#የተቀደደ_መጽሐፍ
መጽሐፍት ሙሉ መልዕክት የሚኖራቸው ሙሉውን ክፍል እስካነበብን ድረስ ነው። የአንድን መጽሐፍ አንድ ገጽ መቅደድ የመልዕክቱን ሙሉነት ያሳንሰዋል። ብዙ መጽሐፍ ማንበብ የሚወዱ ሰዎች መጽሐፍ ሲቀደድ ሲያዩ የመታገስ ጽዋቸው ሞልቶ ለቁጣ ይጋበዛሉ። ያነበብቱ በዚህ ልክ ከተሰማቸው የመጽሐፉ ጸሓፊ ደግሞ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም። አንዳንድ ጸሓፊዎች መጽሐፋቸውን ልጄ ብለው በመጥራት ለልጃቸው የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ሁሉ ለመጽሐፋቸው ሲያደርጉ ይስተዋላሉ።
እግዚአብሔር ቃሉ እንዲጻፍ ለምን የፈለገ ይመስላችኋል? ሳይጻፍ ቀርቶ በንግርት ወይም ከሰዎች ምላስ ላይ እንዲደመጥ አድርጎስ ቢሆን? እንዲ ቢሆን ኖሮ በዚህ ዘመን የምንሰማው ቃል ጥቂት የእግዚአብሔር ይሆንና እልፍ የሰዎች ይሆናል። የተወሰኑ 20 ሰዎችን ደርድረን ለመጀመሪያው ረዘም ያለ መልዕክት ነግረነው ለሁለተኛው እንዲነግረው ሁለተኛውም ለሶስተኛው..... 20ኛው ሰው እስኪ የሰማኸውን ንገረን ብንለው ከዋናው መልዕክት በጣም ጥቂት ቃላት ከ19ኙ ሰዎች ብዙ ስህተት የሆነ ቃላትን ገጣጥሞ ይነግረናል።
በንግርት የሚያልፍ መልዕክት አይደለም ከትውልድ ወደ ትውልድ በሙሉነቱ ሊሸጋገር ቀርቶ በአንድ ትውልድ ውስጥ ባሉ ሰዎች እንኳን በትክክል ለመተላለፍ ይቸገራል። የእግዚአብሔር ቃሉ በንግርት የተቀመጠ ቢሆን ነገስታት ያራቸውን ክብር ለመጨመር ቃሉ ላይ በጨመሩ ነበር፣ ተናጋሪዎቹ የሰሙትን እንደሚረዱት መጠን ባስተላለፉት ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል መጻፍ ዋና ጉዳይ መልዕክቱ ትክክለኛነቱን እንደጠበቀ ዘመናትን እንዲሻገር ነው።
ይኸው ስለተጻፈ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች በዛ ዘመን የተሰበከውን የእውነት ቃል ለማንበብ እና በቅዱሱ መንፈስ አማካኝነት ደግሞ ለመረዳት በቅተናል። እረ እንኳንም ተጻፈ። የመልዕክቱ ርዕስ የተቀደደ መጽሐፍ ስለሚል ከርዕሴ እንዳልወጣ ስለመጻፉ አስፈላጊነት ብዙ አልበል። ብዙ ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል በመቅደድ ተግባር ላይ ናቸው። መርጠው ይሰማሉ፣ ከፍለው ያነባሉ፣ ቆንጽለው ይረዳሉ፣ የተመቻቸውን ክፍል ብቻ ልክ ይላሉ፣ እንደልባቸው ይተረጉማሉ ይሄ ነው መጽሐፉን መቅደድ የሚባለው።
አሁን አሁንማ ከሰዎችም አልፎ ተርፎ ቤተ እምነቶችም ለራሳቸው አስተምህሮ እንዲመች አድርገው መጽሐፉን ይቀዳሉ ግሪኩ እንዲ ይላል በማለት የራሳቸውን ያስቀምጣሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የዕብራስጥ እና የግሪክ ቋንቋ እንደሆነ መረዳት ያሻል። መጽሐፉ ልክ ሲጻፍ እንዲ ይላል ብሎ ሌላ መጽሐፍ መጽሐፉን መቅደድ ካልተባለ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።
ከመሃል መርጠን የተረዳነውን ቃል እስኪ ከነሙሉ መልዕክቱ ለመረዳት ልባችንን ክፍት እናድርግ ያኔ የቀደድናቸው ክፍሎች ይታዩናል። አንድ ጸሓፊ የጻፈው መጽሐፍ ሲቀደድበት ማያትን ካልፈለገ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር መጽሐፉ ሲቀደድ ምን ይሰማው ይሆን? የእግዚአብሔር ከሆነው ነገር ከመጉደል በላይ መጉደል ወዴት አለ? የእግዚአብሔርን ሃሳብ በሙሉነቱ ካልመረዳት በላይ መጎዳትስ ከዬት ይገኛል?
ስለእግዚአብሔር ቃል ያለን መረዳት ስለዘላለማችን ይወስናልና መረዳታችን በተገቢው መልኩ መፈተሽ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሆኖ የማይገባን ነገር እንዳይኖር መትጋት በጣም አስፈላጊ ነው። የእግዚአብሔር የልቡ ሃሳብ ያለው የትም አይደለም ቅዱሱ መጽሐፍ ላይ ነው። ከዚህ ክፍል አንዱን ገጽ መቅደድ በእግዚአብሔር በልቡ ሃሳብ ላይ ማሾፍ ነው። እናማ አትቅደዱ አንቅደድ። በተቻለን ሁሉ ከዚህ ቃል የማይገባን እንዳይኖር እግዚአብሔር መረዳታችንን እንዲረዳው መጸለይ እና ቃሉን ማንበብ የሁል ጊዜ ስራችን ይሁን።
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
@orthodox_new_mezmur