እዚህ ባልሆን
በዚህ ሰአት
ምናልባትም እንዲህ ባልሆን፣
ልሆን የምችለው
እሆነው የነበር የሆነ ሰው ይኖር ይሆን?
ትልቅ ምናልባት ነው
ማለቴ ምናልባት
መለኪያ ባልጨብጥ
አረቂ ባልጠጣ መለኪያውን ባልሰብር፣
የሆነች ቆንጆ ጋር
ጭማቂ እየጠጣሁ
እጇን እየዳበስኩ
አይንአይኗን እያየሁ ሊሆን ይችል ነበር።
ትልቅ ምናልባት ነው
ግን ከዚህ የሚሻል የሆነ 'እኔ' አይጠፋም፣
የሰውን ማንነት 'መሆኑ' አይገልፀውም።
ትልቅ ምናልባት ነው፣
ምናልባት ምናልባት
ሌላ ነበርሽ አሁን
የሆነ ቀን ለታ አንችን ባትሆኚ፣
የዛኑ ቀን ወጥተሽ እኔን ባታገኚ፣
ከህይወት ታሪክሽ ይቺ ቅንጣት ብትቀር፣
የያዝሽው ሲጃራ እጣን ይሆን ነበር፣
ትልቅ ምናልባት ነው...
[ FB; vector de morta ]
@Samuelalemuu