ኑሮ ሲጥለን - ገጥሞን እጅ በ'ጅ
አሜንታ ላይቀል - ለምንታም ላይበጅ
ሕይወት እንደ ሰው - መች ትታማለች
ሥጋ ደህና አይደል - ነፍስም ታማለች
ሞት ቆሞ በሩቅ - ሲል እንቁልልጭ
ኩታ ደርቦ - የሚያብለጨልጭ
አዘጋኝ ጠፍቶ - እፍኝ ጠመዡን
ማልቀስ ተረፈን - እያስጎመዡን
ግን ማልቀስ ከንቱ..
እምባውን ይዞ - ስንቱ አነጅቧል?
ይህ ግጥም እንኳ - በእምባ ታጅቧል
ግን መች ተውቧል?
መቼ ተውቧል - የኑሮ ማጀት
በቃ እጣችን ነው - ሕመም ማቆንጀት?
ሳይነጉ መምሸት - ሳያድጉ ማርጀት?
በዘበት ማለፍ - እንደዳከሩ
ክረምቱስ አልፏል - የታል መከሩ?
ባከነች ነፍሴ
ዘጋኝ በዛባት ባይኖሯት እፊያ
ምን አደከማት? - ኩርፊያና ልፊያ!
ነፍሴን ሸክፏት - አካሌን ቋጥሩት
ንብረቱን ይውሰድ - እግዜርን ጥሩት
እግዜርን ጥሩት - እንድታገለው
ነገን ና በሉት - ይምጣ እንድገለው
በቃ አይግደደኝ - ስለሕልሞቼ
ሊገሉን ሲሹ - ላሸንፍ ሞቼ!
ሁሉንም ወድዶ
ሁሉንም አጥቶ
እንዴት ይኮናል?!
እንዲህ ላለው ጣር - እግዜር ልኮናል!
እግዜር ልኮናል - ኩታ እንባ አልብሶ
ሞት ምን ቢከፋ
ያስለቅሰናል ከሕይወት ብሶ?
ብቻ ደክሞናል!
ብቻ አሞናል!
ባንቀምሰው እንኳን - መሞት ጥሞናል!
[ ዮናታን ጌታቸው ]
@Samuelalemuu
አሜንታ ላይቀል - ለምንታም ላይበጅ
ሕይወት እንደ ሰው - መች ትታማለች
ሥጋ ደህና አይደል - ነፍስም ታማለች
ሞት ቆሞ በሩቅ - ሲል እንቁልልጭ
ኩታ ደርቦ - የሚያብለጨልጭ
አዘጋኝ ጠፍቶ - እፍኝ ጠመዡን
ማልቀስ ተረፈን - እያስጎመዡን
ግን ማልቀስ ከንቱ..
እምባውን ይዞ - ስንቱ አነጅቧል?
ይህ ግጥም እንኳ - በእምባ ታጅቧል
ግን መች ተውቧል?
መቼ ተውቧል - የኑሮ ማጀት
በቃ እጣችን ነው - ሕመም ማቆንጀት?
ሳይነጉ መምሸት - ሳያድጉ ማርጀት?
በዘበት ማለፍ - እንደዳከሩ
ክረምቱስ አልፏል - የታል መከሩ?
ባከነች ነፍሴ
ዘጋኝ በዛባት ባይኖሯት እፊያ
ምን አደከማት? - ኩርፊያና ልፊያ!
ነፍሴን ሸክፏት - አካሌን ቋጥሩት
ንብረቱን ይውሰድ - እግዜርን ጥሩት
እግዜርን ጥሩት - እንድታገለው
ነገን ና በሉት - ይምጣ እንድገለው
በቃ አይግደደኝ - ስለሕልሞቼ
ሊገሉን ሲሹ - ላሸንፍ ሞቼ!
ሁሉንም ወድዶ
ሁሉንም አጥቶ
እንዴት ይኮናል?!
እንዲህ ላለው ጣር - እግዜር ልኮናል!
እግዜር ልኮናል - ኩታ እንባ አልብሶ
ሞት ምን ቢከፋ
ያስለቅሰናል ከሕይወት ብሶ?
ብቻ ደክሞናል!
ብቻ አሞናል!
ባንቀምሰው እንኳን - መሞት ጥሞናል!
[ ዮናታን ጌታቸው ]
@Samuelalemuu