«ሁሉንም አዎን አዎን ትያለሽ ማናቸው ነው ?»አላት።
«እንግዳ ወንድ መጥቶብሽ አልክኝ ከዚህ ዓለም ልዩ የሚሆን ጌታ መጥቷል። ፍቅር ያላለቀለት ወንድ መጥቶብሻል ላልክኝ ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት እንዲል። የሰው ፍቅር አገብሮት ሊሞት መጥቷል። በጥቂት ገንዘብ ብዙ ገንዘብ የሚሸጥ ባለጸጋ ነጋዴ መጥቶብሻል ላልከኝ አዎን በጥቂት ትሩፋት ብዙ ክብር የሚሰጥ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥተልና ለእሱ የምቀባው ሽቱ ልገዛ እሄዳለሁ» ብላ ስሙን ብትጠራበት እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ ጠፍቶላታል።
ከዚህ በኋላ ሃድኖክ የሚባል ባለ ጸጋ ነጋዴ አለ ሄዳ
«ለነገሥታት የሚገባ ሽቱ አምጣ» ብላ ሦስት መቶ ወርቅ ሰጠችው በሀገራቸው ሐሰት የለምና «ይህን ያህልስ የሚያወጣ የለኝም» አላት እሱ የማያውቀው እናቱ የምታውቀው ዳዊት ሰሎሞን ተቀብተውለት የተረፈ «ዕፍረተ ናርዱ» ነበር ከእንዲህ ያለ ቦታ አለ ሽጥላት ብላው ሽጦላት አምጥታ ቀብታዋለች። ይህ ብቻም አይደል ጌታ ግብፅ ሲወርድ ሰሎሜም ፈያታይ ዘየማን ይዘውት ሳለ ከልብሱ ላይ ወዛ ቢያጽቡት ሰፈፈ ይህን በዕቃ አኑረውታል ይህም ተጨምሮበታል።
ናርዶስ ባለመልካም መዐዛ ቅባት ብቻ ሳይሆን በብዙ መንገድ ፍቱን መድኃኒት ጭምር ነው። መድኃኒትነቱንም ከልማዳዊ የባህል ሕክሞና ዘርፍ አንስቶ በአያሌ ጥናት በተደገፉ የዘመናችን ሳይንሳዊ የሕክምና ምርምር ጭምር የተመሰከረለት ነው።
በእርግጥ የዓለም የጤና ድርጅት እንዳረጋገጠው 80እጅ የሚሆነው የምድራችን ነዋሪ ባህላዊ ህክምናን ለጤናው መጠበቅ ምርጫው ያደርጋል [About 80% of the world population totally depends on traditional medicine systems for their primary health care needs]
በቀደመው ልማዳዊ / ባህላዊ ህክምና ጥናት (Ethnomedical research) ሚናው ላቅ ያለው የናርድ ተክል በዘርፈ ብዙ ጥቅሙ ለረቀቀው የሳይንስ ጥናት Scientific ethnomedical studies እንደመነሻ ሆኖ በብዙ ጥናት የተደገፈ የጤና ችግሮች ማቅለያ በመሆን ለነገረ ሰብእና ለመድኃኒቶች ግኝት ጥናት እገዛው ከፍ ያለ ነው።
በሳይንሳዊ ስሙ Nardostachys jatamansi [ዕፀ ናርድ ☞ የናርዶስ ተክል] ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ በህክምናው ረገድ ✧ሥሩ (Root) ✧የሥሩ ግንድ (Rhizome) ✧ግንዱ (Stem) ✧ቅጠሉ (Leaves) ✧አበባው (Flower) እና ✧መላ ተክሉ (Whole plant) እየተቀመመ ከጭንቀት የአእምሮ ሕመም እስከ ነቀርሳ (ካንሰር) ድረስ በመድኃኒትነት በብዙ ዘርፍ ያገለግላል።
በክኒን (Tablet) በሽሮፕ (Syrup) በሚዋጥ ባለሽፋን እንክብል (Capsule ) በቅባት (Oil ) በዱቄት (Powder ) እንዲሁም በሌሎች መንገዶች (Granules & Paste) መንገድ እየተዘጋጀ በዘመናዊ ሕክምናውም ረገድ ለዘርፈ ብዙ ጤና መታወክ መፍትሄ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
አፈወርቅ በድርሳኑ ፬ኛ ክፍል የጠቀሰውን መነሻ ያደረግነውን መድረሻ አድርገን እናብቃ
«እስመ እግዚኣብሔር ይትባረክ ስሙ ሰመየ ሕማማተ ወልዱ ክብረ ወስብሓተ እስመ ተሠግዎቱ ለወልድ ወሕማማቲሁ በእንተ ፍቅረ ሰብእ የዓቢ ወይፈደፍድ እምተፈጥሮተ ዓለም ወአምጽኦቱ እምኀበ ኢሀልዎ ውስተ ሀልዎ»
☞ ስሙ ይክበር ይመስገንና እግዚአብሔር የልጁን ሕማምና ሞት ክብር ምስጋና ብሎ ጠራው ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ብሎ ሰው መሆኑና መከራ መቀበሉ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ከመፍጠሩ በእጅጉ ይበልጣል!
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በምክንያት ሲያስረዳ
«ፍጥረተ ዓለም ይኤምር ኀበ አፍቅሮቱ ሰብአ አላ ሕማማቲሁ ባሕቱ ይከብር ፈድፋደ። ☞ ዓለሙን መፍጠሩ ሰውን መውደዱን ያስረዳል። የሕማሙ ነገር ግን እጅጉን ልቆ የከበረ ነው»
በምን አበላልጦት እንዲህ ይላል ቢሉ
☞ ዓለሙን በመፍጠሩ አልደከመበትም፤ በማዳኑ ደክሞበታልና። ☞ ዓለሙን በመፍጠሩ አላዳነበትም መከራ በመቀበሉ
☞ አድኖበታልና። ሲፈጥር ያየው የለም፤ መከራ ሲቀበል ሁሉ እያየው ነው፤
ማኅየዊትና መድኃኒት በምትሆን ሕማሙ ጠረናችንን በመልካም መዓዛው ለውጦ ለቁስላችን መድኃኒት ለሞታችን ሕይወት የሆነን ክርስቶስ ከበረከተ ሕማማቱ አያጉድለን!
🌴 በቴዎድሮስ በለጠ ✍ ሕማማት ረቡዕ ምሽት ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
📍 የምድር ጌጥ ደብረ ሊባኖስ