በሸረሪት ተነድፎ አውሮፕላን በድንገት ያሳረፈው ፓይለት
በበረራ ላይ ሳለ ታራንቱላ በተባለች መርዛማ ሸረሪት የተነደፈው ፓይለት አውሮፕላኑን በድንገት ለማሳረፍ መገደዱ ተዘግቧል፡፡ አብራሪው የተነደፈው ከጀርመን ወደ ስፔን እያበረረ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡
ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፤ በሸረሪት የተነደፈው አብራሪ፣ ጸረ-መርዝ መድሃኒት እስከሚሰጠው ድረስ የኢቤሪያ አውሮፕላን በረራ ዘግይቶ ነበር፡፡
ይህ የአየር ላይ ድራማዊ ክስተት የተፈጠረው የኢቤሪያ ኤ-320 አውሮፕላን ከጀርመን ዱሰልዶርፍ ተነስቶ ወደ ስፔኗ ማድሪድ ከተማ እየበረረ በነበረበት ወቅት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ሸረሪቷ አውሮፕላኑ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሞሮኮ ካዛብላንካ ባረፈበት ወቅት ገብታ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ አውሮፕላኑ በስፔን ዋና ከተማ ካረፈ በኋላ እስከሚጸዳ ድረስ ሦስት ሰአት በመዘግየቱ፣ ወደ ጋሊሺያኗ ከተማ ቪጎ የሚሄዱ ተጓዦች እንዲጠብቁ መደረጋቸው ነው የተነገረው፡፡
አብራራው እብጠት የሚያስከትሉ በሽታዎችን ለማከም የሚውለውና ከከባድ አለርጅክ ጋር የተያያዙ እብጠቶችንና ሌሎች ምልክቶችን ለመቀነስ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው ኡርባሶን ወይም በሳይንሳዊ ስያሜው ሜታይልፕሬዲኒሶሎን የተባለ መድሃኒት ተሰጥቶታል።
ሸረሪት የወጣችበት አውሮፕላን ከካዛብላንካ ተነስቶ ስፔን ከመድረሱ በፊት ብራሰልዝ፣ ዙሪክና ቶሎዜን በመሳሰሉ ከተሞች ላይ አርፏል ነው የተባለው።
ምንም እንኳን አውሮፕላኑ አርብ ሌሊት ቪጎ ከማረፉ በፊት ቢጸዳም፣ የተወሰኑ መንገደኞች ሸረሪት ፈርተው መቀመጫቸውንና መተላለፊያውን በተደጋጋሚ ሲፈትሹ መስተዋላቸው ተዘግቧል።