+ ሌላ መንገድ +
ሰብአ ሰገል ወደ ሄሮድስ ሔደው ስለተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ጠየቁ:: ከዚያም በኮከብ ተመርተው ወደ ክርስቶስ ደረሱ:: ሔደውም ሰገዱለት:: እጅ መንሻም አቀረቡ::
ከዚያ በኋላ ግን "ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ" ማቴ. 2:12
ይህ መልእክት የተነገራቸው ስለ ሁለት ነገር ነው:: የመጀመሪያው ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ስለሚፈልግ ለሄሮድስ መረጃ እንዳይሠጡ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለተወለደው የአይሁድ ንጉሥ እየመሰከሩ የመጡበትን መንገድ ትተው አየነው እያሉ በሌላ መንገድ እንዲመሰክሩና የሕፃኑ ንጉሥ ዝና እንዲሰፋ ወንጌል እንዲስፋፋ ነበር::
መልአኩ ወደ ሄሮድስ አትመለሱ አለ እንጂ “ሄሮድስ ሊገድለው ነው" አላላቸውም:: ምክንያቱም ይህን ዜና ቢሰሙ ጦር ይዘው የመጡ ነገሥታት ናቸውና "እኛ እያለን እስቲ ይሞክረን" ብለው ውጊያ ሊያነሡ ይችሉ ነበር:: የሰላም አለቃ የተባለው ህፃኑ ክርስቶስም የውጊያ መነሻ ይሆን ነበር:: ክርስቶስ ግን የምትዋጋለት ሳይሆን የሚዋጋልህ አልፎም የሚወጋልህ አምላክ ነው::
በዚህ መሠረት ሰብአ ሰገል
"ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
ወዳጄ ክርስቶስን ሳታገኝ በፊት ሄሮድስ ጋር ብትሔድ ችግር የለውም:: ክርስቶስን ካገኘህ በኋላ ግን ወደ ሄሮድስ መመለስ ኪሳራ ነው:: እንደ ሰብአ ሰገል ለጌታ እጅ መንሻ አቅርበህ ፣ ዘምረህ ፣ የከንፈር መሥዋዕት አቅርበህ ነፍስህ መድኃኒትዋን አግኝታ ከተደሰተች በኋላ ሕይወት እንዴት ይቀጥላል?
ወደ ሄሮድስ ልትመለስ ይሆን? እንዳታደርገው! ሄሮድስ ጋር ያለው ኃጢአት ነው:: ሄሮድስ ጋር ያለው ክፋት ነው:: እመነኝ እንደ ሰብአ ሰገል ጌታህን ካገኘህ ወዲህ ወደ ሄሮድስ አትመለስ!
ወዴት ልሒድ ካልከኝ መልሱ እዚያው ላይ አለ :‐
"በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው ሔዱ"
እስቲ ሌላ መንገድ ሞክር! ትናንት ያልኖርክበትን ዓይነት ኑሮ ፣ ትናንት ያልሞከርከው የንስሐ መንገድ እስቲ ዛሬ ሒድበት! ሌላ መንገድ አልነግርህም "መንገድም ሕይወትም እውነትም እኔ ነኝ" ያለህ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እርሱ ነው:: በእኔ ኑሩ እንዳለ በእርሱ ኑር:: አደራ ወደ ሄሮድስ እንዳትመለስ!
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 2 2017
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo