በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በደብረ ሲሐት የሚኖር አባ ዳንኤል አረፈ።
ይህም አባ ዳንኤል ስሟን እንጣልዮስ አሰኝታ የነበረች ንግሥት በጥሪቃን የገነዛት ነው እርሷም ከሞቷ በኋላ እንጂ ሴት እንደሆነች አልታወቀችም ነበር። በአንዲት ቀንም ወደ እስክንድርያ አገር ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ስሙ ምህርካ የሚባል እብድ አገኘ ብዙ እብዶችም ይከተሉታል ለአገር ሰዎችም በእውነት ያበደ ይመስላቸው ነበር።
አባ ዳንኤልም እጁን ይዞ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ወስዶ ትሩፋቱን ተጋድሎውን ነገረው እንዲነግራቸውም በአማሉት ጊዜ ከዝሙት ጦር በመሸሽ ራሱን እብድ እንዳስመሰለ ነገራቸው ሰምተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው ጥቂት ጊዜም ታመመ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየና በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@sebhwo_leamlakne