ትራምፕ ያዋረዷቸውን ዘለንስኪ የእንግሊዝ ጠ/ሚ አቅፈው ተቀበሏቸው፤
- የአውሮፓ መንግስትታት ከዩክሬን ጎን መቆማቸውን ገለጹ!
የወሰድከውን ብር አምጣ ብሎ ያበደረውን ሰው ጉሮሮ እንደሚያንቅ የሰፈር ጎረምሳ ለአሜሪካ ክብርና ማንነት ሳይጨነቁ በተደጋጋሚ ከባይደን የወሰድከውን 350 ቢሊዮን ዶላር ውለድ በማለት ሲያስጨንቁ ከቆዩ በኋላ፣ ነጬ ቤተመንግስት ድረስ አክብረዋቸው የመጡትን የዩክሬን መሪ አበሻቅጠውና አቃለው፣ አዋርደውና አሳንሰው፣ እንደ አንድ ተራ እና አለሌ ሰው ቆጥረው ያሻቸውን ተናግረውና ተሳልቀው የተናገሯቸው የዩክሬን መሪ በንዴት ጭሰው ኋይት ሀውስን ረግጠው ቢወጡ ምን ይገርማል! ይሁንና የአውሮፓ መንግሥታት ከዩክሬን ጎን እንደሚቆሙ አስታውቀዋል።
ትራምፕ አዋርደውና አሸማቀው ከኋይት ሀውስ በብስጭት እንዲወጡ ያደረጓቸውን የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ለንደን ሲገቡ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር አቅፈው ተቀብለዋቸዋል ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚርን ዘለንስኪ ያደረጉትና ያለስምምነት የተጠናቀቀውን ውይይት ተከትሎ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ከዩክሬን ጎን መቆማቸውን እያሳዩ ነው።
“ዩክሬን በጀርመን እና በአውሮፓ ሀገራት ላይ መተማመን ትችላለች፤ ከዩክሬን ዜጎች በላይ ሰላም የሚፈልግ የለም” ሲሉ የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልስ ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌዬን እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንት ካጃ ካላስ ለዩክሬን ድጋፋቸውን በመግለፅ "እኛ አውሮፓውያን የመጣውን ፈተና በጋራ ሆነን ማለፍ አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።
የቤልጄም፣ ኔዘርላንድ፣ ስዊድን፣ አየርላንድ፣ ሉቲንያ፣ እንዲሁም የላትቪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ከዩክሬን ጎን እንደሚቆሙ እና ዩክሬን የምትታገለው ለመላው አውሮፓ ጭምር ነው ሲሉ አስታውቀዋል።
ለሶስት አመታት የዘለቀው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የዩክሬን ዋንኛ አጋር የነበረችው አሜሪካ ከዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ የአቋም ለውጥ በማድረጓ የአውሮፓ ሀገራትን ሳያስገርም አልቀረም።
ይባስ ብሎም ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪን “ለሰላም ዝግጁ ስትሆን ተመልሰህ ና” ሲሉ በመናገራቸው የአውሮፓ ሀገራት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተቃውመውታል።
(ጥላሁን አክሊሉ)
@sheger_press