር ተወኝ
'
'
ለምንድነው የማትጠራኝ
ለምንድነው የጠፋሁት
ቅዳሴው ሲሰማኝ
ቢራ ቤት ነው የነበርኩት

ለምን ከፋኝ በጭስ መሃል
ሳየው ያንተን የአምላክ ምስል ፣
መከራም እንዲህ ነው
ባለበት እዳ ነው አምላኩን የሚስል ፣

በቢራው አራፋት
በጃምቦው ብርጭቆ
ሀዘንህ ሲታየኝ ፣
ጨልጬ ብጠጣው
የማላይህ መስሎኝ ፣

ባዶ እስኪቀር የስካሬ ሞራል ፣
በማላውቀው ታምር
በማውቀው ቤተስኪያን
ድምፅህ ልጄን ይላል ፣

ለምን

ለምን እኔን ጠራህ
አሉህ አይድል በአጥርህ ፈርጡ
እነሱን ያዛቸው እኔን እንደሆነ
የለሁ ካጥረ ገጡ ፣

ተወኝ ልጠጣበት
ተወኝ አታሰማኝ የእርጋታህን ቃል ፣
ሙዚቃ ስጨምር ጭፈራ ሳበዛ
ለሽንት እንደወጣሁ
ያንተ ድምፅ ይሰማል ፣

ለምን...?እኔ መረጥክ
ተወኝ እግዜር ባክህ
ተወኝ ተወኝ አቦ ፣
አንድ በግ ስትፈልግ
ጠፍተው እንዳይቀሩ
ያሉልህ በደቦ ፣

እንዲህ ስናገር በሲጃራው መሃል
በጭሴ ውስጥ ቅርፁ
ያንተን መልክ ያሳያል

በስካሬ መሃል ይታየኛል እኔ
የሰከረ አምላክ የሰከረ ምስል ፣
አምላክም እንዲህ ነው
ባለበት እዳ ነው ጠፊ ልጁን ሚስል ፣

'
ግዕዝ ሙላት 🦘


ስሯ ቀረቡና ከጀርባዋ ቆመው ግንባሯን እያሻሹ..‹‹ልጄ …ሀሳብ ስታበዢ እኮ ነው እንቅልፍ የሚነሳሽ…..ከህመምሽ በፍጥነት ለማገገም ደግሞ የምግብን ያህል እንቅልፍም ወሳኝ ነገር ነው….አይዞሽ አልኩሽ እኮ..እኔ አባትሽ እያለሁልሽ ምንም አትሆኚ… በዛ ላይ እሱም ወንድምሽ..ለሊሴም እህትሽ ነች..፡፡.››
እንባዋ ከአይኖቾ ያለፍቃዷ ረገፈ…
‹‹አመሰግናለው ጋሼ..በእውነት በጣም አመሰግናለው፡፡››
‹‹ልጅ አባት አያመሰግንም..ዝም ብሎ ብቻ ይወደዳል….በቃ በእኛ መካከል ፍቅር ብቻ ነው ያለው..በሉ ብርዱን ብዙም አትዳፈሩት….››አሉና እንደአመጣጣቸው ወደውስጥ ተመልሰው ገብ፡፡
ስሯ የተቀመጠውን ፊራኦልን በጭለማ ውስጥ አፍጥጣ እያየችው ‹‹ታድለህ››አለችው
‹‹ማለት?››
‹‹እኚን የመሰለ ..የተባረከ እና ፍቅር የሆነ አባት ስላለህ ››
‹‹አዎ አባዬ የእኔ ብቻ ሳይሆን የሀገር ምድሩ አባት ነው…ለሰው ሁሉ ያለው ፍቅር የሚገርም ነው..አንዳንዴ እንደውም ስለሚያበዛው እበሳጭበታለው››
‹‹ጥላቻ እንጂ ፍቅር ሲበዛ እኮ አያበሳጭም››
‹‹አይ ያበሳጫል..ልጅ ሆነን ለእኛ ገዝቶ የመጣውን ሙዝ መንገድ ላይ ላገኛቸው ልጆች ሁሉ አንድ አንድ እየመዘዘ ሲያድል እቤት ሲደርስ ባዶ ፔስታል ብቻ ይቀራል…አባዬ እንደዛ ነው….ቢሆንም ግን በጣም ደሀ ግን በጣም ተወዳጅ አባት ስላለኝ አመስጋኝ ነኝ ››
‹‹አይ አባትህማ ደሀ ተብለው የሚገለፁ አይደሉም…ግርማቸውና ርህራሄያቸው ቢሊዬን ብር ያወጣል….እመነኝ ምነው የእኔም አባት በሆኑ ብዬ ቅናት እያንገበገበኝ ነው፡፡››

‹‹ምንም መቅናት አያስፈልግሽም…በቃ አሁን ልጄ ነሽ ብሎሻል አይደል……ለእሱ ከእኔ የተለየሽ አትሆኚም ፣ላጋንን አይደለም…ታይዋለሽ…..ቅድም ካንድ ጓደኛው ጋር በስልክ ሲከራከር ነበር››
‹‹ለምን?››ለማወቅ ጓጉታ ጠየቀችው፡፡
‹‹የፊታችን እሁድ ማለት ከሶስት ቀን በኃላ የሚወጣል እቁብ አለው…ስምንት ሺ ብር አካባቢ መሰለኝ፡፡እና የወንድሜ ልጅ ታማብኝ ማሳከሚያ ቸግሮኛል …ወይ እቁብን ሰጡኝ ወይ ደግሞ ከወጣለት ሰው እንድገዛ አመቻቹልኝ እያለ ሲለምናቸው ነበር…እኔ ደግሞ ለራሱ ጉዳይ ቸግሮት አንቺን እንደሰበብ እየተጠቀመ መስሎኝ‹‹‹አባ ብሩን ለምን ፍልገህ ነው?››ብለው፡፡
‹‹ይህቺን ልጅ ደህና ሆስፒታል ወስጄ ማሳከም አለብኝ..ከዚህ ሁሉ ሺ ቤቶች የእኔን ቤት ጋር መታ የተላተመችው ያለምክንያት አይደለም..እግዜር እኔን ሊፈትን ይሆናል የላካት…ደግሞስ እንዲህ ተጎድታ የተኛችው ለሊሴ ብትሆን ወይም አንተ ብትሆን እንዲህ ዝም እል ነበር?ልጄ በሬዱ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ቶሎ በፍጥነት አንስቶ ሆስፒታል ሚወስዳት ሰው ብታገኝ ኖሮ በለጋነቷ አትቀጠፍብኝም ነበር…..ከሁለት ሰዓት በላይ መኪና ውስጥ ተቀርቅራ ደሟ ሲንዠቀዠቅ……›› አለኝ…አባዬ የልጁ የበሬዱ ሞት ብቻ ሳይሆን አሟሟቷም ሁል ጊዜ እንደረበሻቸው ነው፡፡
በፀሎት የምትሰማው ነገር ከአእምሮዋ በላይ እየሆነባት ነው፡፡
‹‹ታዲያ አባትህ እንደዛ ሲሉህ አንተ ምን አልካቸው?››
‹‹እውነቱን መስማት ነው የምትፈልጊው?››
‹‹አዎ እውነቱን››
‹‹እንግዲያው እኔ አባቴ ያንን እቁብ እንዴት አድርጎ እንዴት ተቸግሮ በየሳምንቱ በመጣል ያጠራቀመው ብር እንደሆነ ስለማውቅ ተቃውሞ ነው ያሰማሁት..ታያለሽ አይደል ያን የተከመረውን ብሎኬት እንዲህ ከተደረደረ ሶስት አመት አለፈው…እህቴ በሬዱ ነበረች ከመሟተዋ በፊት የገዛችው….ቤተሰብ አሁን ባለው አኗኗር እየተጨናነቀ ስለሆነ አባቴ አንድ ክፍል ቤት ቀጥሎ እንዲሰራ አቅዳ ነበር፣ግን ያው ሞት ቀደማት ….እና አባቴ ከእቁቡ የሚገኘው ብር ለዚህ አዲስ ተቀጥሎ ለሚሰራው ክፍል ቆርቆሮና ምስማር መግዣ ነበር ያሰበው…አላማው ቤቱን መስራት ብቻ ሳይሆን የእህቴንም እቅድ ተግባራዊ ማድረግ
የአእምሮ ሰላም ማግኘት ነበር…በዚህ ምክንያት በቀላሉ ልስማማ አልቻልኩም…በእኔ አመለካከት እስከአሁን ላንቺ ያደረግነው ትብብር በቂ ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡እና የቤተሰቦችሽን ስልክ ፈልገን ደውለንላቸው እንዲወስዱሽ ነበር ሀሳብ ያቀረብኩለት፡፡››
‹‹እና ታዲያ አባትህ ምን አሉ?››
‹‹የከፋት ልጅ ነች…በራሷ ውሳኔ እንደዛ ካላደረገች እኔ እንደዛ እንድታደርግ አልገፋትም…የእኛ ሀላፊነት የቻልነውን ማድረግ ነው..ሌላው የእሷ ውሳኔ ነው..ልጄ በየቤቱ ወጣቱ እራሱን የሚያጠፋውና ህይወቱን የሚያበላሸው እንዲህ የሚያዳምጠው አጥቶ ያም ያም ሲገፋውና ሲያሳድደው ነው…የቻልነውን እናደርጋለን.››አለኝ፡፡
‹‹አሁን እንግባ በቃኝ››አለችው፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ሰቅስቆ አቀፋት..ወደውስጥ ይዞት ገባና ቀስ ብሎ ቦታዋን አስተካክሎ አስተኛትና….በራፉን በትክክል ዘግቶ ወደሶፋው በመሄድ ተኛ…እሱ ወዲያው እንቅልፍ ቢወስደውም እሷ ግን እስኪነጋጋ ድረስ እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም ነበር….ጥዋት ግን ሁሉም ሲነሱ እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡

ይቀጥላል....

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️


‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ›
‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡
‹‹ስምህ ፊራኦል ነው አይደል ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹በትክል የስሙ ትርጉምን ለማወቅ ፈልጋ ሳይሆን እንዲሁ ወደጫወታ እንዴት እንደምትገባ ግራ ስለገባት የሰነዘረችው ጥያቄ ነበር ‹‹ከዘመድ ሁሉ በላይ ነህ..ወይም ከዘመድ ሁሉ በላይ ሁን ማለት መሰለኝ....እኔ ግን ከዘመድ ሁሉ እኩል እንጂ በላይ መሆን አልፈልግም፡፡››
‹‹ሶሻሊስት ነገር ነህ ማለት ነው?››
‹‹በይው..እንዳንቺ አይነት ካፒታሊስት በበዛበት አለም ሶሻሊስት መሆን ከባድ ቢሆንም አዎ ሳሻሊስታዊ ነኝ፡፡››
‹‹እኔ ካፒታሊስታዊ መሆኔን በምን አወቅክ?››
‹‹በወዝሽ››
ከቀናት በኃላ ከት ብላ ሳቀች‹‹እንዴ እንዲህ ቆሳስዬ እና ግማሽ ፊት በባንዴጅ ታሽጎ ወዜን እንዴት ማወቅ ቻልክ?፡፡››
‹‹ወዝሽ  እኮ  ፊትሽ  ላይ  ብቻ  አይደለም  ያለው…የቆዳሽ  ልስላሴ  እኮ  የሰው አይመስልም…ጌጣጌጦችሽም አንዱ ምስክር ናቸው…››
‹‹እንዴ አርቴ እኮ ነው፡››

‹‹አይ ቤተሰቦቼ..ማለቴ እህቴ አርቴ ነው ብላ ስታወራ ሰምቼለሁ....እኔ ግን ስለጌጣጌጥ የተወሰነ እውቀቱ አለኝ …አርቴ እዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹ጎበዝ ነህ!!››
የተወሰነ ደቂቃ በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ ‹‹ምንድነው የምትሰራው?››ስትል ድንገት ጠየቀችው..ጥያቄዋ እንዲሁ በመሀከላቸው የተጀመረውን ጫወታ ለማራዘም ብላ እንጂ ምንም ይስራ ምንም የሚያስጨንቃት አይነት ሆኖ አይደለም፡፡
‹‹ገንዘብ ያስገኝ እንጂ ያገኘሁትን ሁሉ ሰራለሁ››
‹‹ማለት…?››
‹‹ማለትማ ማርኬቲንግ ነው የተመረቅኩት…ሱፐር ማርኬት ውስጥ ሰርቼ አውቃለሁ…የጅውስ ማከፋፈያ ፋብሪካም ተቀጥሬ ሰርቼ አውቃለው…..ቆርቆሮ ፋብሪካም ሰርቼ ነበር..አሁን ግን አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው እየሰራሁ ያለሁት፡፡››ሲል አብራራላት
‹‹አኸ…ስለጌጣጌጤ የተናገርከው ከዛ ልምድ በመነሳት ነዋ››
‹‹ይሆናል››
‹‹ግን ቆርቆሮ ፋብሪካ የትኛው ቆርቆሮ ፋብሪካ ነው የሰራኸው?››
‹‹በፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ…እዛ ሁለት አመት ሰርቼው›› ከድንጋጤዋ የተነሳ ..ትን አላት…ደንግጦ ተነሳና ጀርባዋን ደገፋት
‹‹ደህና ነኝ ደህና ነኝ››
‹‹ምነው ..ያልሆነ ነገር ተናግሬ አስደነገጥኩሽ እንዴ?››
‹‹አይ በፀሎት የሚባል ቆርቆሮ ፋብሪካ መኖሩን አላውቅም ነበር…››
‹‹እንግዲህ ቆርቆሮን በተመለከተ ምንም እውቀት የለሽም ማለት ነው…..በፀሎት እኮ አገሪቱ ውስጥ ካሉ ትላልቆቹ ቆርቆሮ አማራቾች መካከል አንዱ ነው…ባለቤትነቱ የቢሊዬነሩ ባለሀብት የአቶ ኃይለመለኮት ነው…..በፀሎት የልጃቸው ስም ነው፡፡›

‹‹አይገርምም..የእኔም ስም በፀሎት በመሆኑ እኮ በእኔ ስም የሚጠራ ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለማወቄ ተደንቄ ነው...ሰውዬውን ማለቴ ባለቤቱን ታውቃቸዋለህ?››
‹‹አዎ …አውቃቸዋለው…ማለቴ በመጠኑ .. ሁለት ወይም ሶስት ቀን እሷቸውን የማናገር እድል ነበረኝ››
‹‹ልጃቸውንስ?››
‹‹እሷን የፋብሪካው በራፍ ላይ በትልቁ ቢልቦርድ ላይ የተለጠፈው ምስሏ ለአመታት ሳየው ነበር ….ይሄኔ እሷ በስሟ ወላጆቼ ፋብሪካ እንዳላቸው ሁሉ አታውቅም ይሆናል..ግን ይገርምሻል አሁን በጣም ትናፍቀኛለች…ብዙ ቀን ላገኛት ሞክሬ ነበር ግን አውሬ መሳይ ጋርዶቾ ሊያስጠጉኝ አልቻሉም….ግን በቅርብ እንደማገኛትና እንዲህ እንደእኔና እንዳንቺ ፊትለፊት ተቀምጠን ብዙ ብዙ ነገር እንደምናወራ እርግጠኛ ነኝ…በሆነ መንገድ የግድ ማግኘት አለብኝ››
ንግግሩን ስትሰማ በተቀመጠችበት ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥና የልብ ምቷ ሲጨምር ታወቃት…
‹‹ትናፍቀኛለች ነው ያልከው…..ግራ አጋቢ ነገር ነው››ይብልጥ እንዲያወራ የሚያበረታታ ዓ.ነገር ጣል አደረገች፡፡
‹‹ግራ አትጋቢ…አብራራልሻለሁ …ቆይ እንደውም…››አለና ኪሱ ገባና የገንዘብ ቦርሳውን አወጣ ….ምን ሊያደርግ ነው ብላ ስትጠብቅ….ከፈተውን አንድ ጉርድ ፎቶ አወጣና አቀበላት…‹‹አየሻት…በፀሎት ማለት ይህቺ ነች…››ብሎ መች እንደተነሳች የማታውቀውን የገዛ ፎቶዋን እጇ ላይ አስቀመጠላት…ለተወሰነ ጊዜ ድንዝዝ አለች፡፡
‹‹ፎቶዬን እንዴት…..?››
‹‹ምን አልሺኝ?››
በመዘባረቋ ደንግጣ‹‹ማለቴ ..የልጅቷን ፎቶ አንተ ጋር ምን ይሰራል….?››
‹‹…ስለምትናፍቀኝ እልኩሽ እኮ…እርግጥ ቀጥታ እሷ አይደለም የምትናፍቀኝ ….እህቴ በሬዱ ነች…አወሳሰብኩብሽ አይደል፡፡ታላቅ እህቴ በሬድ ከሁለት አመት በፊት ነው በአደጋ ምክንያት የሞተችው…ታላቄ ነበረች..የሁለት አመት ታላቄ..የቤቱ እጅግ ተወዳጅ ልጅ ነበረች….ባንክ   ነበር   የምትሰራው…የቤታችንን   ወጪ   ግማሹን   እሷ   ነበረች

የምትሸፍነው…ግን ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደረሰባትና ሆስፒታል ገባች፣የዛን ጊዜ እኔ የነበፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ ነበር የምሰራው….እና እህቴ ክሪትካል ኬዝ ላይ ደረሰችና ጭንቅላቷ በጣም ተጎድቷ ስለነበረ ወደውጭ ሄዳ ብትታከም ጥሩ እንደሆነ ሀኪሞቹ ምክር ሰጡ ..እኛ አቅማችን አይችልም ነበር…በአጋጣሚ በዛን ጊዜ በፀሎት የልብ በሽታዋ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደውጭ ለህክምና ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበረች…እኔ እህቴን ለማሳከሚያ የእርዳታ ብር ለመሰብሰብ እላይ እታች በመሯሯጥ ላይ ነበርኩ ….ከመስሪያ ቤት ሰራተኞች እየተሰበሰበ ሳለ አቶ ኃይለመለኮት ድንገት ፋብሪካውን ለመጎብኘት ይመጣሉ..እና እያለቀስኩ እርዳታ ከሰራተኞች ስሰበስብ አይተውኝ ወደመኪናቸው ይዘውኝ ገቡና ምን እንደሆንኩ ጠየቁኝ…እያለቀስኩ በቤተሰባችን የደረሰውን መከራ ነገርኮቸው………
‹‹በቃ እርዳታ መሰብሰቡን አቁም እኔ እህትህን አሳክምልሀለው››አሉኝ በፍፅም እውነት አልመሰለኝም ነበር…ግን ከምራቸው ነበር..‹‹ከአስር ቀን በኃላ ልጄን ለልብ ህክምና ወደታይላንድ ይዤት ስለምሄድ እህትህንም እዛ ሔዳ መታከም ትችላለች..የህክምና ማስረጃውን ጨርሱ የጉዞ ሰነድችን የእኔ ሰዎች ያመቻቻሉ››ብለው አስፈነጠዙኝ፡፡
ቃላቸውን ጠብቀው እህቴን ከአባቴ እና ከገዛ ልጃቸው ጋር ይዘው ታይላንድ ሄዱ…እህቴ ታይላንድ በገባች በአስራ ሶስተኛው ቀን ህይወቷ አረፈ….….በዛን ጊዜ ደግሞ በተመሳሳይ ቀን የፀሎት ልቧ ፌል አድርጎ በህይትና በሞት መካከል ስታጣጥር ነበረ…ብቻ ፕሮሰሱ ብዙ ነው…በስተመጨረሻ አባቴ ልጄ ሙሉ በሙሉ እንዳትሞት ልቧን መለገስ እፈልጋለው አለና ፍቃደኛ ሆኖ እዛው የእህቴ የበሬድ ልብ ለበፀሎት ተገጠመላትና..አባቴ የእህቴን ሬሳ ጭኖ መጣ እልሻለው፡፡፡››
‹‹በጣም የሚገርም ልብ ሰባሪ ታሪክ ነው የነገርከኝ››
‹‹አዎ በጣም ልብ ሰባሪ ነው…አይገርምም የአንዱ ቤት ደስታ በሌላው ቤት ሀዘን ላይ መብቀሉ…አንዱ እንዲስቅ ሌላው ማልቀስ አለበት…ህይወት እንዲህ ኢፍትሀዊ መሆኗን ከዛ በፊት አላውቅም ነበር››
‹‹በቃ አትበሳጭ ..እናውራ ብዬ ..አስደበርኩህ አይደል?››
‹‹አረ በፍጽም..››ብሎ ሊያብራራት ሲል የሰርቢሱ በራፍ ተከፈተ… ሁለቱ ፊታቸውን ሲያዞር አቶ ለሜቻ ነበሩ፡፡

‹‹እንዴ ልጄ አመመሽ እንዴ… ?ፊራኦል ለምን ሳትቀሰቀኝ?››ልጃቸውን ተቆጡት
‹‹አይ አባዬ …አላመማትም..እንቅልፍ እምቢ ሳላላትና እቤቱ ስለሞቃት ነው ውጭ የወጣነው፡፡››
‹‹አዎ አበባ ..ደህና ነኝ…እንቅልፍ እምቢ ስላለኝ ነው፡፡››እንዳላመማት አረጋገጠችላቸው፡፡


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ስድስት

ማታ አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡
ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡
‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡

በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››
‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››
ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡
‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››
‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››
‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡
‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡
መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..
‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን  አልትም  ወደቀልባቸው  እንዲመለሱ  ምክንያት  ሊሆናቸው  ይችል

ይሆናል…ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡
‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…
‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡
‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት››በማለት መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..
‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››

‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡
እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡

‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…


ምትመልሰውን መልስ ማሰላሰል ጀመረች….በአእምሮዋ አስልታ ከመወሰኗ በፊት ከአንደበቷ ሾልኮ ወጣ…..‹‹ሰክሮ መጥቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፡፡››ስትል አፈረጠችው፡፡፡
እቤቱ ሁሉ በድንጋጤ ፀጥ አለ….ሁለቱ አዛውንት ወላጆች ስቅጥጥ አላቸው፡፡እሷ እራሷ በተናገረችው ውሸት እራሷ ደነገጠች…በመደንገጧ ደግሞ የማተቆጣጠረው እንባ በጉንጮቾ ላይ እንዲረግፍ አደረገ…አቶ ለሜቻ በቀኝ ወይዘሮ እልፍነሽ በግራ አቅፈዋት እያሻት ያባብሏት ጀመር‹‹ልጄ አይዞሽ..ከዛሬ ጀምሮ እኔ እናትሽ ነኝ….እሷቸውም አባት ይሆንሻል፡፡››ቃል ኪዳን ገቡላት፡፡
‹‹በቃ ልጄ ምንም አታስቢ… እኛ ቤተሰቦች ነን…አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገሽ እርሺና እራስሽን አስታሚ …በደንብ ከዳንሽ በኃላ ..የሚሆነውን እናደርጋለን.፡፡.ልትከሺውም ከፈለግሽ..ወይም ሌላ ነገር ካሰብሽ በማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነን..አሁን ግን ስለምንም ነገር አትጨነቂ በሽታሽን ላይ ብቻ አተኩሪ …እንደምታይው ኑሮችን ደከም ያለ ነው …ትልቅ ሆስፒታል  ወስደን  ልናሳክምሽ  አንችልም….ግን  ደግሞ  ውጌሻው  የማያሽልሽ  ከሆነ

የመንግስት ሆስፒታልም ቢሆን አመላልሰን እናሳክምሻለን..ምንም አታስቢ፡፡››የአቶ ለሜቻ ማበረታቻ ቃል ነበር፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለው…..በእውነት በህይወቴ እንደእናንተ የወደደኝ ሰው የለም……ሰው ሰውን እንዲሁ በነፃ በዚህ መጠን መውደድ እንደሚችል አላውቅም ነበር…በጣም አመሰግናለው..››አለችና ሸርተት ብላ ተኛች…አይኗን ጨፈነች፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽም‹‹ልጄ..ሲያዩሽ እኮ መልዐክ ነው የምትመስይው፡፡ አንቺን ምን አይነት ሰው ነው ላይወድሽ የሚችለው?››ብለው አልጋ ልብሱን ወደላይ ስበው አለበሶትና ከስሯ ዞር አሉ….
ስለዋሸቻቸው ፀፀታት..ግን ምርጫ የላትም..እንዲህ ካላደረገች ከቤተሰቦችሽ እናገናኝሽ ብለው ያስቸግሯታል..እሷ ደግሞ ወደእዛ ምድራዊ ሶኦል ወደሆነ ና ፍቅር ወደነጠፈበት ቤት እንዲ በቅርብና በቀላሉ የመመለስ ምንም አይነት እቅድ ያላትም….፡

ይቀጥላል....

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️


ወ.ሮ እልፍነሽ ጥያቄው መደናገር ውስጥ አስገባቸው‹‹ለምን ጠየቁኝ?››
‹‹አይ እንዲሁ ነው..ይህቺ የወንድሙ ልጅ እጅግ የሀብታም ልጅ እንደሆነች ያስታውቃል››
‹‹እንዴት ነው ሚያስታውቀው…?ያደረገችውን ልብስና የደረገችውን አርቴፊሻል ጌጥ ተመልክተው ነው?››
‹‹አይ ፍፅም እነሱን አይቼ አይደለም…ሰውነቷን አይቼ ነው…ልስላሴው እኮ ከሀር ጨርቅ በላይ ነው…..እጅግ ቅንጡ አስተዳደግ ያደገች የንጉስ ልጅ ነው የምትመስለው…አዎ በደንብ ያስታውቃል፡፡››አሉ እርግጠኛ በመሆን፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽ‹‹ይሆናል››ብለው በድፍኑ መልስ ሰጡ፡፡

‹‹እንግዲ..ከሶስት ቀን በኃላ መጥቼ አያታለው…ሾርባ ነገር እያደረጋችሁ በደንብ ተንከባከቧት …ትድናለች……በሉ›› ብለው ሲወጡ አቶ ለሜቻ ወደውስጥ ገቡና ወደባለቤታቸው በመቅረብ….‹‹የእኔ አለም….ለውጌሻዋ የሚከፈል ብር አለሽ አንዴ?››ሲሉ ልብን በሚሰረስር ትህትና ጠየቁ፡፡
‹‹ስንት ይሆን….?››
‹‹ሁለት መቶ ብር ነው..እኔ ጋር መቶ ብር አለ፡፡››
በፀሎት በወገባቸው ዙሪያ የተጠመጠመ መቀነታቸውን ሲፈቱ አጨንቁራ እያየቻቸው ነው..ከቋጠሮ ውስጥ ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጡና ለባለቤታቸው ሰጦቸው….
‹‹መቶ ብሩን አትሰጪኝም…?››
‹‹ኪስህማ ባዶ መሆን የለበትም…ግድ የለህም ሂድ ውጌሻዋን ሸኛት ››
አቶ ለሜቻ የተሰጣቸውን ብር በእጃቸው እያሻሹ ወደ ውጭ ወጡ…ወ/ሮ እልፍነሽ ወደጓዲያ ገብና በጓድጓዳ ሰሀን ምግብ እና በብርጭቆ ውሀ ይዘው በመምጣት ስሯ ቁጭ አሉ ፡፡
የተኛች መስሎቸው ቀስ ብለው ትከሻዋን ያዙና ‹‹የእኔ ልጅ ..የእኔ ልጅ››ሲሉ ሊቀሰቅሷት ሞከሩ… ቀስ ብላ አይኗን ስትገልጥ እንጀራ የጠቀለለ እጃቸው አፏ አካባቢ ደርሶል….‹‹በ…ቃኝ…እማ….ማ››
‹‹አይ….በቃኝ አይሰራም…ካልበለሽ አትድኚም…እንደምንም ባይጣፍጥሽም ታግለሽ መብላት አለብሽ››ኮስተር አሉባት፡፡
አሳዘኗት…‹‹ቆይ ማንነቴን አያውቁ ለምንድነው እንዲህ እየረዱኝ ያሉት….?ነው ወይስ የልጃቸውን ልብ የተሸከምኩ መሆኔን ደመነፍሳቸው ነግሯቸው ይሆን?››መልስ በቀላሉ ልታገኝለት ያልቻለችው ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡፡
ለእሳቸው ስትል እንደምንም አፏ ከፈተች…አፏ ውስጥ ከተቱት…በመከራ አላመጠችና ዋጠች..እንቁላል ፍርፍር ነው…በመከራ አምስት ጉርሻ ያህል አጎረሶትና ወደላይ ደግፈው ውሀ እንድትጠጣ ካደረጉ በኃላ አስተኟት…፡፡ከዛ አቶ ለሜቻም ውጌሻዋን ሸኝተው ስለተመለሱ ለቤተሰቡ ጠቅላላ ቁርስ ቀረበና ተሰብስበው እየተጎራረሱ  ሲበሉ አየች….ያ

ደግሞ ይበልጥ ስለወላጆቾ ቤት እንድታስብና ልቧ እንዲሰበር አደረገ ..ለእሷ እንቁልል ጠብሰው ያባሏት ሴትዬ ለቤተሰቡ ደረቅ ዳቦ በሻይ ነው ማቅረብ የቻሉት፡፡የገረማት ደግሞ እሱንም በፍቅር እየተሳሳቁ ይጎራረሳሉ፡፡
እሷ ቤት በየቀኑ ጠረጴዛ ሙሉ ለአይን እራሱ የሚያታክት ምግብ ይቀርባል፡፡ የሚበላው ግን አስር ፐርሰንትም አይሞላም…ከዛ የተረፈው ምን እንደሚደረግ አታውቅም..ምን አልባት እዛ ጊቢ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ይታደል ይሆናል… ወይም ደግሞ ተበላሽቶ ገንዳ ውስጥ ሊደፋም ይችል ይሆናል…..እዚህ ግን እቤቱ ያፈራውን ምርጥ ምግብ ለማያውቁት እንግዳ ሰው አብልተው እነሱ ደረቅ ዳቦ ይቆረጥማሉ..ለዛውም በጫወታ የደመቀ በደስታ የታጀበ ቁርስ ነው እየበሉ ያሉት…እነሱ ቤት ግን በኩርፊያ የታጀበ ቁርስ ነው የሚሆነው..ወሬ ካለውም በአሽሙርና በነቆራ የታጀበ በሚያስጠላ ጥል የሚገባደድ ነው የሚሆነው፡፡
ይበልጥ ሆድ ባሳት….‹‹በምንም አይነት ወደእዛ ቤት በቀላሉ አልመለስም››ለራሷ ዳግመኛ ቃል ገባችና አይኗን ጨፈነች..ደክሞት ስለነበረ ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡
‹‹የእኔ ልጅ ተነሽ….›› የሚል ድምጽ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት..ምን ያህል እንደተኛች አታውቅም፡፡ ብቻ አይኖቾን ስትገልጥ ልክ እንደቅዱሙ ያች ደግ እናት ምግብ በሰሀን ይዛ ልክ እንደህፃን ልጅ ልታጎርሳት ስሯ ቁጭ ብላለች፡፡
‹‹እማማ…አራበኝም እኮ ..አሁን አይደል እንዴ የበላሁት?››
‹‹አይ አሁን እኮ ሰባት ሰዓት ሆኗል…አባትሽ ላንቺ ሲል ነው ስጋ ገዝቶ የመጣው… እኔ እናትሽ ደግሞ ቆንጆ አድርጌ ሰርቼሻለሁ››
‹‹በሰማችው ነገር አንባዋ በአይኗ ግጥም አለ….››
‹‹ነይ እስኪ ለሊሴ ትንሽ ቀና ትበል ትራስ ደርቢላት›ለሊሴ መጣችና ደግፋ ቀና አድርጋ ትራስ ደረበችላትና ወደቦታዋ ተመለሰች …ቡና እያፈላች ነው..አቶ ለሜቻ ከለሊሴ ፊት ለፊት ባለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው በፀጥታ እየተመለከቷት ነው፡፡
‹‹እንጀራውን ጠቅልለው ወደ አፏ ዘረጉት…አፏን ከፍታ ተቀበለቻቸው…አላምጣ ከወጣች በኃላ…

‹‹እናንተስ አትበሉም?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹አዬ ልጄ …አኛማ በልተን ጨርሰን ቡና ስንጠብቅ አታይንም..አንቺ ብይ››አቶ ለሜቻ መለሱላት፡፡ወይዘሮ እልፍነሽ አብልተዋት ከጨረሱ በኃላ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነስተው ወደእሷ ተጠጉና ፍራሹ ጫፍ ላይ ተቀመጡ…የሆነ ነገር ሊጠይቋት እንደሆነ ገብቷት ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹ስምሽ ማነው ልጄ?››እስከአሁን ስሟን እና ማንናቷን እንኳን ሳያውቁ ይሄን ሁሉ እገዛና እንክብካቤ ሲያደርጉላት እንደቆዩ ስታስተውል ግርም አላት፡፡‹‹በፀሎት እባላለሁ››
‹‹እኔ አባትሽ..ለሜቻ እባላለሁ..እናትሽ ደግሞ እልፍነሽ ነው ስሟ….የመጀመሪያ ወንዱ ልጄ ፍራኦል..እሷ ደግሞ የእሱ ተከታይ ለሊሴ ትባላለች..፡፡››የቤተሰቡን አባላት ሁሉ በስማቸው እየጠሩ አንድ በአንድ አስተዋወቋት…በፅሞና እያዳመጠቻቸው መሆኑን ከተገነዘቡ በኃላ ንግግራቸውን አራዘሙ‹‹በእውነት በዛ ውድቅት ለሊት በዛ ሞተር ሆነሽ ከቤታችን ጋር ተጋጭተሸ ስትወድቂ በህይወት የምትተርፊ መስሎ አልተሰማኝም ነበር… ሁላችንም በጣም ፈርተን ነበር..ግን አምላክ ደግ ነው እና አጋልጦ አልሰጠንም…ተርፈሻል….ይመስገነው››
አሁን እሷቸው ሲናገሩ ሞተሩና ቦርሳዋ ትዝ አላት….ሞተሩ ምንም ቢሆን ግድ የላትም ቦርሳዋ ግን ያስፈልጋታል…
‹‹ወይኔ አባባ የሆነ ቦርሳ ይዤ ነበር …ጣልኩት እንዴ?››እሰከዛን ሰዓት ድረስ እንዴት ትዝ እንዳላላት ለራሷም ገረማት.፡፡፡
‹‹…አይ ልጄ አልጣልሺውም… ቦርሳውም ሞተሩም ጓዲያ ተቀምጦልሻል…ሞተሩን ወደውስጥ ያስገባነው ምን አልባት ችግር ላይ ሆነሽ ከፖሊስ እየሸሸሽ ወይም ከሆነ ሰው እየተደበቅሽ ከሆነ እንዳትጋለጪ ብለን ነው…››
‹‹አይ አባባ…እምልሎታለው የነገርኳችሁ እውነቴን ነው..ከፖሊስ ጋር የሚያገኛኘኝ ምን ነገር የለም…ከእንጀራ አባቴ ጋር ተጣልቼ ነበር …በለሊት ከቤት ወጥቼ በንዴት ስነዳ የነበረው››
‹‹አዎ እኔም ጠርጥሬለው…የቤተሰብ ችግር እንደሆነ ታውቆኝ ነበር››

‹‹ውይ ልጄ ይሄኔ እናትሽ በጭንቀት ልትፈነዳ ደርሳለች››ወ.ዘሮ እልፍነሽ በእናትነት አንጀታቸው የተሰማቸውን ተናገሩ ….ስለራሳቸው ልጆች እያሰቡ ስለነበር ነው ስሜቱ የተጋባባቸው፡፡
በፀሎት‹‹አይ እናቴ አትጨነቅም››ፍርጥም ብላ መለሰች፡፡
‹‹ምን ማለትሽ ነው ልጄ …?በጣም ነው እንጂ የምትጨነቀው..እናንተ ልጆች የእናትን አንጀት እስክትወልዱ ድረስ አይገባችሁም…ይሄኔ በየፖሊስ ጣቢያው እና በየሆስፒታሉ አንቺን ፍለጋ እየተንከራተተች ነው፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠንካራ እምነታቸውን በድጋሜ ገለፁ፡፡
‹‹እይ እደዛ ማለቴ አይደለም ..እናቴ ከሁለት ወር በፊት ነው የሞተችው›››
‹‹ውይ ታዲያ እንጀራ አባትሽ እናት የሞተባትን ልጅ ምን አድርጊ ነው የሚልሽ….?ሌሎች እህትና ወንድም የለሽም›?›
‹‹የለኝም እኔ ብቻ ነኝ››
‹‹ታዲያ በውድቅት ለሊት ምን አጣላችሁ?››


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አምስት


ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የቀኝ እጇ የመሀል ጣት ተነቃነቀ…እቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በደስታ ፈገገ ..ከአስር ደቂቃ በኃላ አይኖቾ ተከፈቱ፣አራቱም የቤቱ አባላት የተኛችበትን ፍራሽ በሁሉም አቅጣጫ ከበው በፈገግታ ያዩት ጀመር….ግራ ገባት፡፡መልሳ አይኖቾን ጨፈነች…፡፡መንቃቷ እራሱ የእውነት ሳይሆን በህልም አለም ውስጥ የተፈጠረ መንቃት ነው የመሰላት ፡፡ለዛ ነው ዳግመኛ እይኖቾን የጨፈነችው..፡፡መልሳ ስትገልጥ ያየችው ተመሳሳይ ነገር ነው….አራት ወዛቸው የተመጠጠ የለበሱት ልብስ የነታተበ ..በአባቷ ግቢ ውስጥ አትክልቶችን ከሚንከባከቡ ሰራተኞች በላይ ኑሮ የጠበሳቸው ጠና ያሉ ሰውዬ…ቆዳቸው የተሸበሸበ እናት… የ ሀያ አመት ልጅ እግር የምታምር ግን ደግሞ ያልተመቻት ልጃገረዶች..ባለጡንቻ ፈርጣማ እና ባለኮስታራ ፊት ሀያ አምስት ወይም ስድስት የሚሆነው ወጣት ..ጭስ የጠጣና ያረጀ የማዳበሩያ ኮርኒስ ያለው ጠባብ ክፍል…መሬት ላይ የተነጠፈ ፍራሽና ያረጀ በህይወቷ እንኳን ለብሳው አይታው የማታውቀው አይነት ብርድ ልብስ ለብሳ ነበር እራሷን ያገኘችው፡፡ግን እንደዛም ሆኖ የተለየ እና የማታውቀው ቦታ ያለች መስሎ አልተሰማትም….የሆነ ከዘመናት በፊት ታውቀው የነበረ እና ስትናፍቀው የቆየችው ቦታ ተመልሳ እንደመጣች አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው
‹‹…የት ነኝ?››
‹‹ልጄ…አሁን ሰላም ነሽ …ትንሽ አደጋ ደርሶብሽ ነው?››
‹‹የምን አደጋ?››
‹‹አሁን ሰላም ነሽ..በውድቅት ለሊት ሞተር ስትነጂ ነበር…ተገልብጠሸ ነው፡፡››
‹‹ሞተር››

‹‹አዎ..ሞተር..ከማን ስትሸሺ ነበር….?እስከአሁን ለፖሊስ አላሳወቅንም…..ይሄውልሽ እኔና ቤተሰቦቼ በህይወት ፈተና ጋር ግብግብ ገጥመን በትግል የምንኖር ሰዎች ነን…ከሆነ ወንጀል ጋር የተያያዘ ታሪክ ካለሽ እባክሽ.እኛንም ጣጣ ውስጥ እንዳንገባ ከአሁኑ ንገሪን››ሲል ፊራኦል ተናገረ፡፡
‹‹ምነካህ ልጄ? ልጅቷ ገና አሁን መንቃቷ ነው…ተው እንጂ ነውር ነው›እናትዬው ገሰፁት..አባትዬውም ለባለቤታቸው ድጋፍ በመስጠት‹‹ልጄ አዎ..አሁን ዋናው ያንቺ መትረፍ ነው ፡፡ሌላውን ቀላል ነው…የሰው ልጅ በህይወት ካለ የማያልፈው መከራ የማያሸነፍው የህይወት ትግል የለም..አሁን አንቺ ምንም አታስቢ..እኔነኝ የተባለ ውጌሻ ጠርቼያለሁ፡፡ ወለምታ ወይም ስብራት ነገር ካለሽ ያዩልሻል…ከዛ ካገገምሽ በኃላ ለቤተሰቦችሽ እንደውልላቸውና መጥተው ይወስዱሻል››
በፀሎት ለሊት በውድቅት ለሊት ከቤቷ አምልጣ እንዴት እንደወጣችና ምን እንዳደረገችና አሁን ያለችበት ቤትም የእነማን እንደሆነ ትዝ እያላት ሲመጣ ….የመረጋገትና የደስታ ስሜት ተሰማት‹‹አመሰግናለሁ…ምንም ወንጀል አልሰራሁም….ፖሊስም እየፈለገኝ አይደለም…አሁን ደክሞኛል ልተኛ..››አለችና መልሳ አይኖቾን ጨፈነች፡፡
‹‹ሰማችሁ አይደል..ምንም ወንጀል አልሰራሁም ብላለች..አሁን ዞር በሉላት …ትንፋሻችሁ እራሱ በሽታ ነው የሚሆናባት››አባትዬው ተቆጡ፡፡
‹‹አባዬ ደግሞ ፣አንተ ሁል ጊዜ ሰው እንዳመንክ ነው.. ሚገርመው ደግሞ ሰዎች ቃላቸውን እያጠፉ አንተን ማሳዘናቸውን አያቆሙም… አንተም ደግሞ ደግመህ አደጋግመህ እነሱን ማመንህን አታቆምም››ፊራኦል ተነጫነጨ፡፡
‹‹ልጄ ገለባ ቢዘሩት አይበቅልም ተጠራጣሪ ሰው አይፀድቅም ይባላል..ያገኘሁትን ሰው ሁሉ በመጠራጠር ህይወቴን ሳሰቃይ ከመኖር እያመንኩ ብከዳ ይሻለኛል…ቢያንስ በማመኔ ምክንያት የሚደርስብኝ ችግር ምክንያቱ እኔ አይደለሁም..››
ፊራኦል በወላጆቹ ውሳኔ ባለመስማማት ‹‹በሉ እሺ እኔ ወደ ስራ ሄጃለሁ፡፡››በማለት ቤተሰቡን ተሰናብቶ ግቢውን ለቆ ሲወጣ በራፍ ላይ ውጌሻዋ ወደውስጥ ስትገባ ተላለፉ፡፡
‹‹ቤቶች አቶ ለሜቻ››ሁሉም ግር ብለው ወጥተው ውጌሻዋን ተቀበሉና ወደውስጥ አስገቧት፡፡

‹‹የትኛው ልጅህ ነች… ለሜቻ?››
‹‹የወንድሜ ልጅ ነች ከድሬደዋ ልትጠይቀኝ መጥታ ነው››
‹‹እና ምን ገጥሟት ነው?››
‹‹ባኮት ከሆነ የሰፈር ልጅ ጋር ሞተር ተፈናጣ ስትሄድ ሞተሩ ተገለበጠባቸውና ትንሽ ተጎዳች..ምን አልባት ስብራት ወይም ወለምታ ይኖራት እንደሆነ ብለን ስለተጠራጠርን ነው ያስቸገርኖት፡፡››
በፀሎት የሚነጋገሩትን ሁሉ አይኖቾን ጨፍና እየሰማች ነው…
‹‹ታዲያ ተኝታለች?››
‹‹አሁን ነቅታ ነበር…እንዴት ነው እንቀስቅሳት?››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡
‹‹አይ ቆይ ተዋት ..ህመሙ እራሱ ይቀሰቅሳታል፡፡››አሉና ስሯ ፍራሽ ላይ ተቀመጡ…
‹‹ እስቲ እሱን የከሰል ፍም አቅርቡልኝ››ትዕዛዝ ሰጡ፡፡
ማንደጃው ቀረበላቸው…‹‹ እስኪ አንዳችሁ ኑና የለበሰችውን ልብሷን አውልቁላት…..››ለሊሴ ፈጠን ብላ መጣችና ከላይ የለበሳቸውን ጃኬት… ቦዲ ተራ በተራ አወለቀችላት… በጡት ማስያዣ ብቻ አስቀረቻት ፡፡አንገቷ ላይ ያለው የእጅ መዳፍ የሚያህል አብረቅራቂ እንቁ ፈርጥ ያለበት ጌጥ የሁሉንም አይን በቅፅበት ተቆጣጠረ
….ጆሮዋ ላይም ያንጠለጠለችው የጆሮ ጌጥ ከአንገት ሀብሏ ጋር እንዲናበብ ተደርጎ የተሰራ ለልደት በዓሏ ከአባቷ የተበረከተላት ልዩ አይነት ጌጥ ስለሆን በተለይ የሌሊሳን ትኩረት በደንብ ነው የተቆጣጠረው…ሁሉም ግን አርቴ እንጂ ትክክለኛ ነው ብለው አላሰቡም ነበር፡፡
ውጌሻዋ ቦርሳቸው ውስጥ እጃቸውን ሰደዱና በብልቃጥ ከለጋ ቅቤ ጋር ተለውሶ የተዘጋጀ መዳህኒታቸውን አወጡና ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው በሌባ ጣታቸው ዛቅ እያደረጉና በመሀል አጣታቸው ላይ አድርገው በመላ መዳፋቸው ላይ ለቀለቁና ስራቸው በቀረበላቸው የከስል ፍም ላይ ጠጋ አድርገው ሙቀት እንዲያገኝ ካደረጉ በኃላ ከአንገቷ ጀምሮ ትከሻዋን እያሹ መፈተሽ ጀመሩ‹‹ ..ምንም አልሆነችም እስኪ ሱሪዋን አውልቁልኝ››ሌላ ትዕዛዝ ሰጡ..በዚህ ጊዜ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነሱና ወደውጭ ወጡ..ሴቶቹ እንደምንም

ታጋግዘው የለበሰችውን ጅንስ ሱሪ ከላዮ ላይ አወለቁና በፓንት ብቻ ለውጌሻዋ አስረከቧት
…ውጌሻዋ ተመሳሳዩን እሽት ከጭኖቾ ጀመረው ወደታች መውረድ ጀመሩ…ቀኝ እግሯ ቁርጭምጭሚቷ ጋር ደርሰው ጨበጥ..ጨበጥ ሲያደርጓት ግን ከተኛችበት እንደመብረቅ አጓርታ ተነስታ ቁጭ አለች…ሁሉም በድንጋጤ የሚያደርጉት ጠፋቸው..‹‹አዎ እዚህ ጋር ችግር አለ‹‹አሁን በደንብ አድርጋችሁ ግራና ቀኝ ትከሻዋን ያዟት፡፡››የውጌሻዋን ትዕዛዝ ስትሰማ አይኖቾ በፍራቻ ተጉረጠረጠ፡፡በእድሜዋ መርፌ ለመወጋት እሩሱ በስንት እዝጊዎታና ማባበያ ነው...ታዲያ አሁን እንዲህ ላይቨ በስቃይ ስትፈተን እንባዋ ረገፈ
፡፡እናትና ልጅ ግራና ቀኛ ትከሻዋን አጥብቀው እንዳትነቃነቅ ያዙዋት..ሴትዬዋ እየጨመቁና እያሽከረከሩ ያሾት ጀመር…በህይወቷ ተስምቷት የማያውቀው አይነት ህመም…..ተሰማት..የሆነ መጋዝ ጥርስ ያለው አዞ በሁለት መንጋጋዎች መሀከል እግሮቾን አስገብቶ እያኘካት ነው የመሰላት..እንባዋ ብቻ ሳይሆን ንፍጦም በአፍንጫ ላይ እየተዝረከረከ እንደሆነ ይታወቃታል…ለዛ ግን የምትጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለችም…..ውጌሻዋ ከ10 ደቂቃ በኃላ የተሰበረውን አጥንት ወደቦታው ከመለሱ በኃላ እንዳይነቃነቅ በቀርከሃ በደንብ አድርገው ከሰሩት በኃላ በፋሻ ጠቅልለው አጠናቀቁ…ከዛ እቃቸውን ሰብስባው ተነሱ…ለሊሴ የራሷን ቢጃማ አለበሰችትና መልሰው አስተኞት፡፡
‹‹እልፍነሽ››
‹‹አቤት እማማ››
‹‹ለሜቻ ድሬደዋ ሀብታም ወንድም አለው እንዴ?


ይርበኛል፡፡
አባዬ እንደነፍስህ የምትወዳቸው ሁለት የአንተ አንደኛ ሰዎች አንድ ቤት እየኖሩ እንደጠላት ሲታያዩ ከማየት የበለጠ የሚያስጣላና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም….አሁን አሁን ሳድግ ተስፋ ቆርጬ ተውኩ እንጂ በፊት እናትና አባቴ ግራና ቀኝ እጄን ይዘው እርስ በርስ እያወሩና እየተሳሳቁ ወደ መዝናኛ ቦታ ወይም ዘመድ ቤት ይዘውኝ ሲሄዱ አልም ነበር..ሁሌ የማየው ህልም እንደዚህ አይነት ነበር…ያን ህልም ግን አንድም ቀን እውን ሆኖልኝ አያውቅም….ከቤት ውጭ ከሁለታችሁም ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የትም ሄጄ ሆና የትም ቦታ ተገኝቼ አላውቅም……ወይ አንተ ትጎድላለህ ወይ ደግሞ እማዬ ትጎድላለች…ይሄ ምን ያህል ልቤን እንዳቆሰለው አታውቅም….ደግሞ ታውቃለህ በውስጤ

የተሸከምኩት የሌላ ሰው ልብ ነው…ያንን ልብ በአደራ ነው የተረከብኩት ….ላሰቃየውና ላጨናንቀው መብት የለኝም…. እንደአለመታደል ሆኖ ግን በፍቅር የተሰጠኝን ልብ በስርአቱ ተንከባክቤ እንድይዘው እናንተ እየፈቀዳችሁልኝ አይደለም፡፡
አባዬ ይገርምሀል ..ሁል ጊዜ ስለአንተእና ስለእማዬ ሳስብ ‹‹ ቆይ ሁል ጊዜ እንዲህ እየተጠላሉ..ለምን ባልና ሚስት ተብለው አንድ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ? ብዬ በተደጋጋሚ እራሴን ጠይቅ ነበር…፡፡አሁን ግን ለምን እንደሆነ መገመት እችላለው…አንድም እኔ እንቅፋት ሆኜባችሁ ነው…እንደውም ብዙ ጊዜ አንቺን በስለት ነው የወለድንሽ ብላችሁ በየአመቱ መደገሳችሁ ለበጣ ይመስለኛል..ተፈልጋ ለዛውም በስለትና በፀሎት ተወለዳ በጸሎት የሚል ስም የወጣላት አንድ ብቸኛ ልጅ ያላቸው ጥንዶች እንዴት እንዲህ ሊጠላሉ ይችላሉ..?እንዴት ልጃቸውን በፍቅር እጦት ሊያሳቃዩና ሊያሰቅቁ ይችላሉ…? ይሄ የሚያመለክተው ለእኔ ያላችሁ ፍቅር የውሸት እንደሆነ ነው፡፡ፈፅሞ ሁለታችሁም ትወዱኛላችሁ ብዬ አላስብም ፡፡ምን አልባት ከእኔ በላይ ሀብታችሁን አምርራችሁ ትወዱ ይሆናል፣ሁለታችሁም ላለመለያየትና በዛአይነት ጥላቻ ውስጥ ሆናችሁም ቢሆን በአንድ ጣሪያ ስር መኖር መቀጠሉን የመረጣችሁት ሀብታችሁን ላለመበታተን ሰስታችሁ ይመስለኛል፡፡እና ለዚህ ስል ሄጄያለው…ከእናንተ በጣም እርቄ ሔጄያለው፡፡አንድ ቀን ግን ተመልሼ መጣለሁ፡፡ መች እንደምመጣ አላውቅም፡፡ እሱ የእናንተ ውሳኔ ነው…እንድመለስ ከፈለጋችሁ በዚህም ብላችሁ በዛ ህይወታችሁን አስተካክሉ…፡፡ወይ በቃን ብላችሁ ተለያዩና የየራሳችሁን ህይወት መኖር ቀጥሉ፣ቢያንስ በዚህ ውሳኔ ከሁለት አንዳችሁ በቀሪ ህይወታችሁ ደስተኛ የመሆን እድል ይኖራችኋል…ካለበለዘያም ቁጭ ብላችሁ ተነጋገሩና ይቅር ተባብላችሁ ያለፈ ህይወታችሁን ጨለማ ታሪከ ዘግታችሁ ለራሳችሁ እንደባልና ሚስት ለእኔም ደግሞ እንደወላጅ ለመሆን ተዘጋጁ…..እስከዛው ልትፈልጉኝ እንዳትሞክሩ ልታገኙን አትችሉም…ብታገኙኝም ወደቤት ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆንም….ግን ባለሁበት ሆኜ በራሴ መንገድ እከታተላችኃላው….በእናንተ ዙሪያ መኖር ለእኔ ምቹ ነው ብዬ ባመንኩበት ሰዓት እመጣለሁ..ካልሆነም ከእናንተ እንደራቅኩ የራሴን ህይወት እኖራለሁ..፡፡አባዬ አይዞህ ስለበሽታዬ አትጨነቅ…አትጨነቅ የምልህ በእኔ ጥንካሬ ስለምተማመን አይደለም..በውስጤ ያለው የልጅቷ ልብ እጅግ ጠንካራ ስለሆነ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ያወቅኩት የእኛን ቤት ያንን ሁሉ ጥላቻና ጥል ተቋቁሜ እስከአሁን በህይወት የኖርኩት እና ኮላፕስ ያላደረኩበት ብቸኛ ምክንያት የተሸከምኩት ልብ ጥንካሬ ነው፡፡በል ቸው አባዬ… ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ …በጣም እወድሀለው፡፡

ይላል ደብዳቤው፡፡አቶ ሃይለመለኮት ደነዘዙ፡፡ምን ማድረግና ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው እየገባቸው አይደለም፡፡ልጃቸው በእሷቸውም ሆነ በሚስታቸው ይሄን ያህል መጎዳቷ እና መማረሯን ፈፅሞ ልብ ብለውት አያውቁም ነበር፣በዚህም በራሳቸው አፈሩ…. ደብዳቤውን ደረት ኪሳቸው ውስጥ ከተቱና ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡

ይቀጥላል....

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አራት

በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኃላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››

‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡
‹‹ምን እያወራህ ነው?››
‹‹በፀሎት..››
‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡
‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››
‹‹የለችም ማለት…….?››
‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››
‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡
‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››
‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡
‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››
‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኃላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድካዋን ለማግኘት አልተቻለም…
በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡
በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገብና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጽም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡
አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ

ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡
አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…ባቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኃላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ከድሮዬ በተለየ ፍቅር


ጉዞ በፀሎት የተሰኘዉ ልቦለድ ይለቀቃል adminu አልተመቼዉ ሆኖ ነዉ ☺️


‹‹አባዬ…ይሄ ነገር በእኛ እንዳይሳበብ…ከመነካካታችን በፊት ለፖሊስ ደውለን እናሳውቅ፡፡››ወንዱ ልጅ ስጋቱን ለአባቱ ተናገረ፡፡
‹‹ልጄ ገና ለገና እንጠየቃለን ብለን በሰው ህይወት ላይ እንፈርዳለን….?አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም›› በማለት…ሰውዬው ተጠጋና ቀስ ብሎ ሄልሜቱን ፈቶ አወለቀው….ረጅምና ዞማ ፀጉሯ ዝንፍል ብሎ መሬቱን ሞላው፡፡ፊቷ በደም ተሸፍኗል፡፡
‹‹በጌታ ሴት ነች››እናትዬው ተናገሩ፡፡
አባትዬው እጁን ወደ ልጅቷ አንገት ላከና በህይወት መኖሯን አለመኖሯን ለማረጋገጥ ሞከረ፡፡‹‹ተመስገን አለች፣ትተነፋሳለች….ቀስ ብለን ወደቤት እናስገባት…››
‹‹እንዴ አባዬ ለፖሊስ እንደውልና እነሱ ሀኪም ቤት ይውሰዷት››ወንዱ ልጅ ስጋቱን መለሶ አስተጋባ፡፡
‹‹አይ…አይሆንም ፡፡በዚህን ሰዓት እንደዚህ አይነት አለባበስ ለብሳ እንዲህ አይነት ሞተር የምትነዳ ሴት የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ፣…ምን ላይ እንዳለች ሳናውቅ ለፖሊስ በመደወል አሳልፈን አንሰጣትም…አይሆንም..ይልቅ ና ከታች ቀስ ብለህ ያዛት
…ወደቤት እናሳገባት….››አባትዬው ጠንከር ባለ ንግግር ውሳኔያቸውን አሳወቁ፡፡
ወጣቱ ሳይመስለው አባትዬው እንዳለው አደረገ ….ወስደው ጠባቧ ሳሎን ከተዘረጋው ልጆቹ ተኝተውበት ከነበረ ባለሜትር ከ20 ፍራሽ ላይ አስተኟት፡፡እናትዬው ቦርሳውን አንጠልጥላ በማስጋበት ወደ ጓዲያ ወስደው አስቀመጡት፡፡ ….ከላይ የለበሰችው ልብስ አወለቁላትና የቆሰለ ወይም የደማ ቦታ እንዳለ መፈለግ ጀመሩ ግንባሯ ላይ ከጀርባ በኩል የሚፈስ ደም አለ ግማሽ ፊቷ ቆዳዋ ተገሽልጦ በደም ተሸፍኗል፡፡ ሌላ ቦታ ሰላም ትመስላለች፣ቢያንስ ለጊዜ የሚታይ ቦታ የለም፡፡
‹‹ምን እናርግ..ፊቷ እኮ በጣም ተጎድቷል…ደሟም እየፈሰሰ ነው..የግድ ህክምና ማግኘት አለባት፡፡››

ሴቷ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረች‹‹እዚህ ከጀርባችን ያለው ኪሊኒክ ለምን አንወስዳትም?››
‹‹በሊሊት ይሰራሉ እንዴ?››
‹‹አዎ ተረኞች አሉ…፡፡››
ወደኪሊኒክ በመውሰዱ ሁሉም ተስማሙ…ወጣቱ ልጅ እና አባትዬው ተራ በተራ እያዘሉ ከቤታቸው ግማሽ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ኪሊኒክ ወሰዷት…ሀኪሞቹ ቁስሏን አፅድተው ግንባሯ ላይ የለውን ስንጥቅ ሰፍተውና ግማሽ ፊቷን በፋሻ ሸፍነው ህክምናቸውን ጨረሱ…ለማንኛውም ሆስፒታል ወስደው ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ እንዲያደርጉ አዛው… ሸኞቸው፡፡
እነሱ ግን ቀጥታ ወደቤት ነበር የመለሶት፡፡….እሷ ያ ሁሉ ሲሆን ከገባችበት ከፊል ሰመመን አልነቃችም ነበር፡፡….ከዛ አቶ ለሜቻ ከልጃቸው ከፊራኦል ጋር እየተረዳዱ በማዘል ወደበት ከመለሷት እና መልሰው ካስተኞት በኃላ በዛ ውድቅት ለሊት በሞተሩ የተጣሰውን የውጭ አጥር ወደነበረበት መለሱና ሞተሩን ተጋግዘው ወደውስጥ በማስገባት ጎዲያ ውስጥ አስገብት፡፡
ፊራኦል‹‹አባዬ ምን እያደረክ እንዳለ ምንም አልገባኝም?››ሲል አባትዬውን የጠየቀው
‹‹ልጄ እንደምታያት ልጅቷ ሴት ነች..ወጣት ሴት…..እንዴትም አድርጌ ባስበው በዚህ እድሜ ያለች ሴት ልጅ በሰላም ሆና በዚህ ውድቅት ለሊት ሞተር አትነዳም…ልጅቷ የሆነ ችግር ላይ ነች….››
‹‹እኮ እኔም እኮ ምለው እንደዛ ነው..ችግር ላይ ነች..እኛንም አብራ ችግር ውስጥ ትከተናለች እያልኩህ ነው፡፡››
‹‹ልጄ ስጋትህ ይገባኛል …ትክክልም ነህ፡፡እኔ ግን አባት ነኝ…እንደእሷ ልጆች አሉኝ..ነገ እንሱም የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ እና እንዲህ የማያውቁት ቦታ በማያውቁት ሰው እጅ ሊወድቁ ይችላሉ ..ለልጆቼ ጡር አላቆይም…ይህቺ ልጅ ከገባችበት ሰመመን ነቅታና ከህመሟ አገግማ የሆነችውን ከነገረችን በኃላ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስናለን..እስከዛ ግን አይሆንም››
‹‹ከረፈደብንስ?›››

‹‹ከረፈደብን ስትል….?››
‹‹ምን አልባት ባትነቃስ?››
‹‹ተው ልጄ ..እንደዛ አይሆንም….አምላክማ እንዳዛ አሳልፎ አይሰጠኝም፣በል አሁን ተነስ ከብርድ ላይ እንግባ፡፡››
አካባቢው ትኩረት የሚስብ ነገር አለመኖሩን ካረጋገጡ በኃላ ከለሊቱ 10 አካባቢ ለመተኛት ወደውስጥ ተያይዘው ገቡ…እናትዬው እና ለሊሴ የለሌት እንግዳዋን በግራና በየቀኝ አጅበው በድንጋጤ እንዳፈጠጡ ቁጭ ብለዋል….፡፡
እናትዬው ወ.ሮ እልፍነሽ አንዴ ጓዳ ፤ሌላ ጊዜ ሳሎን ይመላለሳሉ…መልሰው ደግሞ ከጎኗ ቁጭ ይላሉ… በፍራቻና ግራ በመጋባት እህህ እያሉ ያጉረመርማሉ‹‹ይሄኔ እናቷ አላየቻት፣ወይ የሰው ልጅ፣አሁን እሺ ባትነቃስ?››ብቻቸውን ይለፈልፋሉ፡፡

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️


ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሶስት

በፀሎት የልብ ንቅለ ተከላ ካደረገች በኃላ ልክ እንደዛሬው አይነት በህይወቷ ወሳኝ የሆኑ ትላልቅ ውሳኔዎችን አሳልፋለች….አንዳንዴ‹‹ በእውነት እንዲህ እያሰብኩና እያደረኩ ያለሁት እኔው ነኝ?››ብላ በራሷ እስክትደመም ድረስ ነበር ለውጦ፡፡

‹‹አሁን የሌላ ሰው ለዛውም የሞች ንፅህ ልብን በሰውነቴ ተሸክሜ ርካሽ የሆነ ስራ ፈፅሞ አልሰራም››የሚል አቋም ላይ ደርሳ በዛ መሰረት ነው የምትንቀሳቀሰው…ትንሽ ለስሜቷ የማይመችና የሚቆረቁር ነገር ሲያጋጥማት እንደድሮው ‹‹ቆይ እስኪ ልሞክረው›› ብላ ዘላ አትገባበትም….ጊዜ ወስዳና ተረጋግታ ታስብበታለች..ነገሩን ትመዝንና እሷንም ሆነ ሌላውን ሰው የሚያሳዝንና የሚያስከፋ መስሎ ከተሰማት ወዲያው መንገዷን ታስተካክላለች….ይሄ በብዙ ነገሮች ጠቅሟታል…ግን ደግሞ ቤተሰቦቾን በተመለከተ እንደበፊቱ ነገሮችን አይታ እንዳላየች እንድታልፍ አላደረጋትም…እያንዳንዱ በመሀከላቸው ያለው ጥላቻና ጥል በጣም ያስጨንቃትና እረፍት ይነሳት ጀመር…ለምን ብላ እንድትጠይቅ..ጥፋቱ የማንኛቸው ይሆን እያለች እንድትመረምርና ፣እንዴት ሊስማሙና ትክክለኛ ባልና ሚስት ሆነው ለእሷም መቼ እንደ ትክክለኛ ወላጅ የምትፈልገውን ፍቅር ሊለግሶት እንደሚችሉ ማለምና መተከዝ የጀመረችው ከበርካታ ወራቶች በፊት ነው፡፡
በፀሎት  ጨረቃ በነገሰችበትና ከዋክብቷች ሰማዩ ላይ ተበትነው በሚንሸራሸሩበት በዛ ውድቅት ለሊት እቤቷን ጥላ ..ከእናትና አባቷ ርቃ …ከጋደርዶቾ አምልጣ መሄዷን እንጂ ወዴት እንደምትሄድ ለምን ያህል ሰዓት መንዳት እንዳለባትና የመንገዷ ማዳረሻ የት እንደሆነ ምንም የምታውቀው ነገር የለም፡፡ዝም ብላ ብቻ በዛ ውድቅት ለሊት የአስፓልቱን መሀከል ይዛ በመድሀንያለም ቤተክርስቲያንን አጠር ተኮ በሚገኘው መንገድ ወደፊት በመውጣት ዋናውን አስፓልት ገባችና ቀጥታ ወደ ስቴዲዬም ሚወስደውን መንገድ ያዘች….መስቀል አደባባዩን እንደጨረሰች ወደግራ ታጠፈችና ወደላንቻ የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ ያዘች..
ከትራፊክ መጨናነቅ ነፃ የሆነውን መንገድ በፍጥነት መጋለብን ተያያዘችው…ምንም ሳታውቀው ለአንድ ሰዓት ያህል ከነዳች በኃላ አቃቂ ድልድይ ጋር ስትደርስ ወደቀኝ ተጠማዘዘችና ወደአቃቂ የሚወስደውን መንገድ ገባች ፣…መንዳቷን ቀጠለች…ድንገት ተረጋጋችና ሞተሩን አቀዝቅዛ አቆመችና አካባቢውን ስታስተውል የምታውቀው ሰፈር ሆኖ በማግኘቷ ደነገጠችም.. ተገረመችም….እዚህ ሰፈርና እዚህ ቦታ ለመምጣት ባለፈው ሁለት አመት ስትመኝ ነበር….ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በህልሟ እዚህ አካባቢ መጥታ ስትዳክር ነው የምታየው..ግን መጥታ የምትፈልገውን ነገር ለማድረግ አባቷ ሊፈቅድላት አልቻለም..ለጠባቂዎችም በጥብቅ ስለተነገራቸው እንኳን አሁን ያለችበት ሰፈር ይቅርና ክፍለከተማው ውስጥም ዝር እንድትል እንዳይፈቅዱላትም ፤ከዚህ ቀደም ምንአልባትም ከአመት በፊት ሰፈሩንና እቤቱን ለአንድ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ ያሳያት እራሱ አባቷ ነበር፡፡

በጊዜው መኪናዋን አሁን ሞተሯን ያቆመችበትን ቦታ አቁሞ…የቤቱን በራፍ በጥቁሩ የመኪና መስታወት ወደውጭ እየጠቆመ…‹‹አየሽ የልጅቷ ቤተሰቦች የሚኖሩት እዚህ ነው..እኛ አሁን የሚገቡት አባቷ ናቸው…አብሯቸው ያለው ደግሞ ልጃቸው ነው….እናትና እህቷም አሉ››እያለ ነበር ያብራራላት፡፡
‹‹አባዬ እንዲት እንዲህ ጭንቁርቁስ ያለ ቤት እንዲኖሩ ትፈቅዳለህ..?እየው እስኪ አጥሩን..እቤታቸውን ተመልከተው››በምሬት አባቷን መጠየቋን ታስታውሳለች፡፡
‹‹ልጄ ምን ላድርግ ?በግድ በወታደር አስገድጄ ሌላ ቤት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አልችል››
‹‹ማለት…?››
‹‹ነግሬሻለሁ እኮ …ቤተሰቡ ከእኛ አምስት ሳንቲምእንደማይቀበሉ ምለው ነው የነገሩን››
‹‹አባዬ ይሄ ምንም ሊገባኝ አልቻለም…የተሸከምኩት እኮ የልጃቸውን ልብ ነው….በልጃቸው ሞት እኮ ነው አሁን እኔ በህይወት መኖር የቻልኩት…አልገባህም አባዬ …ለምን እሷ ሞታ እኔ ኖርኩ..?እግዚያብሄር ይሄን እንዴት ፈቀደ…?.አባዬ በየቀኑ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ነው…እየተሰቃየሁልህ ነው…››
‹‹አውቃለው  ልጄ…እነሱ  ፍቃደኛ  ቢሆኑ  እኔ  የሀብቴን  ግማሽ  እንኳን  ብሰጣቸውና
..ላደረጉልኝ ነገር ምስጋና ባቀርብ ደስ ይለኝ ነበር…ግን ተቀባይ ከሌላ መስጠት ስለፈለግሽ ብቻ አይሳካልሽም፡፡››
‹‹ቢሆንም አባ ..እኔ ልቧን ሰጥታኝ ህይወቴን እንዲራዘም ያደረገቺኝን ልጅ ቤተሰቦች እንዲህ በጉስቁልና እንዲኖሩ አልፈልግም…..ልጃቸው በህይወት ኖራ ቢሆን ትጦራቸው ነበር…የሆነ የሆነ ነገር ታደርግላቸው ነበር….ብቻ አላውቅም የሆነ ዘዴ ፍጠርና እርዳቸው፡፡››
‹‹አይ ልጄ አልገባሽም እንዴ…ልጃቸው ላንቺ ልብ ከመስጠቷ ከአመታት በፊት በእኛ ፋብሪካ የሚሰራውን ወንድ ልጃቸውን እራሱ ስራ እንዲለቅ አድርገውታል…..ለማንኛውም የተቻለኝን እሞክራለው..አሁን ይሄን ያህል ካየሻቸው ይበቃሻል… አንሂዱ ››ብሎ ነበር ከአካባቢው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለቀቁት፡፡

ከዛ ወዲህ ግን ፍፅም ወደአካባቢው እንድትጠጋና ከቤተሰቡ ጋርም በምንም አይነት መንገድ ተገኛኝታ እንዳትተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ተሳክቶላቸዋል…አሁን ግን ይሄው በደመ ነፍሷ ከቤቱ ፊት ለፊት አስፓልቱ ጠርዝ ላይ ሞተሯን አቁማ ቁልቁል አዘቅዝቃ እያየችው ነው፡፡
‹‹ወደእዚህ መምጣት በአእምሮዬ ስሌት ውስጥ አልነበረም….ሳስበው ግን የልጃችሁ ልብ ነው እየመራ እዚህ ድረስ ያመጣኝ››ስትል አጉረመረመች፡፡ድንገት ስሜታዊ ሆነችና ነዳጁን ረገጠችና ጨምቃ የያዘዘችውን ፍሬን ለቀቀች…አስፓልቱ ን ለቃ ቀጥታ ወደቤቱ አቅጣጫ መንዳት ጀመረች …የሞተሩ ፍሬን ድንገት እምቢ አላት… ያ ደግሞ ጠቅላላ ሰውነቷ በፍራቻ እንዲቀዘቅዝ ነው ያደረጋት…ሞተሩ ከቁጥጥሯ ውጭ እየወጣ ነው.. መንገድን ሰታ ወደቀኝ እየተጓዘች ነው…›የተውሸለሸለ የእንጨት አጥር ቤት ጥሳ ገባች…. የቆርቆሮ በር ካለው ሰርቢስ ቤት በራፍ ጋር ተላትማ በአየር ላይ ተንሳፈፈችና መሬት ላይ ጧ…ጧጧ ብላ ወደቀች....ሞተሩ አጥሩን ጥሶ ሲገባና ከቆርቆሮ በራፉ ሲጋጭ የፈጠረው ድምፅ የፍንዳታ አይነት ነው….እሷ ወዲያው ነው ጭልም እያለባት የሄደው…እንዲህ ባለ ሁኔታ እራሷን አደጋ ላይ የመጣል እቅድ አልነበራትም…….ከቤት ውስጥ ግን ቡዙ ጫጫታና ትርምስ ተሰማ…
‹‹አማዬ ምንድነው……?››
‹‹.ልጆቼን ..››
‹‹ልጆቼን ››
‹‹አባዬ ሰላም ነህ?››
የሶስት ወይም የአምስት ሰዎች ድምጽ እየተሰማት ነው….እያንዳንዱ ድምፃ ልቧ ላይ እየተንጠባጠ እያቀለጣት ያለ ነው የመሰላት፡፡‹‹ምን ሆኜ ነው …?ምን ተፈጠረ…?ይሄን እያሰበች ሳለ ጭልም እያለባት ሄደ ፣እንደምንም ላለመጥፋት ብትሞክርም አልቻለችም
…እራሷን ሙሉ በሙሉ ሳተች….፡፡እቤቱ ውስጥ ያለ አንድ ጎረምሳ እና አንድ ወጣት ሴት… እናት አባት በዛ ውድቅት ለሊት ፈጣሪ ምን አይነት መብረቅ እንደላከባቸው ለማወቅ በሀይለኛ ድንጋጤ እንደተመቱ የተተራማመሱ የቤታቸውን በራፍ እንደምንም ተራ በተራ እየተጋፉ ወደውጭ ወጡ….የውጭ መብራት አብርተው ሲመለከቱ ..ከበራፉ በሶስት ሜትር ርቀት መሬት ላይ የተዘረጋ ጥቁር እና ነጭ ቀለም የተቀባ ዘመናዊ ሞተር ሳይክል ይታያል...ከሳይክሉ ሁለት ሜትር ርቀት አንድ ሄሌሜት ያደረገ ባለመካከለኛ ቁመት ሰው እጥፍጥፍ ብሎ ወድቆ ይታያል....ሁሉም በቃል ሰይነጋገሩ እየሮጡ ሰውዬውን ከበቡት…


እልልታ
ጭብጨባ
ከአውደ ምህረቱ ተነስቶ ይነፍሳል፤
የሰማእቷ ታ'ምር እንደ ጉድ ይወሳል።

"ሰምታኛለች እናቴ..."
"ታውቃለች አርሴማ..."
ክብሯን የሚመጥን
ይገባል ስለት - ጧፍ፣ ጥላ፣ ብር፣ ሻማ።

ሰው ይጸልያል
ሰው ይለምናል ክፍተቱን አይቶ፣
እኔ ከንቱ ግን
የጎደለኝን አላውቅም ከቶ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፣
ደጅሽን ስረግጥ እታደሳለሁ።

እዪኣት ያቺን ሴት
ከአትሮንሱ ጀርባ የምትዘምረው
ስምሽን ደጋግማ የምታነሳው፤
እኔ እስከማውቃት
ፊደል የሚያንቃት
ኩልትፍ አንደበት - ነው የነበራት።

ምን ጸልያ ነው አፏ የተፈታ?
ምን ብላሽ ይሆን
ቃል አቅሙን አጥቶ ለእሷ የተረታ?
የእኔማ ምላስ አግድም ለፋፊ
ለ'ንቶ ፈንቶ እንጂ ለጸሎት ታጣፊ።

እይው ያንን ሰው
ኑሮ የደቆሰው
የደስታን እንባ ሞልቶ ሚያፈሰው፤
እኔ እስከማውቀው
ሞት 'ሚናፍቀው
ማጣት በዝቶበት ገዳይ ሚፈልግ
ተስፋን ተነጥቆ
አለመኖርን የሚያነበንብ።
ምን ሰጥተሽው ነው ፊቱ የፈካ?
ምን አግኝቶ ነው
የደስታው መጠን ጣሪያ የነካ?
እኔ ሳቅ አላውቅ እንባም አይገደኝ
መኖርም መሞት ትርጉም አይሰጠኝ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፤
ደጅሽን ስረግጥ ነፍስ እገዛለሁ።

#ኤልዳን


#የኢትዮጲያው
ሰይጣን
#ለአውሮፓው
ሰይጣን የጻፈው
ደብዳቤ» በአዜብ መሰለ
****
እንደምነህ ሰይጣን ያውሮፓው ወንድሜ
እኔ አለሁ በመዝሙር በፀሎት ደክሜ።
😴
“አይጥ ሞቷን ስትል ስታበዛ ሩጫ
ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ።”
የሚሉት ሆኖብኝ ኢትዮጲያ መጥቼ
ይኸው እነሳለሁ ዕለት ዕለት ሞቼ።
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እነዴት ነው አውሮፓ ነዋሪው በሙሉ?
‘ቸርች’ ሰርተውልህ
ስምህን በመጥራት
#ያመልኩሀል
አሉ።
😋
የእኔን አትጠይቀኝ…!
😔
እዚህ
#በመስጊዱ
በአራቱም ማእዘን በዱዓ በፀሎት
አላህ ነው ሚወደስ…
🙄
እሱ ነው ሚመለክ ሰርክ ቀንና ሌት።
እኔማ መሮኛል…!
ዘወትር መዋረድ ነጋ ጠባ ቅሌት።
ግን አንተ እንደም’ነህ?
🫡
ታገኛቸዋለህ ናኒን እና ሩኒን
‘ህይወት’ ሰጠሀቸው በመርፌ በኪኒን?
እዚህ
#ኪኒን
ብትሰጥ የለም የሚቀበል
ሁሉ
#ዳንኩኝ
ይላል እየጠጣ
#ፀበል
😏
እኔማ ተቃጠልኩ…
🤬
እዚም እዛም ስፍራ ውሃ እያፈለቁ…
“በስመአብ ወወልድ” በስመ ስላሴ እያሉ ሰው እያጠመቁ
ስንቱን
#የያዝኩትን
በግድ
#አስለቀቁ

😠
አንተ ግን እንዴት ነህ?
🤔
እንዴት ነው አውሮፓ ጎዳናው መንገዱ?
ለማኞቹስ አሉ?
“ሆምለስ” ብለው ፅፈው ብሶት የሚያስረዱ።
እዚ ያሉ ለማኞች አቤት ሲያናድዱ!
“ምስኪን”ብለው ፅፈው ማሳጠር ሲችሉ
በአዛኚቷ
#ማርያም
በእግዚአብሔር እያሉ…
🙏
የሰው አንጀት በልተው፤
የእኔን አንጀት ደሞ ያንጨረጭራሉ።
🥶
ደሞ ሙስሊሞቹ አያተል ኩርሲን
አጣቅሰው ሲቀሩ
#ብረር
ብረር ይለኛል ከሰፈር ካገሩ።
አንተ ግን ደህና ነህ?
እዛ አገር እንዴት ነው?
ወጣቱ ፈጣን ነው? ወይስ ይዘገያል?
በጭፈራ መሀል…
💃
🕺
ያንተን
#ቀንድ
፣ያንተን ዐይን
#ምልክት
ያሳያል?
☹️
እዚህ ‘እኔን ተወኝ…!
😴
የሀበሻ ነገር ባህሪው ይለያል።
ጭፈራ ቤት ገብቶ _
መጠጥ ሊጠጣ ያዝ‘ና
#በደሌ
‘ሚያስከፍተው ዘፈን…
“እመቤቴ ማርያም አርጊልኝ
#የግሌ
”።
/ ኧ…ረ …! እንደው እ…ድ…ሌ! /
🤦‍♂
እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ…
··
ላንተ ይቀርብሀል
#ዩኔስኮን
ካገኘህ ‘ ባክህ ንገርልኝ
ይቺን ጉደኛ ሀገር
🇪🇹
“ለሰይጣን ‘
#ማትመች
” ብሎ ይመዝግብልኝ😂😂

ካነበብኩት🤗🤗🤗


የአብ!

በአምሳሉ በጥበቡ
          የሰራን፣
ኩሎ በምግባር
        የፈጠረን፣
በህጉ ስር የምንኖር፣
በሰው አምሳል ተገኝቶ
          የሚመክር፣
እኛ ነን ልጆቹ እኛ ነን
           ተማሪዎቹ፣
ደሙን በቀራኒዮ
     እርቃኑን ተሰቅሎ ያበቃን
                ደቀመዝሙሮቹ፣
የአብ ስራ የወልድ
       የመንፈስ ቅዱስ፣
ባሪያዎች የምናመሰግን
        የሚያኖረን በመቅደስ፣
ለዕምነታችን ተገዝተን፣
በነጭ ልብስ በመላዕክት
               ታጅበን፣
የድል ዜማ በዳዊት ዝማሬ
              እያመሰገንን፣
ምድራዊውን አለም እረስተን፣
ከሰማይ ከዋክብት በላይ
               አብርተን፣
ከፀሀይ ሰባት እጅ በላይ
     ብርሀን ከሆነው ቤት ተገኝተን፣
በዕልልታ በሽብሸባ
        ምስጋናን እያቀረብን፣
ልባችን ሳይስት ለቃሉ
            ታማኝ ሆነን፣
ያብቃን ለዛን ጊዜ ለምህረት
          ለሰዓቱ፣
ያኑረን ከዕቅፉ በገነት
          በክብራዊ መንግስቱ።☺️


..............


ከማበዴ በፊት፤ኣንድ ቃል ልንገርሽ
ላንቺ ብዬ ኣይደለም፤ጨርቅ የምቀድልሽ
ስለተውሺኝ ብዬ
መራቅ መገፋቴን፤መቻል ስላቃተኝ
ፍቅርሽ እንደ ቅዘት፤ስለሚያቃትተኝ
ከምቀደው ልብሴ፤ከገላዬ ካለው
ትዝታሽ ብቻ ነው፤በውብ የተሳለው
ጠረንሽ ነው ያለ፤ከገላ ከጨርቄ
የሄድሽ ቀን ጣልኩት፤ሀፍረቴን ኣውልቄ
    ከማበዴ በፊት
ኣንድ ቃል ለናገር፤ፍቅርዬ ባንቺ ፊት
  ኡ ኡ ብዬ ብጮህ
እንዳትጠብቂ ከጬኀቴ መሀል
ከቶም ስምሽ የለም
የኔ ውድ የኔ ኣለም
ለኔ ኣይነቱ ኣፍቃሪ
እብደት ጤንነት ነው ከእስሩ መፈቻ
ኣንቺን አንቺን ብቻ
ማለቱን እረስቶ
ፍቅርን እንደጨርቅ፤ከገላው ለይቶ
     ከገረባው መሀል
ተግቶ ሊፈልጋት፤የጠፋችው ፍቅሩን
ቅጠሏ ኣመርቅኖ
ግንዷ የበከለ ሰማይና ምድሩን
    ቅጠሏ ፍቅር ነው፤ሙትን የሚባብል
ግንዷ ደሞ ግፍሽ፤በቁም የሚገድል
  ለዚህ ይሆን ? እብድ ሁሉ
ገረባ የሚያነሳ፤ገረባ የሚጥለው
የጠፋችው ፍቅሩን፤ስለምትመስለው
       እናም ፍቅርዬ
    ላብድ ስለሆነ እንዳትጸጸቺ
ኣንቺን ፍለጋ ነው፤የማበዴ ፍቺ
ከሰው መሀል ባጣሽ፤ካትሮንስ ባትገኚ
ኣብጄ ፈለኩሽ፤ገረባ ስትሆኚ


      


…….ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት..የሆነ ስህተት ፈጥራ እግሯ አዳልጦት ከመወጣጫው ላይ ተንሸራታ ብትፈጠፈጥ ሁሉ ነገር እንደሚያበቃለትና የአሰበችውን አንዱንም ሳታሳካ እግረ ሰባራና አካለ ጎዶሎ ሆና ለሌላ ስቃይ እደምትዳረግ አሰበችና ዝግንን አላት…በአእምሮዋ የተፈጠረው ክፉ ሀሳብ እዳይፈጠር እየጸለየች..በጥንቃቄ ወደታች መውረዷን ተያያዘችው…ምንም እንኳን ያን የአደጋ ጊዜ ጠባብ መወጣጫ ተጠቅሞ ወደታች መውረድ ሊወስድ ከሚገባው የጊዜ ስሌት በላይ የወሰደባት ቢሆንም ግን ደግሞ ምንም ክፉ ነገር ሳይከሰትባት ሻንጣዋን እንዳዘለች መውረድ ቻለች…ከዛ በግቢው ውስጥ ባሉ የጽድ ዛፎች እየተከለለች፣ከጀርባ ወደሚገኘው ገራዥ አመራች..የአባቷ ታናሽ ወንድም አልፎ አልፎ የሚጠቀምባት ሞተር ሳይክል ወደ ቆመበት ስፍራ አመራችና ቀድማ ሄልሜቱን አንስታ ጭንቅላቷ ላይ ከሰካች በኃላ መተሩን አስነስታ ቀጥታ ወደመውጫው በራፍ አስፈነጠረች፡፡…ወጪ ገቢ ስላለ የውጪ በራፍ አንደኛው ተካፋች ወለል ብሎ እንደተከፈተ ነው፡፡
ዘበኛው ሞተሩን ቢያውቃትም ማን እየነዳት እንደሆነ መለየት አቅቶት ላስቁም ወይስ ልፍቀድ…? በሚል ግራ መጋባት ውስጥ ሳለ ምንም እንዲል እድል ሳትሰጠው አስፈንጥራ የግቢውን ድንበር ጥሳ ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች፡፡ ዘበኛው የፈለገ ቢገምት የቤቱ ቅምጥል ልጅ ትሆናለች ብሎ ሊገምት እንደማይችል እርግጠኛ ነች…ዘበኛው ሞተርም እንደምትነዳ እንኳን አያውቅም

ይቀጥላል .....

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
https://t.me/manbabemulusewyaderegal
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.