📓🌓 ቅምሻ 🌗📓
🇪🇹 ክፍል ሰባት 🇪🇹
የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣኖች የጥላቻቸው ባህሪ እና አተገባበር ነጻብራቅ ረዘም ያለ ጊዜ የቆየ ቢሆንም ለዚህ ምክንያታዊ መግለጫ አላገኘሁለትም፡፡ ብዙ ሰዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ላይ ያሉ ስለ ወደፊት ምንይመጣል አያሉ ነው ምክንያቱም በቀጣይነት የሚከሰተው ሁኔታ የማይታወቅ እና ለመተንበይም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ፣ የጥንት 19ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚፈሩትን ሰዎች በትክክል ለመረዳት አልችልም፡፡ በሞያዬ ካለኝ ልምድ አንጻር ያለፈውን ጊዜ የሚፈሩ እና የሚሸበሩ ወንጀለኞ ይሄዉም በፊት በፈፀሙት ወንጀል የሚያዙ ሰለሚመስላቸውና ሰለሚፈሩ ነው:: በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎችን መብት የጣሱ እና የደፈጠጡበትን ወንጀል ለመደበቅ ሲሉ ጥላቻን በማራመድ እና ከፋፍሎ መግዛትን አጀንዳቸው አድርገው ይይዙታል ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ጎሳዎች ላይ ጥልቅ ጥላቻና እና ፍርሀትን በመፍጠር ለፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እና ኃላፊነትን እንዳይወስዱ የጥላቻ መንፈስን እንደ መርህ በመያዝ ያራምዳሉ፡፡ በህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራትም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተወጥረው ያሉትን ዜጎች ሀሳቦች ለማስቀየሻ ይጠቀሙበታል፡፡
በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣ ወርቃማው ህግ እንዲህ ይላል፣ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ፡፡“ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “የሚጠላህን እንደ እራስህ ውድ፡፡“ ከመጥላት ይልቅ መውድደ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ጥላቻ ወርዋሪውን ተመልሶ እንደሚጎዳ ቦንብ ነው፡፡ መጀመሪያ ከሚወረውረው ሰው እጅ ይወጣል ተመልሶ ግን በጥላቻ የተሞላውን ሰው እራሱን ይጎዳዋል፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ፣ ጥላቻ የነብስ መርዝ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞሉት በሚጠሉበት ጊዜ መርዝን ይጠጣሉ እናም የሚጠሏቸው እንዲሞቱ ይጠብቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ጥላቻን ማራመድ እንዳለባቸው ልዩ ምክር የሚሰጥ ለየት ያለ የፍልስፍና ዓይነትም አለ፡፡ ጥላቻ ሁልጊዜ የተጠላውን ሰው የተወደደ እና የተከበረ ስብዕና ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጠው ያሉ ወገኖች በዱሮዋ ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት የአፓርታይድ መሰል የመንፈስ ጓዶቻቸው ትምህርቶችን ሊማሩ ይገባል፡፡ የአፓርታይድ ጌቶች የማንዴላን ስብዕና፣ አመራር እና ክብር ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማዋረድ ፈለጉ፡፡ ማንዴላ አሸባሪ እና ኮሙኒስት ናቸው በማለት ማንኛውንም ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ይንንም ምክንያት በማድረግ ማንዴላ በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ምስላቸው እንዳይወጣ አደረጉ፡፡ ሆኖም ግን ያልታሰቡ አጋጣሚዎች ተከሰቱ፡፡ በሂደት ጊዜ እያለፈ እና የጸረ አፓርታይድ ንቅናቄው እየተጠናከረ ሲሄድ ማንዴላን አሳንሶ የማየት አባዚያቸው የማንዴላን የመላዕክነት ደረጃ ከፍ እያደረገ ወደ ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌነት እንዲሸጋገሩ እገዛ አደረገላቸው፡፡ ከዚህ ሊወሰድ የሚችለው ታላቅ ቁምነገር የአጼ ምኒልክን እና የአጼ ኃይለስላሴን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ ጥረት ባደረጉ ቁጥር እነዚህ መሪዎች በኢትዮጵያ የወጣቶች ትውልድ የአስተሳሰብ አድማስ ዘንድ የበለጠ ክብር እና ሞገስን እየተቀዳጁ ታዋቂ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ በእነዚህ መሪዎች ላይ የማያቋርጥ እና ዘለቄታዊ ያለው የማዋረድ ዘመቻ ባደረጉ ቁጥር የቀድሞው ትውልድ ጉዳዩን የበለጠ እንዲገመግመው እና አቋሙን እንዲያጠናክር ያደርገዋል፡፡
ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች........
~ ይቀጥላል ~
ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም
❣ እናመሠግናለን ❣