ናሁ ሰማን(Nahu seman) dan repost
እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት፡ እርሱም ክርስቶስ፡ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
(ሉቃ. 2፡10)
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳይሁ!!!
☦በእንተ ነገረ ልደት በአፈ አበው ሲገለፅ☦
ክርስቶስ ከእለት ከሰዐት አስቀድሞ የነበረ ቀዳማዊ ሲሆን የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ፤ ሰው ሆይ ስጋ ያልነበረው እርሱ ለአንተ ብሎ ስጋን ተዋሀደ፤ ሰው ሆይ በመለኮቱ የማይዳሰስ የነበረ አምላክ ለአንተ ብሎ ተዳሰሰ ፤በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍፁም ስጋ ተዋሀደ፤ አይታይ የነበረ እርሱ የሚታይ ስጋን ተዋሃደ፤ የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ስጋ ተዳሰሰ የማይለወጥም አደረገው፤ ባዕል የሆነ እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች ድንግል ማህፀን አደረ ፤ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፤ የነገስታት ንጉስ የሆነ እርሱ በበረት ተኛ
☦ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አስጢፎስ ☦
ከሶስቱ አካል አንዱ አካል በእመቤታችን በንፅሕት ድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ ፤ ስለ መለኮት ተዋህዶ በዚህ የምንናገረው በወልድ ያለውን ነው ፡፡ ስለ አብ ስለ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ፈፅሞ አብ መንፈስ ቅዱስ ሰው ለመሆን በድንግል ማኅፀን አደሩ አንልም ፡፡
☦ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ☦
ሰዎች መለኮትን ያዩት ዘንድ የበቁ እሰኪሆኑ ድረስ በሰው ባሕርይ ተገለጠ በስጋ ዘመዳችን ሆኖ ባየነው ጊዜ በአብ ቸርነት የወልድን ጌትነት እናመስግናለን