"በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነባችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም እንዳለባችሁ እንድታውቁት ለማሳሰብ እንወዳለን"- የፖለቲካ ፓርቲዎች
(መሠረት ሚድያ)- መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ "አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም" በሚል ባወጡት የጋራ መግለጫ በኮሪደር ልማት ዙርያ ተቃውሞ እና ትችታቸውን አጋርተዋል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አኹን ላይ የኮሪደር ልማት በሚል መጠኑንና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው ሥራ አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺህዎችን ሕይወት እያመሰቃቀለ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ በድንገት ቤታቸው የፈረሰባቸውና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ሕመም የተዳረጉ፣ ከለመዱት ማኅበራዊ መሠረት የተናጠቡ፣ ሥራቸው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠና ለከፋ ችግር የተዳረጉ፣ ቍጥሩ በውል ያልታወቀ በድንጋጤም የሞቱ እንዳሉ ለመረዳት ችለናል ብለዋል፡፡
"ከዋና ባለቤቶች/ባለይዞታዎች ባልትናነሰ ተከራዮች ከፍ ላለ ስቃይ እንደተዳረጉ፣ አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ታዝበናል፡፡ ይዋል ይደር እንጂ ይህ የሕይወት መመሰቃቀል የማይነካው የከተማዋ ነዋሪ እንደማይኖር ለመገመት ነቢይ መሆን አይጠይቅም" ያሉት ፓርቲዎቹ የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ የከተማዋን ነዋሪ በማፈናቀልና በአንድ ጀምበር ኑሮውን ወደ ሲዖልነት መለወጥ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አለፍ ሲልም ሀገር የምትተዳደርበትን ህግ በመሠረታዊነት የጣሰና ይጠብቀው ዘንድ ሓላፊነቱን በተቀበለ መንግሥት እየተፈጸመ የሚገኝ ከፍተኛ ወንጀል ነው ብለዋል።
ፓርቲዎቹ አክለውም መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ ከሚያናጋ በልማት ሽፋን የሚተገበር ደባ እንዲያቆም፤ የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር፤ ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የነበሩበትን ቦታ ካርታና መሰል የነዋሪነት/ባለ ይዞታነት/ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡ እንዲሁም አዲስ በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነባችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም እንዳለባችሁ እንድታውቁት ለማሳሰብ እንወዳለን ብለዋል።
መሠረት ሚድያ!
@MeseretMedia