የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድን ሰላማዊ ትግል እንደሚያደርግ አስታወቀ
በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በመቐለ፣ ሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ ከባለሃብቶች ጋር ባካሄደው ስብሰባ፣ እርሳቸው የሚመሩት ቡድን ሰላማዊ ትግል እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
በዚሁ ስብሰባ ላይም፣ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ ዕውቅና ባልተሰጠው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያልተሳተፉትንና በቡድናቸው የተባረሩትን የድርጅቱን አመራሮች ወቅሷል፡፡
“ጉባዔ እንዳናካሂድ ብዙ ሙከራ ተደርጎብናል፡፡ ጉባዔ አለማካሄድ ድርጅቱን ማፍረስ ነው። ይሁንና ወደ ጉባዔ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰን እያለ፣ እነርሱ ግን ‘አንገባም’ ብለው አንገራገሩ። ‘ጉባዔው ከተካሄደ ጦርነት ይከተላል’ ተባለ። የጉባዔው ተሳታፊዎች ጉባዔው ወደሚካሄድበት ቦታ እንዳይመጡ ጥረት ተደርጓል።” ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን ተናግረዋል፡፡
በጉባዔው ላይ እርሳቸው የሚመሩት የህወሓት ቡድን ያለፉትን ስድስት ዓመታት ፖለቲካዊ ስራዎች መገምገሙን የጠቆሙት ዶ/ር ደብረጽዮን፤ “በዚህ ጉባዔ ተበትኖ የሚገኘውን ሕዝባችንን ወደ ቀድሞ ቀዬው እንዲመለስ፣ መሬታችን ተመልሶ በእኛ አስተዳደር ስር እንዲሆን፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና በኢኮኖሚ ግንኙነቶችና በሌሎች ተጀምረው በነበሩ ጉዳዮች ላይ ጥናት በማካሄድ እንቅስቃሴው ዳግም እንዲጀመር ውሳኔዎችን አስተላልፈናል” ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የህወሓት፣ የትግራይ ሃይሎች፣ የምሁራንና ተቃዋሚ ድርጅቶች በመቀናጀት እንደመሰረቱት በማስረዳት፣ “ለአስተዳደሩ የጊዜ ገደብ አስቀምጠንለት ነበር። ይሁንና በክልላችን ሰላም ልናሰፍን አልቻልንም። ሕዝባችን ወደ ቀዬው አልተመለሰም። ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ትግራይን መልሶ ወደ መገንባቱ ሊገቡ አልቻሉም” ሲሉ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡