“You never really understand a person until you consider things from his point of view… until you climb into his skin and walk around in it.”
Harper Lee, 'To Kill a Mockingbird'
_
መግባባት በሌሎች ጫማ ውስጥ ለመቆም የመድፈር ውጤት ነው... መጣጣም ግማሽ መንገድ ለመምጣት የመፍቀድ ፍሬ ነው... እንድረዳህ አንተ ቦታ ቆሜ ነገሩን ማየት ይኖርብኛል... እንድትረጂኝ በኔ በኩል አሻግረሽ ሁኔታውን መመዘን ይጠበቅብሻል...
መግባባት የግድ ሁኔታውን መቀበልን አያሳይም፣ ይልቁን የእሳቤ ማዕዘኑን መረዳትን ያጠይቃል እንጂ... አሜን ማለትን አይነግርም፣ 'አሃ...' ማለትን ያንጸባርቃል እንጂ...
ሰውየው አቋም የያዘበትን ምክንያት መረዳት ከስምምነት ለመድረስ የመጀመሪያው ደረጃ ነው... የሴትየዋን የእምነት ጠገግ መገንዘብ የመቀራረቢያ መንገዳችሁ ጥርጊያ ነው...
"ይህን ሰውዬ አልወደድኩትም፣ በደንብ ላውቀው ይገባል" ያለው ማን ነበር?...
"I don't like that man. I must get to know him better." - Abraham Lincoln
ሳይረዱ መስማማት የለም፣ ሳይገነዘቡ መደራረስ የለም... መግባባት ከ 'እኔን ስሙኝ' አይጀምርም - ከ 'እስኪ ላድምጥህ/ሽ' ይለጥቃል እንጂ... መገንዘብ ለሌላው እሳቤ እውቅና ከመንፈግ አይወለድም - ምልከታን ወደ ጠረጴዛ ከመሳብ ይሰናኛል እንጂ...
ሌላን መረዳት የራስን ኢጎ ጥግ ከማስያዝ ይጀምራል፣ ሌላን መገንዘብ ግለሰባዊ ገደብን ከማወቅ ይወለዳል... የልክ ነኝ ጥመትና ራስን ያለመፈተሽ ግትርነት የመግባባት ድልድይን ይንዳል... ሃሳብን በምክንያት ያለመለዋወጥ ልምምድና የ 'ካፈርኩ አይመልሰኝ' አባዜ የመቀራረብ ፍላጎትን ይጎዳል...
ስብሐት ገ/እግዚአብሔር በአንድ መጣጥፉ ላይ "የሰለጠኑ ሰዎች የትክክለኛነትን ዕድል ለሌሎች በመስጠት ያምናሉ" ብሎ ነበር፤ እውነቱን ለመናገር ሰውን አንድ ጊዜ 'በተሳስተሃል' ሚዛን ዶለኸው ስታበቃ ልትገነዘበው መሞከር ያጣመምከውን ሚስማር እንደ መጀመሪያ ተፈጥሮው ካልሆነ የማለት ያህል ከንቱ ድካም ነው...
ሁሌም ቢሆን 'ከእኛ የተሻለ ሃሳብ ሌሎች ዘንድ ይኖራል' ብሎ ማሰብ አዳዲስ ምልከታዎችን ወደ ራስ ለመሳብ ሁነኛ መንገድ ነው... ነገሩ የአጉል ትሁት ነኝ ባይ አስመሳይነት አልያም የራስን ነገር አሳንሶ የማየት ጉዳይ አይደለም - ይልቁንስ ጉድለትን በሌሎች ምልዓት የማስጎብኘት ብልህነት እንጂ...
"ማን ያውቃል ዓለምን - ምስጢሯን ጨርሶ
ያለፈው ቢነግረው - ከሚያውቀው ጠቃቅሶ
ቢጽፈው ቢነበብ - ገብቶት ፊደል ቆጥሮ
እርሱ ያላየው አለ - ሌላው ያየው ኖሮ...
___
ስንቱን ትልቅ ችግር - ሲፈታ የኖረ
ከእርሱ አልፎ ለሌሎች - ዘዴን የቀመረ
ቀላል ነገር ገጥሞት - ሲከዳው ብልሃቱ
በታናሹ ምክር፣ ካሳብ ከጭንቀቱ፣ ሲወጣ ማየቱ
ኦህ... ይገርማል...
ሰነፉ ብርቱ ነው - ከሚያውቀው ሲገኝ
ካለቦታው ገብቶ - አዋቂው ሲሞኝ..."
___
ኢዮብ መኮንን - 'እሮጣለሁ' አልበም
___
አንዳንድ ሰው የሌሎችን ሃሳብ መስማት መተናነስ ነው ብሎ ያምናል... 'የእከሌንማ ሃሳብ መቀበል ደካማነት ነው' ብሎ ይደመድማል... ቀድሞ ነገር የዝቅተኝነት ችግር ያለበት ሰው እንኳንና ሌላን ራሱንም ስለማይሰማ ከሌላ መግባባትን ከማሰቡ በፊት ለግሉ መታከም ይኖርበታል... አደባባይ ከመዋሉ በፊት በራስ ጉባኤ ላይ መዋል ይኖርበታል... የሌላን እንከን ከመንቀሱ በፊት የራሱን ጓዳ ማረቅ ይኖርበታል...
መግባባት 'የአቻነት' ጉዳይ አይደለም፤ የመለካካት መነካካት ነገርም አይደለም... መግባባት ደረጃና አንጃ አያውቅም... የአንደራረስም ጉራና ቀረርቶም አይነካካውም... የጋራ ጉዳይ እስካለህና በሌሎች እገዛ የሚሞላ ሽንቁር በጉዞ መስመርህ እስካልጠፋ ድረስ ሊቅ ብትሆን ረቂቅ፣ ሃብታም ብትሆን ምጡቅ፣ ባለወንበር ብትሆን ባለዝክር ዝቅ ብለህ የምትወስደውና ከፍ ብለህ የምትጠይቀው አይጠፋም - ይህ በምንም ሁኔታ ውስጥ የማይቀየር ሕግ ነው... 'ከፍታ' ደግሞ ከእሳቤ ጥራት እንጂ ነገ ከሚገፋ ወንበር፣ አድሮ ከሚጠፋ ወረት፣ ከርሞ ከሚያልፍ እውቀት ተወልዶ አያውቅም...
___
ስንወጣም እንዲህ እንላለን...
መብት ለመጠየቅ ግዴታን መወጣት የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ ነው... ብዙ ሰዎች ግን የማይገባቸውንም ሳይቀር የሚጠይቁት የሚጠበቅባቸውን ክደው ነው...
አለመግባባት የግል ጥቅምን ብቻ ከማሳደድ ሲመዘዝ መጣጣም የሌላውን ጉድለት ከመረዳት ይጀምራል... ልዩነት በሌሎች ስንጥቅ ከመሳለቅ ሲነሳ ስምረት የራስን ሽንቁር ደፍኖ ከመጀመር ይመነጫል...
መግባባት በራስ ክበብ ውስጥ ብቻ ከመሾር አይቀዳም - በሌሎች ጠመዝማዛ መንገድ ላይ ለመገኘት ከመድፈርም ጭምር እንጂ... መግባባት 'እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል' ከሚል እኔነት አይጸነስም - 'እኔ ሞቼ ሰርዶ አበርክቼ' ከሚል እኛነት ውስጥ እንጂ...
'የሃሳብ ልዩነት ለዘላለም ይኑር' ለሚሉ ሰዎች መግባባት የፈጠራ ማግስት ሲሆን 'ተቀበል' ብቻ ለሚሉ አምባገነኖች ደግሞ የውድቀት ዋዜማ ነው...
___
"Only the development of compassion and understanding for others can bring us the tranquility and happiness we all seek." ~ Dalai Lama