በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ከሀምሳ በላይ ቤቶች ለኮሪደር ልማት ተብሎ ፈረሰብን ያሉ ዜጎች ሜዳ ላይ ቀርተናል አሉ
(መሠረት ሚድያ)- በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ ጌራ ወረዳ 'ከሚሴ' በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ 'ለኮሪደር ልማት' በሚል ከሀምሳ በላይ ቤቶች ፈረሰብን ያሉ ዜጎች ሜዳ ላይ ቀርተናል አሉ።
ለመሠረት ሚድያ ቃላቸውን የሰጡ እነዚህ ዜጎች እጅግ አነስተኛ በሆነችው እና ያላት የቤቶች ቁጥር ራሱ በጣም ውስን በሆነባት ከተማ ይህን ያህል ቤት በልማት ስም መፍረሱን ኮንነው ህዝብ የሆንነውን ይወቅልን ብለዋል።
"የወረዳው አስተዳደሮች ያለ ምንም ካሳ ክፍያ የግለሰብ ቤቶችን እያፈረሱ ነው። የሚሰማን አጥተን እየተሰቃየን ነው" ያሉት እነዚህ ዜጎች በዚህ ክረምት ሜዳ ላይ ቀርተናል ብለዋል።
በስፍራው ቤቶችን ማፍረስ ከተጀመረ አንድ ሳምንት የሞላው እንደሆነ የታወቀ ሲሆን እስካሁን ከሀምሳ ቤቶች በላይ ፈርሰዋል፣ ከዚህ ውስጥ 27 ቤቶች አነስተኛ ሱቆች እና የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ነበሩ ተብሏል።
"እኛ የትንሽ ከተማ ነዋሪዎች ስለሆንን ብንጮህም ብዙ አይሰማልንም፣ ድምፅ ሁኑን" ያሉት እነዚህ ዜጎች በተለይ ካለ ምንም ካሳ ህይወታቸውን ይመሩባቸው የነበሩ ቤቶች በድንገት መፍረሳቸው ድንጋጤ ላይ እንደጣላቸው ተናግረዋል።
የጅማ ዞን አስተዳደርን በጉዳዩ ዙርያ መረጃ ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ያለውን የኮሪደር ልማት ተከትሎ በርካታ የክልል ከተሞች እና መንደሮች ጭምር የ 'ኮሪደር ልማት' ስራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል።
ከዚህ ልማት ጋር ተያይዞ በርካቶች የመኖርያ፣ የስራ፣ የትምህርት እንዲሁም የሀይማኖት ስፍራዎቻቸው እንዲፈርሱ እንደተደረጉ ሲገልፁ ይሰማል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia