በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ማጋጠሙ ተገለጸ
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጋር ተያይዞ በአዋሽ አካባቢ 15 ሜትር ርዝመት ያለው ሀዲድ ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች (ማጥበቂያዎች) ቦታቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
የጉዳቱ መንስኤ እየተጣራ እንደሆነና ጉዳቱን በፍጥነት ለማስተካከል የጥገና ባለሞያዎች በስፍራው ተገኝተው ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።