" ገንዘቡን፣ ሃይማኖቱንና ነፍሱን አጣ"
በእጁ ያቆረባቸውን ልጆቹን በሰይፍ የገደለው ፎላ እና ፍጻሜው
ሰማዕቷ ቅድስት ጤቅላ፡- ጤቅላ ማለት ‹‹ልጅ፣ ለግላጋ›› ማለት ነው፡፡ ቅድስት ጤቅላና ከእርሷ ጋር የነበሩ አራት ደናግል ጥር 30 ቀን ፎላ በሚባል ኃጥእ ቄስ እጅ ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ፡፡ ይህም ፎላ የተባለ ቄስ በአመጽ የሰበሰበው ብዙ ገንዘብ እንዳለው በከሃዲው መኰንን ዘንድ ነገሩበት፡፡ ስለዚህም መኮንኑ ገንዘቡን ሁሉ እንዲወርሱ አዘዘ፡፡ ፎላም ወደ መኰንኑ ዘንድ በመሄድ ገንዘቡን ይመልስለት ዘንድ ቢለምነው እምቢ አለው፡፡ ከሃዲው መኰንንም ስለ እነቅድስት ጤቅላ የምግባር የሃይማኖታቸውን ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘና አስመጣቸው፡፡ ጌታችንን አስክዶ እምነታቸው አውጥቶ ለጣዖት እንዲገዙ ግድ አላቸው፡፡ እነርሱ ግን በእምነታቸው በጸኑ ጊዜ መኰንኑ ፎላንን ጠርቶ ‹‹እነዚህ ደናግል ለፀሐይ ይሰግዱ ዘንድ እነርሱን ብትሸግልልኝ ገንዘብህን መልሼ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላንም እነ ቅድስት ጤቅላን ይሸነግላቸው ጀመረ፡፡ ደናግሉም ‹‹አንተ የሰይጣን ልጅ የክብር ባለቤት ክርስቶስን እንክደው ዘንድ እንዴት ትፈትነናለህ? አንተ ቀድሞ መምህራችን የነበርክ ስትሆን›› ብለው ዘለፉት፡፡
መኰንኑም ይህን ቃላቸውን ከአንደበታቸው በሰማ ጊዜ በጅራፍ ጽኑ ግርፋትን አስገረፋቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳት ደናግል ግን ስለ ጌታችን ይመሰክሩ ነበር እንጂ ምንም አልፈሩም ነበር፡፡ መኰንኑም ፎላንን ‹‹የበከተ ብትበላ ደምንም ብትጠጣ ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› ባለው ጊዜ እንዳለው አደረገ፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነዚህን ደናግል ብትገድላቸው ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላም ይህን በሰማ ጊዜ እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ ልቡ በገንዘብ ፍቅር ተነድፏልና ልቡናውን አጽንቶ ቅዱሳት ደናግሉን ሊገድላቸው ሄደ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉት፡- ‹‹ከሃዲ ሆይ የመድኃኒታችንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በእጅህ ታቀብለን አልነበረምን? ስለ ገንዘብ ፍቅር ብለህ እኛን የክርስቶስን በጎች ልታርድ መጣህን?›› እያሉ በገሠጹት ጊዜ ሰልፍ እንደተማረ አርበኛ ሰው ሆኖ በሰይፍ ራስ ራሶቻቸውን ቆረጣቸው፡፡ መኰንኑም የፎላንን ብላሽነትና ድንቁርናውን አይቶ ወዲያው በሰይፍ ገደለው፡፡ ፎላም ገንዘቡን፣ ሃይማኖቱንና ነፍሱን አጣ፡፡ የእነዚህም ቅዱሳት ደናግል ስማቸው መሪ የሆነቻቸው ጤቅላ፣ ማርያ፣ ማርታ፣ አመታ፣ አበያ ሲሆን ጥር 30 ቀን ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!ስንክሳር ዘጥር 30