የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ፤ አስመራ በህወሓት እና በትግራይ ክልል "ጊዜያዊ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ግጭት" ውስጥ "ምንም አይነት ሚና" እንደሌላት ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ "የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር" ግፊት እንዲደረግባት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጥያቄ አቅርበዋል።
ኦስማን ይህንን የተናገሩት ማክሰኞ፣መጋቢት 9/2017 ዓ.ም. መቀመጫቸውን አስመራ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እንደሆነ የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል።
ማክሰኞ ጠዋት በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ማብራሪያ የተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፤ "አምባሳደሮች" እና "የዲፕሎማቲክ ኮር አባላት" እንዲሁም በሀገሪቱ "እውቅና የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት ተቋማት አመራሮች" መሆናቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው አሰፋ እና በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የከረረ ውጥረት ተፈጥሯል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሳምንት አንደኛው የህወሓት ክንፍ የአገሪቱ ተቀናቃኝ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እና ትብብር አለው በማለት መውቀሱ አይዘነጋም።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ማብራሪያ፤ ሶስት ጉዳዮችን በዋናነት ማንሳታቸውን የማነ ተናግረዋል።
የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጉዳዮች በኤርትራ ላይ የቀረቡ "ሀሰተኛ ክሶችን" የሚመለከቱ እንደሆኑ በማስታወቂያ ሚኒስትሩ መረጃ ላይ ሰፍሯል።
በቀዳሚነት የተጠቀሰው "ኤርትራ በኢትዮጵያ ጦርነት ለመክፈት እያደረገች" ነው ስለሚለው "ግምታዊ" ክስ ነው።
ሁለተኛው ክስ የፕሪቶሪያ ስምምነትን የተመለከተ እንደሆነ ተገልጿል።
ማብራሪያ ተሰጥቶበታል የተባለው ሶስተኛው ጉዳይ ደግሞ፤ "የኢትዮጵያ የባህር በር [የማግኘት] አባዜ" እንዲሁም "ይህንን ተከተሎ" የመጣው "ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ" እና "አብሮት ያለው" ተንኳሽ ድርጊት እንደሆነ ተጠቅሷል።
የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ይህንን ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጤሞቲዮስ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመሆን በተመሳሳይ አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ከሰጡ ከቀናት በኋላ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን እና ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም. የሰጡት ማብራሪያ በትግራይ ክልል በህወሓት አመራሮች መካከል ከተፈጠረው ቀውስ ጋር የተገናኘ ነበር።
ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ፋኖ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ረቡዕ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
ትዊተር: x.com/nisirinternati1
ዩቱብ: https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=_LD-OmtO1nJ0RVr2
ቴሌግራም: https://t.me/nisirbroadcasting
ቲክታክ:- tiktok.com/@nisirbroadcas…
ዌብሳይት : nisirbroadcasting.com
WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084pp