ሚዛን ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ በሦስት ዙር ቴክኖሎጂ ነክ በሆኑ ኮርሶች ያሰለጠናቸውን 127 ተማሪዎች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በዌብ ዲቨሎፕመንት፣ በሞባይል አፕ ዲቨሎፕመንት፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ በቤዚክ ኮምፒውተር ስኪል እና በዳታ ሳይንስ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
ተማሪዎቹም በመደበኛ፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት በአካል እና በኦንላይን ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የኢንስቲትዩቱ ሥራ አስኪያጅ አህመድ ሙሀመድ ገልፀዋል።
በ2014 ዓ.ም የተቋቋመው ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ከ300 በላይ ተማሪዎችን ከ 2-9 ወር በሚሰጡ ኮርሶች በሰባት ዙር ማስመረቁን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
https://t.me/minster_of_education