Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


#በባንዳነት በትልቁ የተመዘገቡት ደጃዝማች ጉግሳ ኃይለሥላሴ እና ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት

frim Ethiopian hisory and tourism

መዝግብ
ለሀገር እጥፊ ቡድን በዘመቻ እና በዝምታ የተሰለፋችሁ
ከምዕመን እስከ ሀይማኖት መሪ፤
ከሚሊሻ እስከ ጦር አዝማች፤
ትውልድ እና ታሪክ በዚህ መልኩ ይዘክራችኋል


የቀጠለ👆👇
ጊዜው አልረፈደም እንዲስተካከል እንጠይቃለን። ካልተስተካከለ የእርስ በእርስ የአገልጋዮች ዕልቂት እንደሚፈጠር አስረግጨ መናገር እፈልጋለሁ። የአጥማቂው ጀሌዎች ሐሳብና ዕውቀት የሌላቸው መሆኑን ስንቶችን የአካል ጉዳተኛ እንዳደረጉ ሕይወት እንዳጠፉ የሚያውቅ ያውቀዋል። ዛሬም ያንን ሲደግሙትና አጥቢዎችን በጉልበት ሲወሩት ዝም የምንልበት ምክንያት አይኖርም።
እነ መምህር ገብረ መድኅን ዋጋ ከፍለው ሰጥ ያሰኙትንና ከምዕራብ ጎጃምና ከሌሎች ሀገረ ስብከቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያደረጉትን ጉድ እናንተ በማን አለብኝነት ነፍስ ስትዘሩባቸው ማንም ዝም አይልም። ጦርነት ላይ ላለ ሕዝብ ሌላ ጦርነት አንፈልግም። ግን አይ ካላቸው አሁን ድሮ አይደለምና ዋጋ ትከፍላላችሁ።
ማኅበረ በኩራት ማለት የሐሳዊ መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች ቡድን ነው።

ይድረስ
ለባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ሥራ አስኪያጅ
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል
  ቤተ ክርስትያን ስትወረር ቁመን አናይም


እስከዛሬ ድረስ ለዓመታት ዋጋ እየከፈልሁ ያለሁት በአጥማቂው ዮሐንስ ምክንያት ነው። ከምወደው መሥሪያ ቤትም የተፈናቀልሁት በእሱ ጀሌዎች እንግርግሪያ ነው። ግን ባንተ ስሜት ልክ የሚጓዝ መሪ ከሌለህ ሁለመናህም ይወረስብሃል። ይኸው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ድረስ ወረሩን። የመጨረሻውን ጦርነት አድርገን ግልብጥ ብለን መጥተን ሀገረ ስብከት የምትሉትን እንበትነዋለን። ብፁዕ አአቡነ አብርሃም ሆይ ከእርስዎ ጋር ስለ አጥማቂያን ገመና ከማስረጃ ጀምሮ አውርተን ነበርና እኔ በግሌ እንደሚያስተካከሉት ተስፋ ነበረኝ። ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ንዋዕያተ ቅድሳት ዝግጅትና ሽያጭ፣ ስለ አእምሯዊ ንብረት፣ አጠቅላይ መንፈሳዊ ሕትመቶች ማእከላዊ ሆነው እንዲታተሙና ሌሎች ጉዳዮችም ጭምር አውርተን በእርስዎ የሥራ አስኪያጅነት ዘመን እንደሚስተካከሉ ተስፋ ነበረኝ። ግን ብፁዕነትዎ የተለወጠ ነገር የለም ይባሱን ይኸው ሀገረ ስብከት ላይ ሃይማኖተኛ መሳይ ከሃይማኖቱ መንገድ ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ጎረምሶች ዕውቅና ሰጥተው እሾህ እንዲተከል አመቻችተዋል ወይም በቀጥትታ ፈቅደዋል ወይም በዝምታ አልፈዋል።


ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official) dan repost
#በተለይ_ለኢትዮጵያውያን #የነፃ_ተሳፋሪነት_ጽንሰ_ሐሳብ #Free_Rider_Theory #የምንፈልገው_ሀገራዊ_ሁኔታ_ቁልፍ_ጉዳይ #በያሬድ_ኃይለመስቀልhttps://youtu.be/wfjZKbYHQG4?si=_5W_1Mb_CM1eSG5T


ቢዝነሳችሁ በመሠረተ ልማት ወይም በጦርነት የተቃወሰባችሁ

1) ካሳ የምታገኙ ከሆነ ሞክሩ፡፡ ግን እኛ ሀገር የሰነድ አደረጃጀታችን ለካሳ ስለማይመች ጊዜና ገንዘብ ባትፈጁ ይመከራል፡፡ የሚያሰጥም ከሆነ እንደ አንድ ጉዳይ ያዙት እንጂ ሕይወታችሁ እዚያ ላይ አይንጠልጠል፡፡ ባይሆን ጉዳያችሁን ተደራጅታችሁ ለጠበቃ ስጡት

2) ፋይናንሻል ሪከቨሪ ላይ አተኩሩ

- መቋቋሚያ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ የልሆኑ ድርጅቶች፣ ወረዳዎች የሥራ ፈጠራ ተቋማትን ቅረቡ፡፡ ቀላል ብድር ፈልጉ
- ከአበዳሪዎቻችሁ ጋር ተደራደሩ፡፡ የቀድሞ ብድር ሠርታችሁ እንድትከፍሉዋቸው እንዲያግዙዋችሁ አድርጉ እንጂ አትራቁ፡፡ ስልክ ዘግቶ መጥፋት ለተጨማሪ ድብርት ይዳርጋል፡፡ ስል ጭንቅላት ይዶለዱማል፡፡
- ቀድሞ ሥራውን ስለምታውቁት በአጋር የሚያሠራችሁ ድርጅት ፈላልጉ፡፡ የሦስት ዓመት ውል ግቡ፡፡
- ከባንክ የተበደራችሁም ከባንኮች ጋር የብድር ሪስኬጁል እና አማራጮች ተነጋገሩ፡፡ የባንኮች የሐራጅ ማስፈራሪያ አትፍሩ፡፡ አንድ ባንክ ቢበዛ ሐራጅ የብድሩን 5% ብቻ ነው፡፡ በአብዛኛው NPL (Non performing loan) 3% አካባቢ ነው፡፡ ለራሳቸው ሲሉ ይተባበሯችኃል፡፡

3) ድጋሚ ሥራችሁን ጀምሩ
-ተመሳሳይ መረበሽ የማይገጥማችሁ ሰፈር ወይም ከተማ በመቀየር ያንኑ ሥራ ጀምሩት፡፡ ከመጀመራችሁ በፊት ቢያንስ ሦስት ቦታ ሂዱ፡፡ የመሬት ማኔጅመንት፣ ፕላን ኮሚሽንና የኮሪደር ልማት ጽሕፈት ቤት ጠይቁ
-የወትሮ ሥራ ለምትሄዱበት ሰፈር የማይገጥም ከሆነ ሪብራንድ አድርጉት፡፡ ስሙን ቀይሩት ለማለት ነው፡፡ ለሰፈሩ የሚመች ሐሳብ ለማፍለቅ መንደሩን በእግርም ሆነ በመኪና ዙሩት
-ከስተመር ቤዝ ቀይሩ፦ ወትሮ በጨረታ ወይም እግረ መንገዱን ለሚገዛ እየሸጣችሁ ነበር ይሆናል፡፡ አሁን ጨረታውም በመስመር ላይ (ኦንላይን) ሆኗል፡፡ የሶሻል ሚድያ የሽያጭ አማራጮች ጥሩ ናቸው፡፡
-የጎንዮሽ የተለያዩ ቢዝነስ አማትሩ
-ባልና ሚስት ብቻ ሳይሆን ልጆችም ከሶሻል ሚድያ scrolling ጋብ ብለው ይስሩ፡፡ በቴክኖሎጂ ያግዙዋችሁ፡፡
-ዕድሜያችሁ ገና ከሆነ ለተወሰነ ጊዜ ከሀገር ወጣ ብላችሁ ኑ

4) ሳይኮሎጂያዊ ዝግጅት
-በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሕይወቱን ያጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ አለን፡፡ እናንተ ግን በሕይወት አላችሁ፡፡ ብዙ የምትናገሩት ታሪክ አላችሁ፡፡ መከራ በዘነበ ማግስት ያለ ጥርጥር ጸደይ ይመጣል፡፡ ሱስ ግን በተቸገሩ ወቅት ይብስ ያስቸግራል፡፡ ይህ ምናልባትም ከሱስ መላቀቂያ ምቹ ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡
-የሃይማኖት መሪዎች ቢበላሹ እንኳ ቅዱሳት መጻሕፍቱ አሉ፡፡ ትጉና ጸልዩ፡፡
ምንጭ - ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን


❝...እሱ እንዳስተማረው ሳይኖሩ የተገኙት በእውነት ክርስቲያኖች እንዳልሆኑ ይረዱ ፤ ምንም እንኳን ትምህርቱ ከከንፈሮቻቸው ቢሆንም፣ የሚድኑት የሚያምኑ ብቻ ሳይሆን ሥራ የሚሰሩት ናቸውና❞
"በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ጌታ ሆይ፥ጌታ ሆይ፥የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።"
ሰማእቱ ቅዱስ ዮስጢኖስ st.justin martyr


©orthodox digital library

ንዋይ ካሳሁን


«የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የአርሶአደሩን እህል እየሰበሰቡ በመጫናቸው ሰበብ በማግስቱ በተቀሰቀሰ ውጊያ አንድ የ14 አመት ታዳጊ እና መነኩሴን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል!» -አዲስ ስታንዳርድ


ጅማ ላይ በአብይ አህመድ የተመራው ድብቅ ስብሰባ‼

ጥር 27/2017
ቢዛሞ ሚዲያ


     ኦርቶዶክሳውያን አስተማሪዎች እና አባቶች፦እንዲህ ቢሆኑ ጥሩ ነው።

ኦርቶዶክሳዊነትን ለማስቀጠል የክርስትና አደራን በሐዋርያዊነት ጠብቀው አስተምረው ለትውልድ የሚያቀብሉ አስተማሪዎች👇
=-ጥንቁቅ፣ጭምጥ፣ቁጥብ፣ሥውር፣ግልጽ የተራራ መቅረዝ መሆን አለባቸው።
=-በአርአያነት የሚያስተምሩ አባቶች፦ ለእግዚአብሔር መታመን፣ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ድኅነትንም ማመን፣ለሚያስተምሩት ምእመን በአባትነት መታመን መቻል አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦ግልጽ በሆነ የወንጌል ራዕይና የሐዋርያዊ አስተምህሮ ፍኖተ-ድኅነት መጓዝ መቻል አለባቸው።
=ኦርቶዶክሳውያን አስተማሪዎች፦

በተገለጸ ክርስቲያናዊ የወንጌል ዕቅድ እና ዘመኑን በተላበሰ የትኩረት አቅጣጫ ወንጌልን እያስተማሩ መመራት አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ቅን እና አገልጋይ መስቀል ተሸካሚ መሆን አለባቸው።
=ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦ በእግዚአብሔር አማኝ፣ሁል ጊዜ የሚማር ትምህርት መማርን ያላቆመ፣ወቅቱን ሁኔታውን የተረዳ፣እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰማህትነት ህሊናን የተላበሰ፣እንደ ሰሎሞን ፍርድን ያስተካከለ፣መሆን አለባቸው።
=-ኦርቶዶክሳዊ አስተማሪዎች፦
በምንም አይነት ምድራዊ ጥቅም የወንጌልን እውነት መባያ የማያደርጉ፣በመስቀሉ የማይቆምሩ፣ምላስ አስልተው የማይሸነግሉ፣የሚሉትን የሚያስተምሩትን የሚኖሩ፣አውግዠ እስክመጣ እየፈጨሽ ቆይኝ የማይሉ፣በዓለም ቢኖሩም የምናኔ ሕይወትን የተላበሱ፣እንደ ኤልያስ እንደ ዮሐንስ ለእውነት የሚኖሩ፣የአክዓብ የሄሮድስን ግርማውን ማማውን አይተው የማይፈሩ..መሆን አለባቸው።

-መንፈሳዊ አስተማሪዎች
ትምህርት፣ዕውቀት፣መረዳት፣ኅብረት፣ተግባር፣ተስፋ..ያላቸው የሐዋርያት ልጆችና ተከታዮች መሆን አለባቸው።
እንዲህ እንሆን ዘንድ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን።

ከምሠራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት ገጽ


ዋቄ ገጽ dan repost
በተለይ 5ኪሎ ተጎልታችሁ ክርስቲያን ማኅበርሰብ ሲፈርስ ስለ መሬት ካዳንች መርከብ፣ ስል ሕንጻ ምሠረት-ድንጋይ ማስቅምጥ ዜና እያስነገራችሁ፣ መንፈሳዊነት በራቀው እና ቱሪሰታዊ አብረቅራቂ በዓላት እያከብሩ ብርና ባዶ ዝና ብማጋበስ የተጠመዳችሁ፣ በዘረኛ ፖለቲካ ማኒፌስቶን በቀኖና ሐዋርያት እየትካችሁ ክህነት አልባ ካድሬ በማሰማራት ነፍሳትን የምታስግድሉና የምታደነዝዙ እረኞች መንቂያ ካላችሁ በዚህ ቪዲዮ የቀረበው መርጃ ትንሽ ዓይናችሁን ግለጡበት!!
===============
ዓይናችሁን ጭፍናችሁ ትግልን ከግብ የምታዝገዩ የአማራ ባንዳዎች፣ ለግል ሥልጣናችሁ ብላችሁ አንድንትን ያዝግያችሁ
👉 የፋኖ መሪዎቸ በተለይ --- እና ---- (ራሳችሁን ስለምታውቁ ስማችሁን ከመጥራት በመቆጠብ ለመስተካከል ጊዜ እንድታገኙ ትቼዋልሁ) ፣
👉 ጠባብ የአማራ ዳያስፖራዎች፣
👉 የተኛው የአዲስ አበባ ወጣቶች፣
👉 እረኝነታችሁን ለዘነጋችሁ ምንደኛ ጳጳሳት፣ የከተማ መነኮሳትና አሰትዳዳሪዎቸ ---- ራሳችሁን ለማረም ይህን መርጃ ስሙት፦ https://www.youtube.com/live/vwxAsTssX2c?feature=shared


በትኩረት አንብቡት

የአብይ አህመድና የኦህዴድ/የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ድብቅ ስብሰባ በጅማ

አብይ አህመድ በጅማ ከተማና አካባቢው የልማት ጉብኝት ባደረገበት ወቅት በተለያዩ ጊዜያት የኦሮሚያ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት የመሩትን ኦህዴዶችንና ጥቂት የኦሮሚያ ብልጽግና አመራሮችን በመያዝ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገዋል።

እነሱም

1 . ኩማ ደመቅሳ የቀድሞ የኦሮ/ክ/ር/መ/ር
2. ጁነዲን ሳዶ የቀድሞ ኦሮ/ክ/ር/መ/ር
3.አባ ዱላ ገመዳ የቀድሞ ኦሮ/ክ/ር/መ/ር
4.ሙክታር ከድር የቀድሞ ኦሮ/ር/መ/ር አሁን የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር
5.ሽመልስ አብዲሳ
6. አዳነች አቤቤ
7.ጫልቱ ሳኒ የከተማ ልማት ሚ/ር
8.ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የቀድሞ ፕሬዚዳንት
9.ግርማ ብሩ የብሄራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ እና የአብይ አማካሪ
10.ብርሃኑ ጁላ
11. ወርቅነህ ገበየሁ
12.ዶ/ር ግርማ አመንቴ ግብርና ሚ/ር

ከላይ በስም የተዘረዘሩት የኦሮሞ ባለስልጣናት በልማት ጉብኝት ስም በጅማ ከተማ ጥልቅ የሆነ እና ልዩ ግምገማዊ ስብሰባ አድርገዋል።
የስብሰባው አንኳር አጀንዳዎች ሁለት ነበሩ

1.ባለፉት ስድስት አመታት የሰራናቸው ስኬታማ ስራዎች ምንድን ናቸው ?
2.በቀጣይ አመትስ ምን መስራት ይጠበቅብናል ?

የሚል ሲሆን ከአማራ አኳያ ተከታዩ ነጥቦች ላይ ተነጋግረዋል ።


ያልተሰሙ_ድምጾች dan repost
የሻሸመኔ ሰማዕታት

"…አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።”ራእ 6፥ 9-10

በጥር 27/2015ዓ.ም በእነ ሳዊሮስ ፥ዜና ማርቆስና ኤዎስጤቴዎስ ትዕዛዝ ሰጭነት፥ በኦሮሚያ ልዪ ኀይል፥በኦሮሚያ ፖሊስ ፥በኦሮሚያ ሚሊሻ፥በአክራሪ  እስላም ወሀቢያ፥በጽንፈኛ  ጴንጤዎችና የዋቄፈታዎች ጥምረት በሻሸመኔ  ከተማ በግፍ ተጨፍጭፈው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

         በረከታቸው ይደርብን!


ዋቄ ገጽ dan repost
ይህን ሰሞን ስለ ዓለማወ ዘፈንና ሙዚቃ የሚወዛገዱ መምህራኖችን ተመልክቻለሁ።

እኔ የቀኖና ሊቅ አይደለሁም። ነገር ግን በሃይማኖት የማስብ ስለሚመስለኝ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ መስሎ ታየኝ።


ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን ሕይወቱ ስላደረገ ሰውና ማኅበረሰብ ስንነጋገር የሰሞኑን ፖለቲካና ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የሆኑ ድብቅ ፍላጎታችን በተቻለ መጠን ያልተቀላቀለበት ትምህርት መስጠት ምእመናንን በማሳሳት ምክንያት ከበጎቹ ጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ቅጣት ያድናል።
ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላይ የቅዳሴ የጸሎት ዜማን እስከነ ዓላማውና መንፈሳዊ ግቡ፥ ከእነ ጥልቅ ምሥጢሩ ተረድተን እንድናዜም ትፈልጋለች። ታስተምራለች፥ በተግባርና በህይወት ታሳያለች። በሂደቱ ሁሉ ህሊናችን፥ ዓይነ ልቦናችን እና መላው ተስፋችን ሁሉ ሰመያዊ ማንነታችንን አንጾ በመገኘት ላይ ታተኩራለች። ልጆቿም እንዲሁ በግልና በጋራ ድምፍ አውጥተው ወይንም በአርምሞ ሲያዜሙና ሲናገሩ ቅዳሱው ባመለከታቸው መሠረት ነፍሳቸውን ወደ ሰማዩ አባታቸው እንድታተኩር አድርገው ፈጣሪያቸውንና መድኀኒታቸውንን ክፍ ክፍ ማድረግና ማመስገን እንዲሆን እንደምታስተምር የቅዱሳን ሕይወት ሁሉ ይጠቁማል።
ቤተ ክርስቲያን በግልጽና በአትቃላይ ዓለማዊ/ሥዝም ዘፈንን ኣታወግዝም። በመጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠን ምልክት በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል፦
ሮሜ 13፡13-14 “በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን። ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም ይፈጽም ዘንድ ለሥጋ በዐሳባችሁ አትመቻቹለት። “
1 ጴጥሮስ 4:3 “አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣ ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል። “
ገላትያ 5:16-25፤ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። 17፤ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። 18፤ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። 19፤ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ 20፤ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ 21፤ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። 22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፣ 23፤ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። 24፤ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። 25፤ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክትና የቤተ ክርስቲያናችን የምንመለከተው ተግባራዊ ሕይወት የሚናበቡና የሚተረጓጞሙ መስለው ይታያሉ። የጠቀስናቸው ጥቅሶች በአንድ መሥመር ቢጠቃለሉ ገላ 5፥25 ይሆናሉ። እርሱም “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ፨“ የሚለው ይሆናል።
እንግዲ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በመንፈስ የመኖር አቅም እንዲያዳብሩ፥ ጎጂውንና ጠቃሚውን በራሳቸው እየለዩ አምላካቸውን እንዲያስደስቱ፥ የመንፈስ ቅዱስ ማኅደርበነታቸውን በሕይወት እንዲቀምሱ ታበረታታለች።
እንደ ኣይሁንና እንደ እስላም ወይንም እንደ ሌሎች ሰው ሠራሽ እምነቶችና ድርጅቶች ንካ-ኣትንካ፥ ቁም-ተቀመጥ እያለች በትምቀት በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ በጥምቀት ተካፍለው ዓለምን ሊዋጁ በውትድርና የተሠማሩ ልጆቿን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስት አልፈው እንዲኣድጉላት “በመንፈስ ኑሩ!” ብላ የገዳማውያንን ሕይወት እንደ ምሳሌ በተግባር እያሳየች በጎቿን ትመግባለች።
እንግዲህ ዘፈን ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለውን እሰታ ገባ ለሊቃውንት ጉባኤ ብያኔ ትቼ እኔ የበለጠ እስክማርና እስክረዳ አሁን እንደምረዳው ከሆነ ዘፈንን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንድንል ትፈልጋለች፦
1. የዘፈኑ ዓላማ ይዘት፦ ክርስቲያኖች ዘፈን ሲሰሙ (ሲዘፍኑ አላልኩም) የዘፈኑን ዓላማና ይዘትን በሚመለከት በክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ሚዛን ሊለኩ ይገባል። ይዘቱ ከመንፈሳዊ ዓላማ የሚያዘናጋ፥ ሥጋዊ ስሜት የሚቀሰቅስ፥ አሉታዊ ጠባይ እንድንለማመድ ምክንያት የሚሆን እና መንፈሳዊ ተመስጦን በሚያዳክም መንገድ በአእምሮ ምስለ-ዘማን (ፖርኖገራፊክ ምስሎች) የሚያትም እንዳይሆን አትብቃ እንደምታስጠነቅቅ ከአባቶቻችን ትንቃቄ እንማራለን።

2. በነፍስ ላይ የሚኣሳድረው ተጽእኖ፦ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተግባራዊ ሕይወት እንደምንረዳው ቅዳሴውና ማኅሌቱ ከይዘቱና አካል እንቅስቃሴ፥ ዝውውርና ሂደት ሁሉ የክርስቲያኖችን ነፍስ (ካህን በዓብይ ዜማ “ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርጉ” ሲል ምእመናን ደግሞ “ብግዚአብሔር ዘንድ አለን/ነን” ማለታቸው የማዜማችንን ዓላማ ያመለክታል። ዜማ/ሙዚቃ በነፍስ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚኣሳድር ከቤተ ክርስቲያን የበለጠ የሚረዳ ያለ አይመስለኝም። የቅዱስ ያሬድ ክግዚአብሔር የአገልግሎት፥ የውዳሴና የቅዳሴ ዜማ መቸሩ ይህንነኑ ተጽእኖ ያመለክታል። ከዚህ ተነስታ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ዓለማዊ ዜማና ዘፈንን ከእግዚአብሔር ጋር ከሚኖረን የቀና ግኑኝነትና ከመንፈሳዊ እድገታችን አንጻር እንድንመረምር ታስተምረናለች።

3. አቅመ-ማንጸር፦ ምእመናን ሙዚቃ ወይንም ዘፈን ለማዳመጥ የትኛው ለነፍስ የሚጠቅም ወይንም እንደሚጎዳ የማንጸር አቅም እንዲያዳብሩ ታበረታታለች እንጂ እንደዚህ እንደ ኣሁኑ ትውልድ በጭፍን መንጋነት ብዙኃን የወደዱትን መከተል፥ ዘመኑ ያገለለውን መጥላት፥ ማስታወቂያ ያገነነውን በጭፍን መጋትን እንድንጸየፍ ታሳየናለች። ማንጸሪያችን ዘፈኑ ከክርስትና እሤት፥ ዓላማና የመኖር ትርጉም ጋር ያለውን ግኑኝነት በመመዝን መሆን አለበት። ጥያቄውም ዘፈኑ ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ምስጋና የሚመራ ነው ወይስ ለመንሳዊነት እንቅፋት ነው? በሚል ማንጸር ያሻል።
4. ከመምህረ ንስሐ መመሪያ መቀበል፦ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ በተለያዩ መንፈሳዊ አቅም፥ በተለያዩ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ስለሚኖሩ አንድ አስገዳጅ ሕግና መመሪያ የሰጠቸን ኤእመስለኝም። በዚህ ምትክ ክርስቲያኖች በሚኣደርጉት ብቻ ሳይሆን በሚኣስቡትና ባቀዱት ጉዳይ ከንስሐ አባቶቻቸው ከካህን ጋር በመምከር ለነፍሳቸው የሚበጀውን መመሪያ መቀበል አንደሚገባቸው እንደምታስተምር ቤሌሎች የትዳርና የግል ሁኔታዎች ውስጥ ሁላችንም እናውቀዋለን። ለክርስቲያን “መዝናኛ” በሚል ዓለማዊ ስሜት ቀስቃሽ፥ ርኩሰትና ኃጢአትን የሚኣበረታታ የዘመኑን ዘፈን ከክርስትና መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፈጽሞ የማይስማማ በመሆኑ ከንስሐ አባት ጋር መምከርን ታዛለች።
ሲጠቃለል ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ዘፈንን ሁሉ ስታወግዝ አልመለከትም። ግልጽ ሆኖ የሚታየኝ ምእመናን ሙዚቃን/ዘፈንን በሚመለከት የመጀመሪያ ጥያቄያቸው “የምሰማው ወይንም የምዘፍነው ዘፈን ለመንፈሳዊ ሕይወቴ እድገትና ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ግኑኝነት ያሳድግልኛል ወይስ መንፈሳዊ ሕይወቴን ይጎዳል?” ብሎ በመጠየቅ፥ እንዲሁም ከመምህረ ንስሐ ጋር በመምከር መበየን ይኖርባቸዋል።


በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ ንፁሃን አርሶ አደሮች ተረሸኑ‼

የአብይ አህመድ የጥፋት እጆች በአማራ ህዝብ ላይ እየተባባሰ እና ከእለት እለት ንፁሃንን በተገኙበት በየቤታቸው መረሸን የዕለት ተግባሩ አድርጎ ተያይዞታል።

የአማራ አርሶ አደርን ማዳበሪያና ዘር ከልክሎ የአማራን አርሶ አደር ዘርቶ እንዳያመርት የተሴረበት አርሶ አደር ዛሬ ላይ ደግሞ በህይወት እንዳይኖር ዘርፈ ብዙ ጭፍጨፋዎችን እያደረሰበት ይገኛል። ይህ ፋሽስታዊ መንግሥት የአማራውን የመንቀሳቀስ መብት ገድቦና መንገድ ላይ መንግስታዊ ሽፍታ አሰማርቶ በጅምላ እያሳገተ አማራውን በማንነቱ እንዲሰቃይ እያደረገ ይገኛል።

የአማራን እናት ሆድ በሳንጃ በመቅደድ አማራ አይወለድም የተወለደውንም እናጠፋዋለን በማለት ወደ አማራ ምድር ዘልቆ የገባው ጨፍጫፊ ሰራዊት ዛሬም ንፁሃን አርሶ አደሮችን በተወለዱበት ቀዬ በዕለተ አርብ ከየቤታቸው እያወጣ ረሽኗቸዋል።

ቃሉን በተግባር እያሳየን የሚገኘው የብርሃኑ ጁላ ጨፍጫፊ ሰራዊት አሁንም አማራ የሆነን ፍጡር ሁሉ በአማራ ምድር ደም ማፍሰሱን ቀጥሎበት በ 23/05/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ ልዩ ሰሟ ገሸር በመባል የመምትጠራ ቦታ አስር ንፁሃንን ከቤታቸው እያወጡ ረሽነዋል።

ስርዓተ ቀብራቸው ስነ ትናንት በ24/05/2017 ዓ.ም በገሸር ማርያም ቤተክርስቲያን የተፈፀመ ሲሆን ከባህር ዳር ተጉዞ ለለቅሶ የመጣን የሟች ወገን በለቅሶው ቦታ ላይ መግደላቸው ታውቋል።

በዕለቱ ከተረሸኑት መካከል ለጊዜው ስማቸውን ማወቅ የተቻሉት።

1. ተመስገን አለሙ
2. ጥሩየ ፀጋ
3. ምስጌ ፈጠነ
4. በቃሉዘመነ

ከባድ ቁስለኞች
1. በላይ መንጌ
2. ምትኬ ጥሌ
3. ፀጋ ሞላ
4. አትርሰው ተፈራ
5. ሙሉነህ ፈጠነ


ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት dan repost
               ቅዱሳት መጻሕፍት፦
ሁሉም ሰው እንደ አቅሙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያነብ ይሆናል።ስናነባቸው በምን የመረዳት ደረጃ ውስጥ ሁነን ነው? ንዑስ መግቢያ የሚሆኑ መሠረተሀሳቦች ከዚህ ታች ተቀምጠዋል፦
[  ] ፩.በንባብ፣
[  ] ፪.በትርጉም፣
[  ] ፫.በአረዳድ፣
[  ] ፬.በምሥጢር፣
[  ] ፭.በሕይወት፣
[  ] ፮.በተስፋ..የከበሩ ናቸው።
በንባብ የከበሩ ናቸው፦ማለት ቃለ እግዚአብሔር ረቂቅ ሁኖ ሳለ በመጽሐፍ ከመጻፉ የተነሣ በዓይን የሚታይ በጆሮ የሚሰማ ሁኗል።ይህ ቅዱስ ቃል የሚነቡብ የሚታይ እንደመሆኑ መጠን የላይ የላዩ ንባብ ዘር ይባላል።
[  ] በትርጉም የከበሩ ናቸው ማለትም፦ ሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ትርጉም የሚያሻው እንደመሆኑ መጠን በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተቀመጠውን ሀሳበ እግዚአብሔር ለማወቅ የግድ ትርጉም ያስፈልጋል።እየተነበበ የሚተረጎም ቃለ እግዚአብሔር ዋና መሠረተ ሀሳቡ ሲተረጎም ለሰሚ ልቡና የተረዳ ይሆናል።
በአረዳድ የከበሩ ናቸው ማለትም፦ ተነበው እና ተተርጉመው ጥንተ መሠረቱን ሳይለቁ ፈቃደ እግዚአብሔርን የምንረዳባቸው ናቸው ማለት ነው።የቅዱሳት መጻሕፍት አረዳድ ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን ኅብረታዊ መሠረተ ሀሳብ ይዘው የሚቀጥሉ ናቸው እንጂ ዘመን አመጣሽ ሁነው መረዳት አይችሉም።
[  ] በምሥጢር የከበሩ ናቸው ማለትም፦የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና አረዳድ ለቅዱሳን የተገለጠውን ሃይማኖት እና የድኅነት ምሥጢርን መጠበቅና ለሰው ሁሉ መስጠት ሲችሉ ነው።የቀለም ሠረገለ መዳረሻው ወደ ትክክለኛ ምሥጢረ ድኅነት መሆን አለበት።
በሕይወት የከበሩ ናቸው ማለትም፦ተነበው፣ተተርጉመው፣ተረድተው፣ተመሥጥረው ሰውን ሁሉ በትክክለኛው የወንጌል ሕይወት ማኖር ይችላሉ ማለት ነው።የቅዱሳት መጻሕፍት ዓላማ ሰምቶ ለሚተገብራቸው ሁሉ ሕይወትን ማሰጠት ነውና።የሰማነው ያወቅነው ቃል በሕይወት ሲተረጎም የሚኖር ቃል ይሆናል እንጂ የሚነበብ ቃል ብቻ አይሆንምና።
[  ] በተስፋ የከበሩ ናቸው ማለትም፦በዚህ ዓለም የቅዱሳት መጻሕፍትን ሀሳብ ጠብቆ የኖረ ሰው ሁሉ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማግኘቱ አይቀሬ ነውና።ከሚታየው በኋላ፣ከሞት በኋላ፣ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ፣ የሚገኘውን ጸጋ ክብር ማግኘት የሚቻለው ዛሬ በቅዱሳት መጻሕፍት የተነገረውን ተስፋ ተረድቶ በመጠበቅ ላይ ጸንቶ በኖር ነውና።
ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናነብ ባጭሩ መታሰብ የሚገባቸው ቅደም ተከተሎች እነዚህ ናቸው።


ቢዛሞ ሚዲያ(Bizamo media) dan repost
አሳዛኝ ዜና
ከጅጋ ከፍኖተ ሰላም እና ከሆዳንሽ ተሰባስቦ ጅማት ቀበሌ የገባዉ የአብይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በጅማት ቀበሌ አሳዛኝ እና የነዉረኝነት ተግባሩን አሳይቷል በገባበት ቀበሌ ሰላማዊ 2 ሰወችን ገሎ 1 ሰዉ አቁስሎ ከነዚህ መሀል አንዷ የ13 ህፃን ስትሆን ቤታቸዉ የተዘረፉ ግለሰቦች ደግሞ
1 ብናልፈዉ ታሪኩ
2 ምኒችል ሙሉጌታ
3 ቀሬ መንገሻ
4 የሽዋስ በላይ
5 አያሌዉ
6 ቄስ ዘመኑ የተባሉትን አርሶ አደሮች ሙሉ ንብረታቸዉ
ተዘርፈዋል የቻሉትን ጭነዉ ወስደዋል ያልቻሉትን አቃጥለዋል ቤት የዘረፉት አለበቃቸዉ ብሎ የጅጋ ሻለቃን ክንድ መቋቋም ሲያቅተዉ በዲሽቃ እና በሞርተር
7 ክምር ጤፍ እና 2 ክምር በቆሎ ሰብል እና 5 በጎች 1 ላም እና 2 የእርሻ በሬወችን አቃጥሎ ወጧል
ለዚህ ነዉ (ሰራዊት ሳይሆን አራዊት ነዉ )ብለን እምንታገለዉ የአማራ ህዝብ በሂወት እንዲኖር ቀርቶ መሬቱ ያበቀለዉን ሰብል እንኳን አማራ መሬት ላይ የበቀለ ስለሆነ ያጠፋናል ብለዉ ስለሚያስቡ በዚህ መንገድ አዉድመዉታል

Kora Yehuala


የጉልበት ስራ ሰርቼ ይቺን ቀን ሳይርበኝ ባሳልፍ ብሎ በየመንገዱ የሚንከራተት የሀገሬ ወጣት እየታፈሰ የሚደርስበት የግፍ ፅዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው

@EliasMeseret


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የብልጽግናው ሥርዓት በዓለም ላይ ያሉ አሉታዊ ሪከርዶችን በመሰባበር ሀገራችንን ለዚህ ደረጃ..‼️‼️

በአለም ላይ ካሉ እጅግ ደካማ እና መጥፎ ስርአተ መንግስት በፅንፈኛው ጠባብ ጠ/ሚር  የምትመራው ኢትዮጵያ ስርአተ መንግስት መሆኑ አሁን አለም አውቆታል ።

ከአለምአቀፍ የመረጃ ዳታዎች ብዙውን ጊዜ በማሰባሰብ ነባራዊ ደረጃዎችን በማሳወቅ የሚታወቀው እና ከ 2.7 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው የሶሻል ሚዲያ ባለሞያ እውነታውን ሊያሳውቀን ችሏል ።

ይህንን ያበቃለት ደካማ ስርአት በሁሉም ረድፍ ሁሉም በድርሻው የመታገል ኃላፊነት አለበት ።


Beles Media - በለስ ሚዲያ dan repost
በመንግስት ታጣቂዎች የተገደለው ሀኪም ጋር አብረውት የተማሩ እና የሰሩ ጓደኞቹ ከሰጧቸው አስተያየቶች መካከል !!

******
ቀዳሚው ሰው

ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ልፋትህን አፈር በላው እኮ። አንዱ ተቀጠፈ! አይ ርጋታ! አዬ ትህትና! 2005 ዓ/ም የወርቅ ሜዳልያ ሸልመህ፣ ህዝብህን አገልግል ብለህ የሸኘኸው ፍሬህ በአጭር ቀረ።

የጅማዋ ኪዳነ ምህረት ደጅሽን በነጋ በነጋ 6 ዓመት ሙሉ ይሳለምሽ የነበረው ልጅሽ፣ ደሙ በከንቱ ፈሰሰች!!! የሰማይ ቤቱን አደራሽን!!!

ሌላው ጓደኛ

1 ሚሊዮን ሰው ነው የሞተው ብቻውን አልሞተው። ትህትናው እውቀቱ እርጋታው ሁሉን ጥበብ የታደለ ሀኪም ነበር። እግዚአብሔር ለልጆቹ እና ለዚ ምስኪን ህዝብ ሲል ባቆየልን የነበር። ያሳዝናል በጣም በጣም። ወንድማለም እግዚአብሔር ነፍስህን ይቀበላት። ነፍስ ይማር

ሶስተኛው ሰው

በእውቀት በፀባይ በትህትና በሁሉም ነገር የባረከህ እንዲህ በአጭር ሊወስድህ ነው ???

ወይኔ እኔ አፈር ልብላልህ የኔ ትሁት !!

አራተኛው አስተያየት ሰጭ

ዶር አንዷለም ዳኜ አብሮኝ የተማረ ባቼ ነው። የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም ነው። በትምህርት ጀግንነቱ በዘመናት መካከል እንደ አጋጣሚ ልታገኘው የምትችለው እንቁ ልጅ ነው። ባህርዳር ሲሰራ አምሽቶ ሲወጣ ገደሉት እያሉኝ ነው😪😪😪 እጅግ በጣም ያማል። ነፍስህ በሰላም ትረፍ ወንድማለም!!!

አምስተኛው አስተያየት ሰጭ

"አንዱ"ን አይደለም ያጣነው ሚሊዮኖችን እንጂ።
አይ ወንድሜ እንደዚህ በቅርቡ ትጠራለህ ብዬስ አስቤም አላውቅ ነበር። ላንተስ ከዚህ ከንቱ የመባላት ዓለም ነው የተገላገልህ። ወዮ ለሚሊዮኖች! ወዮ ለሀገሬ! ወዮ ለወገኔ! 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.