..................https://
t.me/poem_4_lord/ከለታት አንድ ቀን ነዉ ሁሌ በማልፍበት የታክሲ መያዣ አቅጣጫዬ አካባቢ ያለ ትልቅ ቦይ ነበር እናም ዶፍ ሲዘንብ ይመስለኛል አንዲት ሴት ልጆቿን ያዛ በዛ ቦይ ዉስጥ ተሸሸገች ግንብ እና ከሲሚንቶ የተሰራ በመሆኑ አንዳች ዉሃ አያስገባም ነበር እናም ሳስተዉል በአካባቢዉ በተቃራኒ ቦታዎች ላይ ያሉትን ቀዳዶች በሸራ ደፍነዉ ቋሚ መኖርያም ያደረጓቸዉ ሰዎችም ነበሩ ግን አስፋልቱ ቦዮቹን የሚፈልግበት ደረጃ ላይ ሲደር መነሳታቸዉ አይቀሬ ነዉ ምክኒያቱም ቦዮች እንጂ መኖርያዎች ስላልሆኑ ማለት ነዉ።እናም በሰዉ ሂወትም እንዲ ያለዉ ነገር የተለመደ ነዉ እኛ የጌታ ሃሳብ ሚተላለፍን ሆነን ሳለ በኛ ዉስጥ ያስጠለልናቸዉ ከተፈጠርንበት አላማ ርቀን እንድንኖር አርገዉናል።እነዛን ምስኪን ሰዎች ማባረር ጭካኔ አይመስልም? ነገር ግን ትክክለኛዉም ነገር እሱ ነዉ።ሚመስለዉን እና የሆነዉ ነገር መለየት ግድ ነዉ።አዎ ቦዮቹ ላስፋልቱ ሁነኛ ነገር ናቸዉና ያስፈልጉታል።እናንተም ለጌታ ታስፈልጉታላቹ እናም ያስጠለላቹኋቸዉን ሁሉ አስወጡ ስጋ ቢሆን ሃሳብ ቢሆን ልማድ እና ሃጥያት ቢሆን እናት አባት ዘመድ ልጆች ቢሆኑ ለጌታ ታስፈልጉታላቹ እና ከልባቹ ይዉጡ ይንፈስበት ። ያኔ ዜማዉ መድገም መቻል እና ማስተማርም ትችላላቹ ።ባገራችንም ቆሎ ተማሪን ማተት ትችላላቹ ገዳም ርቆ ይሄዳል ዉሎዉ እዛ ምግቡ ቆሎ እንደሁሉም መሆን ሲችል ካዋከበዉ ፍላጎቱ የፈዘዘለትን ዜማ ከኪሱ ሊቀዳ ርቆ ይሄዳል።ራስን መካድ እሱ ነዉ።እንዲህ አለን ወንድም ሄርሞን በአንድ ወቅት ስለደቀ መዝሙር እያወጋን “now a days we are conforming what we are suppose to confront.”......... ከበኔበኩል መጽሃፍ ለቅምሻ