ሰነፍ ፍቅር
"ሃሳብ ያለው ብቻ ነው አይደል ሚናገረው?"አሉ አባት"ኸረ ሁሉም ነው" ልጆቹ አልጎመጎሙ።የሰዎቹ እምነት እጅን በአፍ ያስጭናል እንደ ድግስ ወጥ ታዳሚውን ለማጥገብ የሚያንተከትኩት ፍቅር ተጨልፎ ተጨልፎ እየጣመ የጎረሱት ሰዎች አድናቆት እነ ጳውሎስ ዘንዳ ደርሶ ማመስገኛ ሆኗል።በመከራቸው መፅናታቸው ባመኑት እግዚአብሔር ስር ስለመስደዳቸው ማስረጃ ነው።
ውይይቱ ቀጥሏል ተራው ለ9ኙም የቤተሰቡ አባላት ተዘገነ እናት አሟቸው እሶፋው ላይ ጋደም ብለው ያደምጣሉ ዛሬ አስተያየት ያለመስጠት ህጋዊ ባለመብት ናቸው ።ወንድም ነው በተነበበው የተሰሎንቄ የመጀመሪያ 4 ምዕራፍ ላይ ሃሳብ በመስጠት የጀመረው እና እያለ ወረደ ኋላም አባት ተጠየቀ "ስለአንድ ቁጥር ድጋሚ?" ነገሩ እንብዛም አልተዋጠላቸውም ።የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት አይመቻቸው በልጆቻቸው ጉትጎታ መጀመራቸው ነው።የተረዱትን ለመግለፅ ሞከሩ እና ተራው ለመሪዋ ታላቅ ልጅ ተሰጠ ።ሰላምታው በንቀት መታለፉ ገርሟታል አንዳንድ የእግዚአብሔር ሃሳብ እንዲ በቸልታ ማድበስበሱ እየቆጫት እድሉ ደርሷት ያንን እስትተነት ጓጉታ ነበር እናም የእምነት ፣ተስፋ እና ፍቅራቸው መሰረት በክርስቶስ መሆናቸው እንደነበር እናም መመረጣቸውን በእነዚህ 3 ነገሮች ለዓለም እንዳረጋገጡ ተነተነች።በመሃል አባት የአቁሚ ምልክት አሳዩ እንደመከፋት ብላ የማጠቃለያ ሃሣብ ተናግራ አበቃች።እንዳበቃችም አባት በቁጣ" ነገር አታርዝሚ ሰዓቱንኮ ወሰድሽው።ተኝተው የነበሩት እናት ተከተሉ "ሲጀመር ይሄ ቅዳሜ እና እሁድ ነው መሆን ያለበት ተነስቼም እንዳልሰራራ ያዘኝ" "ቆይ ምንድነው ሰዓት ከሆነ መስተካከል ይችላል ወይስ አትፈልጉም?" " አልወጣንም ! በቃ እንፀልይ" "ቆይ አልጨረስኩም በሚቀጥለው ከቁጥር 5-7 ነው ሚሆነው።"ረዘም አርጊው ባሁኑ በጣም ጠልቀን ገባን" አሉ አባት። "እሱ አይደል እንዴ ሚፈለገው ጠለቅ ማለት"መለሰች።"የቃል ጥናት ጥቅስ ደግሞ " "እእእእ!?" "አዎ በቃል የሚያዝ" "ምንድነው ምንሸመድደው"አሉ አሁንም አባት " 1ተሰ 2-3 ቀጣይ ደግሞ እንዳልነው 5-7 " "አትደጋግሚ አንዴ ተናገሪ ጆሯችን ይሰማል" አሉ አሁንም አባት። "እንዴዴዴዴ ምንድነው ነገሩ አልፈለክም እንዴ ምን አመጣው ቁጣውን!?" "ምክንያቱም አርዝመሻል በቃ!" "እኛ ስራ ወለን ነው ምንመጣው ይደክመናል" "አንቺ እኮ አሳብ እንኳ አልሰጠሽም ተኝተሽ አልነበር እንዴ" "እስኪያቅ ቁጭ አልኳ ስራ ምሰራውን" "በኢየሱስ ስም" አለች የኘሮግራሙ መሪ ራሷን በመያዝ። " እሺ አበባ ፀልይ" " ማን እኔ?!" አባት በድንገት ጀመሩ " እግዚአብሔር ሆይ እናመሰግናለን .....
ሆስ