ስሜትን በግጥም dan repost
በራፉ አልተዘጋም ገርበብ ብሎ ነበር። በደከመ ሰውነት ከፍቶት ሲገባ እናቱ ምስር ስትለቅም አገኛት። እግሯ ስር ወደቀ፤እናት አልተደናገጠችም አዘነች እንጂ ነገሩ ገብቷታል። ምስሩን ከጎኗ ካለ ወንበር ላይ አስቀመጠችም። ደገፍ አርጋው አንስታ ጭንቅላቱን ጭኗ ላይ አስቀምጣ ፀጉሩን ትደባብሰው ጀመር ልክ እንደ ልጅነቱ። ....አለቀሰ፤ አላባበለችውም። በማባበል የሚድን ህመም እንዳልሆነ ታውቃለች። ቃል አወጣ። አ...አ...አገባች እኮ። ምንም አልተናገረችውም። ውስጡ ያፈነውን አውጥቶ እንዲቀለው የፈለገች ይመስላል፤ ባይቀለውም። ....ዳርኳት እያየኋት ችቦ አይሞላም ወገቧ ብዬ ብር አምባር ሰበረልሆ ጨፍሬ። አናስገባም ሰርገኛ ሲባል እውነት የማይገባ መስሎኝ አምላክ የውስጤን አይቶ ረዳት እንደላከልኝ ተደሰትኩ፤ ሰርገኞቹ መልአክ ናቸው አልኩኝ። ትንሽ ተጋፉና መሳሳቅ ጀመሩ፤ ሙሽራው የጫጉላው ንጉስ ገባ። እንዴ አምላኬ ሆይ ምነው ተስፋ ሰጥተህ ነሳኸኝ? በወደደ ይቀለዳል? በምን ሀጥያቴ? አምላኬን አማረርኩ። መልአክ የነበሩት በቅጽበት ጋኔል ሆነው ታዩኝ፤ እየተጠቋቆሙ የሳቁብኝ መሰለኝ። ህመሜን ታማው ይሆን ብዬ ተመለከትኳት አይኖቿን ከአይኖቼ ታሸሻቸዋለች፤ ጥርሷን ማሸሽ አልቻለችም ነበር። አየኋቸው ደስተኛ ነበረች አይኖቿን ባላያቸውም። በድንገት እንባ ከአይኖቿ መፍለቅ ጀመረ። ሀዘኔን አዝናለች ይኸው አነባች አልኩኝ ለራሴ፤ በሰዎች መሀል ብቸኛ ሆነናል የሚረዳን አጣን እንጂ። አንድ የማላውቀው ሰው "ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ" ሲል ሰማሁት። እውነት ነው ሲዳሩ እንጂ ሲያገቡ የሚያለቅሱ ማን ናቸው? እንዴትስ ቢሞኙ? ከጭኖቿ ቀና ብሎ እማ...አቤት ልጄ...በቃ አገባች አትደውልልኝም ድምጿን አልሰማውም አትደውልልኝም እንደ ድሮው አባቴ ብላ አጠራኝም እኔም ሀኑኔ እያልኳት ደስታዋን ማየት አልችልም ናፍቀኸኛል አትለኝም....እማ ወሰዷት እኮ። እናቱ ስታዳምጠው ቆይታ ልጄ ልብህን አደንድነው። እነዛ በወደዱት የተወደዱ የሚወዱትን ያገኙ ምነኛ እድለኞች ናቸው።....ልብህን አደንድነው ልጄ። በረጅሙ ተነፈሰች ዝምታ ሰፈነ....።
አፈቀራት ተከልክሎ
ይኸው ዳራት እልል ብሎ
አንቺን ይንሳኝ ምሎ ነበር
ልታገባ ቆሞ ሊቀር።
✍ ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ
አፈቀራት ተከልክሎ
ይኸው ዳራት እልል ብሎ
አንቺን ይንሳኝ ምሎ ነበር
ልታገባ ቆሞ ሊቀር።
✍ ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ