SEBIL TUBE 🇵🇸


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


قُل هذِهِ سَبيلى أَدعو إِلَى اللَّهِ عَلى بَصيرَةٍ أَنا وَمَنِ اتَّبَعَني وَسُبحانَ اللَّهِ وَما أَنا مِنَ المُشرِكينَ ﴿١٠٨﴾
"ይህች መንገዴ ናት። ወደ አላህ እጠራለሁ። እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን።ጥራትም ለአላህ ይገባው። እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም"በል።
ቁር 12:108
@muslimman99

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


አንዳንድ ሰወች ህይወታቸው የብርሀን መንገድ ነው። በዙሪያቸው ላሉ ሰወች ያበራሉ!
አንዳንዴ በሀሳብ አንዳንዴ በቆንጆ ንግግር
አንዳንዴ በመፅሀፍ....በሌላም ነገር....😇

@sebil_tube
@sebil_tube


በመጨረሻው ዓለም ፍሬውን ለመሰብሰብ በዱንያ ላይ መልካምነትን ዝራ
አንድ ቀን እንሄዳለን  ስራወቻችን ይቀራሉ ...

@sebil_tube
@sebil_tube


🌟 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ተጠናቀቀ 🌟

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን የማጠቃሊያ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ በቁርዓን ሂፍዝ፣ በቁርዓን ቲላዋ እና በአዛን ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በዳኞች አማካኝነት ይፋ ሆነዋል።

በዚህም
በወንዶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር
1ኛ. ሙሐመድ ፉዓድ … ከሊቢያ
2ኛ. ዩሱፍ አሺር … ከኳታር
3ኛ. አህመድ በሺር …ከአሜሪካ

በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር
1ኛ ሩቅያ ሳላህ … ከየመን
2ኛ ነሲም ጀናዉጃ … አልጄሪያ
3ኛ ቀመራ ወሊዩ መሐመድ … ከኢትዮጵያ

በአዛን ውድድር
1ኛ ሙሀመድሻን አቡበከር … ከኢንዶኖዢያ
2ኛ ኡመር ዱራን … ከቱርክ
3ኛ አደም ጅብሪል … ከኢትዮጵያ

በወንዶች የቁርአን ቲላዋ ውድድር
1ኛ አብዱራዛቅ አል ሸሀዊ …ከግብፅ
2ኛ ከራር ለይስ … ከኢራቅ
3ኛ አንጀድ ካምዳን … ከየመን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ጥር 21 ተጀምሮ ዛሬ በተጠናቀቀው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር ላይ ከ60 በላይ ሀገራት ተሳትፈዋል ተብሏል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማዕ ጽህፈት ቤት፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች መታደማቸውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡»


@sebil_tube
@sebil_tube


ኢትዮጵያዊያኑ ጅብሪል አደም እና ቀመሪያ ወሊድ በቁርኣን ሒፍዝ እና በአዛን ውድድር ሦስተኛ ደረጃ በማግኘት አሸናፊ ሆኑ

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሔደው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር፤ ኢትዮጵያዊያኑ ጅብሪል አደም በአዛን እንዲሁም ቀመሪያ ወሊድ ደግሞ በቁርኣን ሒፍዝ ውድድር ሦስተኛ ደረጃ በማግኘት በውድድሩ ከአሸናፊዎች መካከል ሆነዋል።

ከማለዳ ጀምሮ በተካሔደው ውድድር በወንዶች ቁርኣን ሒፍዝ ውድድር አንደኛ ደረጃ ያገኘው የየመኑ ሙሐመድ አህዋጂ ነው። የኳታሩ ዩሱፍ ሁለተኛ እና አሕመድ በሺር ከአሜሪካ ሦስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል።

በሴቶች ቁርኣን ሒፍዝ አንደኛ የወጣችው የየመኗ ተወዳዳሪ ሩቂያ ሳሊህ ቃሲም ሆናለች። ነሲም ጂናውጂ ከአልጄሪያ ሁለተኛ እና ኢትዮጵያዊቷ ቀመሪያ ወሊድ ሦስተኛ ደረጃ አግኝተዋል።

በሌላኛው ውድድር በአዛን አንደኛ የወጣው ሙሐመድ አቡበከር ከኢንዶኔዥያ ነው። ዑመር ደራን ከቱርክ ሁለተኛ እና ጂብሪል አደም ከኢትዮጵያ ሦስተኛ በመሆን የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።

በቲላዋ ዘርፍ አንደኛ ዓብዱረዛቅ አል ሻዊ ከግብፅ፣ ሁለተተኛ ከራር ለይሰ ከኢራቅ እንዲሁም ሦስተኛ አሕመድ ገምዳን ከየመን ሆነዋል።

Source 👉 (ሚንበር ቲቪ)

@sebil_tube
@sebil_tube


ሁለተኛው ዙር አለምአቀፍ የቁርአን ውድድር ባማረና በሚማርክ መልኩ ተካሂዷል።


@sebil_tube
@sebil_tube


በተዘጋብኝ በር አላማርረውም
የሚበጀኝ ቢሆን ፊትም አይዘጋውም
ሳለቅስ አልገኝም በምሬት ስኳትን
ከፍቶልኝ ስለሚያውቅ ያላንኳኳውትን!
........الله🤍


የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሱጁድ አቀማመጥ ለጀርባ ህመም መድኃኒት መሆኑን ገለጸ።

@sebil_tube
@sebil_tube


አሜሪካዊ-ሩሲያዊው MMA ቦክስ ተደባዳቢ ጄፍ መንሶን እስልምናን ተቀበለ።

አላሁ አክበር comment 👇

@sebil_tube
@sebil_tube


#ሼር
እባካችሁን_ልጄን_አድኑልኝ😭😭😭" አባት

ይህች ውብ የዘጠኝ ወርዓ ህፃን ሷድ_ዩሱፍ ትባላለች! ከተወለደች ጀምሮ በተደጋጋሚ ስትታመም እናትና አባት ጤናጣቢያ ቢወስዷትም ቶንሲል ነው እየተባሉ  መርፌ እየታዘዘላት ደህና ትሆናለች በሚል ተስፋ ቢጠብቁም ልትድንላቸው አልቻለችም!!

አንጀት የምትበላው ትንሿ ሷድ  ከጊዜ ወደ ጊዜ የባሰ እያመማት ጡት አልጠባም ብላ ስታስቸግርና ላብና ለቅሶዋ ሲያስጨንቃቸው ለተሻለ ህክምና ሌላ ሆስፒታል ወስደዋት"እረ ልጃችን በጣም ታመመችብን ምን ሆናብን ይሆን?እዩልን"ብለው በፍርሀት ጠየቁ!

ጨቅላዋ  ሷድ በሚያሳዝን ሁኔታ ከፍተኛ የልብ ህመም እንዳለባት ለወራት በተለያየ ጊዜ የወሰደችው መድሀኒት ህመሟን እንዳባሰባት በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሄዳ ካልታከመችም ለህይወቷ አስጊ እንደሆነ ተነገራቸው!!

ቤት ኪራይ መክፈል ሲከብዳቸው ወደ እናታቸው ቤት የተመለሱት ባልና ሚስት ይህ መርዶ አስደነገጣቸው!ከ3,000,000(3ሚሊዮንብር) በላይ ለሚያስፈልገው የህክምና ወጪ ምንም ማድረግ እንደማይችሉና ልጃቸውን እያዩአት ሊያጧት እንደሆነ ሲያስቡ በጣም ጨነቃቸው!እርዱን ብለው ሰውን መለመንና ሰው ፊት መቅረብ በጣም ከበዳቸው😭

ሀዘንና ስብራታቸውን የተመለከቱ ጓደኞቻቸው ግን
እባካችሁን ሰው አስቸግረን እንሞክርና ሷድን እናድናት ብለው እገዛችሁን ፈልገው መጥተዋል!
#እንድረስላቸው🙏ምንም ማድረግ ካልቻልን #ዱአ እነድርግ ለብዙ ደጋጎች እንዲደርስ
#ሼር እናድርግላቸው🙏

#አካውንት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000304310937 የሱፍ ሀምደላ

  "ለመልካም ስራ ረፍዶ አየውቅም💔🙏
ስቁ
0713172605

9 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.