የአሜሪካ የጦር ጄት በስህተት ተመትታ ወደቀች‼️
በልምምድ ላይ የነበረች የአሜሪካ ኤፍ/ኤ-18 ሆርኔት የጦር ጄት በቀይ ባህር አካባቢ በአሜሪካ ጦር ተመትታ መውደቋ ተነገረ፡፡
በጦር ጄቱ ውስጥ የነበሩ ሁለት አብራሪዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸው የተነገረ ሲሆን÷ አንደኛው አብራሪ ላይ አነስተኛ ጉዳት መከሰቱ ተነግሯል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ የተነገረ ሲሆን÷ አሜሪካ ክስተቱ የተፈጠረው በልምምድ ላይ በነበሩ ጦሯ መካከል መሆኑን አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ ጦር በቀይ ባህር አካባቢ በየመን መቀመጫውን ያደረገውን የሁቲ አማጺ ቡድን ኢላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ክስተቱ አስደንጋጭ ነው ተብሎለታል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ አዘዥ ኤፍ/ኤ-18 ሆርኔት የጦር ጄት መብረር ከጀመር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መውደቁን አስታውቋል፡፡
ምንም እንኳ አሜሪካ አደጋው የተፈጠረው በልምምድ ላይ ባለ ጦሯ መካከል መሆኑን ብትገልጽም ከሁቲ አማጺ ቡድን የተተኮሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የጸረ- መርከብ ክሩዝ ሚሳኤልን ለመመከት የተወነጨፈ አንደሆነ ተነግሯል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ አዘዥ ቀደም ሲል በርካታ የሁቲ አማጺ ቡድንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የጸረ- መርከብ ክሩዝ ሚሳኤሎችን መትቶ መጣሉን ይፋ ማድረጉን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡