የኛ መፀሐፍቶች / Our Books🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የተለያዩ የ ኢትዮጵያ እንዲሁም የ ዉጭ መፅሐፍቶችን እዚህ ያገኛሉ....... በማንበብ እራሳችንን ወደተሻለ ከፍታ እናድርስ ::
ከ1000 በላይ መፅሐፎችን እንዲሁም የ ዉጭ የየወሩ ምርጥ 10 መፅሐፍቶችን ያገኛሉ::
We want to bring back the reading culture.
Sources, telegram, drives, personal libraries
Our contents are free.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የኮስሞቲክስ ፣ የሞባይል አክሰሰሪ መደርደሪያ እና ለተለያዩ እቃዎች መደርደሪያ ለሱቆች !!
@Daron_12 ላይ ያናግሩን
ወይንም
📞 0940255925 ይደውሉ


እኔ አንችን ሳፈቅርሽ

አሌክስ አብረሀም




ዳንኤል ክብረት

ትልቅ ሰው


ታገል ሰይፉ

የተማረ ይግደለኝ !






የነጻነት ጎህ ሲቀድ.pdf
21.3Mb
ጸሀፊ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ






ቀይ ሽብር በኢትዮ.pdf
8.5Mb
📖 ርዕስ:ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ

📖 ደራሲ: ባቢሌ ቶላ

📖 ተርጓሚ: ጸጋዬ ገብረመድህን

📖 የገጽ ብዛት:244

📖 የህትመት ዘመን: 1989ዓ.ም

📖 ዘውግ: ታሪክ


የመንጌ ውሽሚት - ተስፋዬ አለነ አባተ.pdf
28.9Mb
#እንደ_ናና_ከረሜላ_የሚጣፍጡ_ታሪኮች

የኢትዮጵያውያን የልጅነት ህይወት መመሳሰሉ ሲያስገርም ❤️

በልጅነቱ ጋዝ ግዛ ተብሎ የተላከ ፣ ገላውን በሳፋ የታጠበ ፣ አሹቅ ያነከተ ፣ በወተት ላስቲክ ኳስ ያንጠባጠበ ፣ በካልሲ ኳስ ሰርቶ የተጫወተ ፣ የወደቀ እቃ አግኝቶ ብጌ .. ባትጌ የተባባለ ፣ ጀላቲ የመጠጠ ፣ • ቡቲካ • ተባብሎ የተኮራረፈ ፣ የማርያም ጣቶቹን አቆላልፎ የታረቀ ፣ ፔፕሲ የተገዛለት .. ፔፕሲው እንዳያልቅበት በውሀ የበረዘ ፣ ለበዐል አዲስ ልብስ የተገዛለት .. ልብሱ እንዳይቆሽሽ አጥብቆ የተጨነቀ ፣ ፊኛ ( አፉፉ ) ያስገዛ ፣ ጎረቤት ቤት ቁጢጥ ብሎ ቲቪ ያየ ፣ • እቃ እቃ • ሹሌ • እርግጫ • ሰኞ ማክሰኞ • ፔፕሲ • ቅልልቦሽ • ሱዚ • ሌባና ፖሊስ • አባሮሽ እና አኳኩሉ የተጫወተ ፣ እሟ ቀሊጥ ያለ .. ያስባለ ....... ይህን መፅሀፍ ሲያነብ በደስታ ይሞታል ።

ሙሀመድ ሰልማን : የፒያሳ መህሙድ ጋ ጠብቂኝ መፅሀፍ ደራሲ


ሐሽማል ትረካ ክፍል 4
ደራሲ ፡ ማዕበል ፈጠነ


ሐሽማል ትረካ ክፍል 3
ደራሲ ፡ ማዕበል
ፈጠነ


ሐሽማል ትረካ ክፍል 2
ደራሲ ፡ ማዕበል
ፈጠነ


ሐሽማል ትረካ ክፍል 1
ደራሲ ፡ ማዕበል
ፈጠነ


Albert_Einstein_አልበርት_አንስታይን
#ማቆያ ስለ አንስታይን የህይወት ታሪክ!
⏱ : 26:55min


📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ስምንት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች እና በህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ፍቅር ያለውን የማይበገር የአሸናፊነት ኃይል፣ እንዲሁም ፍቅር በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት የተዘራን የጥላቻ ካንሰር የመፈወስ ችሎታ እንዳለው በግልጽ አስተምረውናል፡፡ ማንዴላ ለመጥላት እና በቀልን ለመፈጸም ምክንያት አላቸው፡፡ ለ27 ዓመታት የማንዴላ ስም የእስረኛ ቁጥር 46664 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 1990 ጧት ከእስር ቤት ተለቅቀው ከእስር ቤቱ በር ሲወጡ ከሚሊዮን ዶላር ዋጋ በላይ የሚያወጣውን ፈገግታቸውን አሳይተዋል፡፡ ለ27 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው በእስር ቤት ውስጥ ባማቀቋቸው የአፓርታይድ ጌቶች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላሳዩም፡፡ ማንዴላ ታላቅ ትምህርት አስተምረውን አልፈዋል፣ እንዲህ በማለት፣ “እየተራመድኩ ወደ በሩ በምቃረብበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ወደ ነጻነት እየመራኝ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡ የበቀልተኝነት ስሜቴን እና ጥላቻዬን እዚያው እስር ቤት ጥዬው ካልወጣሁ እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡“ በማለት የጥላቻን መጥፎነት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ማንዴላ ፍጹም የጥላቻ እስረኛ አልነበሩም፡፡ እስረኛው የአፓርታይድ ጥላቻ ነበር፣ እናም አስረኞቹ የአፓርታይድ አለቆች እና ጌቶች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ከእስር ቤት በመውጣት በጥላቻ ሰንሰለት ከአፓርታይድ ግንብ ጋር የታሰሩትን እውነተኞቹን የአፓርታይድ እስረኞች ከጥላቻ፣ ከፍርሀት፣ እና ከበቀልተኝነት ነጻ ለማውጣት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ገዥዎች በጥላቻቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ዕጣ ፈንታ የሚደርስባቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
በአፓርታይድ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ “ነጻዎቹ” ነጮች እውነተኛው የማይቀረው የብዙሀን አገዛዝ በሚመጣበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ በጭቆና ቀንበር አስረው ሲያማቅቋቸው የነበሩት ጥቁር አፍሪካውያኖች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ሌት እና ቀን ያሰላስሉ ነበር፡፡ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የነበራቸው ጥላቻ እንቅልፍየለሽ ሌሊቶችን ብቻ እንዲያሳልፉ አላደረጓቸውም፣ ሆኖም ግን ልቦቻቸው፣ አዕምሯቸው እና ነብሳቸው እንዲሁም ስብዕናዎቻቸውም ጭምር እንዲሰበሩ አደረጋቸው እንጅ፡፡
ሙት መንፈሶች አደረጓቸው፣ ነጻ ሆነው ባሏቸው ኃብቶቻቸው ለመደሰት ባለመቻል የቁም ሙት አደረጓቸው፣ እንዲሁም በኤሌክትሪክ እና በእስር ቤት የሽቦ አጥር ታጥረው የእራሳቸው ጎረቤቶች የእስር ቤት በሮች ሆኑባቸው፡፡ በእርግጥ በጦር ካምፕ የሚኖሩ ህዝቦች ሆኑ፡፡

ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡

በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ......

~ ይቀጥላል ~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

❣ እናመሠግናለን ❣


📓🌓 ቅምሻ 🌗📓

🇪🇹 ክፍል ሰባት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣኖች የጥላቻቸው ባህሪ እና አተገባበር ነጻብራቅ ረዘም ያለ ጊዜ የቆየ ቢሆንም ለዚህ ምክንያታዊ መግለጫ አላገኘሁለትም፡፡ ብዙ ሰዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ላይ ያሉ ስለ ወደፊት ምንይመጣል አያሉ ነው ምክንያቱም በቀጣይነት የሚከሰተው ሁኔታ የማይታወቅ እና ለመተንበይም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ፣ የጥንት 19ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚፈሩትን ሰዎች በትክክል ለመረዳት አልችልም፡፡ በሞያዬ ካለኝ ልምድ አንጻር ያለፈውን ጊዜ የሚፈሩ እና የሚሸበሩ ወንጀለኞ ይሄዉም በፊት በፈፀሙት ወንጀል የሚያዙ ሰለሚመስላቸውና ሰለሚፈሩ ነው:: በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎችን መብት የጣሱ እና የደፈጠጡበትን ወንጀል ለመደበቅ ሲሉ ጥላቻን በማራመድ እና ከፋፍሎ መግዛትን አጀንዳቸው አድርገው ይይዙታል ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ጎሳዎች ላይ ጥልቅ ጥላቻና እና ፍርሀትን በመፍጠር ለፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እና ኃላፊነትን እንዳይወስዱ የጥላቻ መንፈስን እንደ መርህ በመያዝ ያራምዳሉ፡፡ በህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራትም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተወጥረው ያሉትን ዜጎች ሀሳቦች ለማስቀየሻ ይጠቀሙበታል፡፡

በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣ ወርቃማው ህግ እንዲህ ይላል፣ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ፡፡“ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “የሚጠላህን እንደ እራስህ ውድ፡፡“ ከመጥላት ይልቅ መውድደ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ጥላቻ ወርዋሪውን ተመልሶ እንደሚጎዳ ቦንብ ነው፡፡ መጀመሪያ ከሚወረውረው ሰው እጅ ይወጣል ተመልሶ ግን በጥላቻ የተሞላውን ሰው እራሱን ይጎዳዋል፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ፣ ጥላቻ የነብስ መርዝ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞሉት በሚጠሉበት ጊዜ መርዝን ይጠጣሉ እናም የሚጠሏቸው እንዲሞቱ ይጠብቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ጥላቻን ማራመድ እንዳለባቸው ልዩ ምክር የሚሰጥ ለየት ያለ የፍልስፍና ዓይነትም አለ፡፡ ጥላቻ ሁልጊዜ የተጠላውን ሰው የተወደደ እና የተከበረ ስብዕና ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጠው ያሉ ወገኖች በዱሮዋ ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት የአፓርታይድ መሰል የመንፈስ ጓዶቻቸው ትምህርቶችን ሊማሩ ይገባል፡፡ የአፓርታይድ ጌቶች የማንዴላን ስብዕና፣ አመራር እና ክብር ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማዋረድ ፈለጉ፡፡ ማንዴላ አሸባሪ እና ኮሙኒስት ናቸው በማለት ማንኛውንም ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ይንንም ምክንያት በማድረግ ማንዴላ በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ምስላቸው እንዳይወጣ አደረጉ፡፡ ሆኖም ግን ያልታሰቡ አጋጣሚዎች ተከሰቱ፡፡ በሂደት ጊዜ እያለፈ እና የጸረ አፓርታይድ ንቅናቄው እየተጠናከረ ሲሄድ ማንዴላን አሳንሶ የማየት አባዚያቸው የማንዴላን የመላዕክነት ደረጃ ከፍ እያደረገ ወደ ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌነት እንዲሸጋገሩ እገዛ አደረገላቸው፡፡ ከዚህ ሊወሰድ የሚችለው ታላቅ ቁምነገር የአጼ ምኒልክን እና የአጼ ኃይለስላሴን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ ጥረት ባደረጉ ቁጥር እነዚህ መሪዎች በኢትዮጵያ የወጣቶች ትውልድ የአስተሳሰብ አድማስ ዘንድ የበለጠ ክብር እና ሞገስን እየተቀዳጁ ታዋቂ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ በእነዚህ መሪዎች ላይ የማያቋርጥ እና ዘለቄታዊ ያለው የማዋረድ ዘመቻ ባደረጉ ቁጥር የቀድሞው ትውልድ ጉዳዩን የበለጠ እንዲገመግመው እና አቋሙን እንዲያጠናክር ያደርገዋል፡፡
ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች........

~ ይቀጥላል ~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

❣ እናመሠግናለን ❣


🇪🇹 ክፍል ስድስት 🇪🇹

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ፦

አጼ ምኒልክን መጥላት ይወዳሉ፣

ጥላቻ የነብሳችን የመጨረሻው የበሽታ ምልክት ነው፡፡ ጥላቻ ኢምክንያታዊ ነው ወይም አመክንዮ የለውም፡፡ በጥላቻ ላይ የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ጽሁፎች እንደሚያመለክቱት በጥላቻ የተመረዙት ምንጊዜም ይጠላሉ ምክንያቱም ይፈራሉ፣ ደህንነት አይሰማቸውም፣ ምቀኞች ናቸው፣ ወይም ደግሞ እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም የጥላቻቸው መነሻ እና መድረሻ እነዚሁ በጥላቻ የተሞሉት ግብዞች ናቸውና፡፡ ከሁሉም በላይ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም ብቁነት የጎደላቸው፣ ኃይልየለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ እና የእረዳትየለሽነት ስሜት የተጠናወታቸው ነው፡፡ ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሰው በቆዳው ቀለም፣ ወይም ደግሞ በማንነቱ፣ ወይም በኃይማኖቱ ምክንያት ብቻ ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች መጥላትን መማር አለባቸው፣“ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉትን የገዥው አካል ኃላፊዎች ሁኔታ በማስብበት ጊዜ በማንዴላ ፍልስፍናዊ ግምገማ ላይ አምነት ማጣት ይቃጣኛል፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለትም አክለዋል፣ “መጥላትን የሚማሩ ከሆነ ፍቅርን ሊማሩም ይችላሉ፣ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው የበለጠ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የመስረጽ ተፈጥሯዊ ባህሪ አለውና፡፡“ ተቃራኒውን በተጨባጭ የሚያመላክቱ በርካታ መረጃዎች ቢኖሩም የማንዴላ መርሆዎች በስልጣን ላይ ባሉት ባለስልጣኖች ሁሉ ሊተገበሩ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
በመርህ እና በተግባርም እንደሚታየው በጋንዲ መርሆዎች መሰረት ለመኖር ጥረት ማድረግ አለብን፣ “ኃጢያተኛውን ሳይሆን ኃጢያቱን እንጥላ፣“ በጥላቻ የተመረዙትን የምንጠላ ከሆነ የእነርሱ የመስታወት ነጸብራቅ እንሆናለን፣ እራሳችንም የምንጠላቸውን እንሆናለን፣ እንደ ሰው ስብዕና አቶ መለስን እና መሰሎቻቸውን የምንጠላ ከሆነ እነርሱኑ ሆን ማለት ነው፡፡ የምንጠላ ከሆነ ምግባራቸውን እንጅ እንደ ሰው እራሳቸውን መሆን የለበትም፡፡

ጥላቻ ጠንካራ ኃይል ነው፡፡ በናዚዝስቶች የተሰራጨው ጥላቻ አገሮችን በጠቅላላ እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ በሩዋንዳ የተከሰተው ጥላቻ የሚሊዮኖችን ሩዋንዳውያን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በዳርፉር የተቆሰቆሰው ጥላቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኃይማኖት ጥላቻ በናይጄሪያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ወደ ጥላቻ መግባት የለብንም፡፡
በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ህዝቦች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ“ የሚለውን ወርቃማ ህግ የሚከተሉ ህዝቦች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “የመዳብ ህግ” እያልኩ በምጠራው “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ጥላ“ እያሉ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የእራሳቸውን እረዳትየለሽነት፣ የደህንነት እጦት ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና በጥላቻቸው መሳሪያነት ድርጊቶችን በመለወጥ አሸናፊነትን የሚጎናጸፉ ይመስላቸዋል፡፡ ሌሎችን በመጥላት የራሳቸውን የበታችነት ስሜት እና የእራስን ዋጋ ዝቅ አድርጎ የማየት ችግራቸውን በማስወገድ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ይመስላቸዋል፡፡ አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች በእርግጥ አይጠሏቸውም፣ እራሳቸውን የሚጠሉ እና ምኒልክን ለመሆን የሚያስቡ ምኒልክ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ሁሉ አዝንላቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ እነዚህ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች የኢትዮጵያን ታላላቅ መሪዎች እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት በመቀባት በቅርቡ በህይወት የተለዩትን መሪያቸውን እና የሁለት አስርት ዓመታት ኃጢያታቸውን በማስሰረይ ብጹ የሚያደርጓቸው ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ ኃይለስላሴን በጎ ተግባራት ጥላሸት በመቀባት የአቶ መለስን ስብዕና የሚገነቡ ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን ሐውልት ከህዝባዊ ቦታዎች በማራቅ እና የአቶ መለስን እርካሽ ወረቀት ፎቶግራፎች በየመንገዶች ላይ በመለጠፍ አቶ መለስን ወደ መልዓክነት ያቀረቧቸው ይመስላቸዋል፡፡ አቶ መለስ የአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ከንክሩማህ ቀጥሎ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይቆም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ንክሩማህ እራሳቸው የአጼ ኃይለስላሴ ያልተጠቆጠበ ጥረት ባይኖር ኖሮ የአፍሪካ ድርጅት እውን መሆን አይችልም ነበር በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ.....

~ ይቀጥላል ~

ምንጭ:-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

❣ እናመሠግናለን ❣

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

2 882

obunachilar
Kanal statistikasi