♦ የእሳት ልጅ አመድ . . .
ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እና መንበረ ፓትሪያሪክ አጥርን ሊያፈርሱት ነው !
የኮሪደር ልማት በሚል ሰበብ አዲስ አበባን ታሪክና ምስል አልባ ለማድረግ የሚሮጠው ሩጫ፣ የፓትሪያሪኩን መንበር እና የቅድስት ማርያምን አጥር ወደ ማፍረስ እያደገ ነው። ነገ መቅደሱ እንደማይፈርስ ምንም ማስተማመኛ የለንም።
የመንበረ ፓትሪያሪክ ቅድስት ማርያም አጥር ላይ ከ2 ሜትር እስከ አራት ሜትር የሚደርስ ገብተው ለማፍረስ ማቀዳቸውን ፣ በቀይ ቀለም አጥሩ ላይ በመፃፍ ምን ታመጣላችሁ ብለዋል ።
ሀገር አናስነካም የሚሉ አባቶች የነበሩባት ሀገር፣ የቤተክርስቲያን ቅጥር ሲፈርስ ዝምታን የሚመርጡ አባቶች ተፈጥረውባታል። አባቶቻችን መድፍ ከፊታቸው ተደቅኖ ፤ ሃገር የሚወር ሐይማኖት የሚያጠፈ ሲመጣ እጅ እንዳንሰጥ ይመክሩን ነበር ።
ክፉው ዘመን መጣና ግን ከአምላካችን ይልቅ የአገዛዙን ሥርዓት መሪ የሚፈራበት ዘመን ተደርሷል። ጭራሽ ከአሳዳጆቻችን ጋር ኅብረትን ፈጥረዋል ፤ ምንም ሀፍረት አይታይባቸውም። ይባስ ብሎ ከመሀላቸው ገዳዮቻችንን የተቃወሙትን እንደ ጠላት ሲያሳድዱ ይታያሉ።
ዛሬ ለኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ምልክት የሆነውን መንበረ ፓትሪያሪክ እና ቅድስት ማርያም ሊፈርሱ በቀይ ቀለም ሲፃፍባቸው ትንፍሽ ያለ አባት አልታየም። ያሳፍራል😭!።
ነገስ መቅደሱን ቢያፈርሱት ይናገሩ ይሆን ?!
👉 ይድነቃቸው ከበደ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖