ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠረጠሩ አቶ ሰለሞን ጎበዜና እሸቱ የተባሉ ግለሰቦችን ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ የቻሉት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ሀና ማርያም ቀለበት አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ ሁለት የልደት ሰርተፍኬትና አንድ ያገባ ያለገባ ሰርተፍኬት፣ ሀሰተኛ ዲጅታል የቀበሌ መታወቂያ ይዞ ሲንቀሳቀስ እጅ ከፍንጅ ተይዞ የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ
1ኛ.1 ሰርተፍኬቶች መስሪያ ማሽኖች
2ኛ. 3 የማሽን ቀለም ብዛት
3ኛ. 4 ላፕቶፖች
4ኛ. 6 የልደት ካርድ እና ሌሎችም ንብረቶች መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።
በመሆኑም ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ ወንጀል ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን አሳልፎ ለፀጥታ አካላት በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ EFPapp በመጠቀም መረጃ በምስል፣ በቪዲዮ እና በፅሑፍ በመላክ ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መልዕክት በመላክ ጥቆማ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
@Sheger_press