«ከጀርባዬ አንድ ግዙፍ ተራራ!!»
---------------------------
.......✍አባትነት
ግዙፍ ተራራ ነው ስሙ የደመቀ፡
ለልጁ ነፍስ ሰጭ ወኔው የታመቀ፡
በህይወት እስካለ ይደምቃል ልጅነት፡
ጋሻ መከታ ነው ማዕረግ ነው ወንድነት፡
የጥበብ መነሻ ይህ ነው አባትነት፡
ልጄ የሚል ጥሪ አባት ሲያስተጋባ፡
አበጥሮ ሲለይ ምርቱን ከገለባ፡
ልጁን እንዳይደፍረው ዱርየና ሌባ፡
አለኝ ማለት ብቻ ማዕረግ ነው አባ።
«አባት ሳለ አጊጥ ጀንበር ሳለ ሩጥ»
........ ከኔ የበዙ ደስታዎች ጀርባ አንድ የሆዱን በሆዱ አምቆ የያዘ የኔን ሳቅ ብቻ በጉጉት የሚጠብቅ አንድ ግዙፍ ሰው አለ።ከኔ የወጣትነት ውበትና መሽቀርቀር ጀርባ አንድ የተበሳቆለ፣የተንከራተተ፣ያደፈ ልብስ የለበሰ አንድ እምቅ ወኔ ያለው ሰው አለ።
......ከኔ የለሰለሱ እጆች ጀርባ አንድ የሻከሩ መዳፎች ያሉት ሰው አለ።
.......ከኔ በሁለት እግር መቆም እና በራስ መተማመን ጀርባ አንድ ጠንካራ ሰው አለ ።
........ከኔ የመኖር ትርጉም እና ሰው የመሆን ማንነት ጀርባ አንድ ብልህ ሰው አለ ።
.......ከኔ ዛሬና የተስፋ ነገዎቼ ጀርባ አንድ ለኔ ሲል ትናንቱን ያጣ ሰው አለ ።
......ከኔ ሂዎት መቃናት ጀርባ አንድ የጎበጠ ሰው አለ ።
......➢ከኔ ምርጥ አባወራ የመሆን ምኞት እና ለሰው የመኖር ጥበብ ጀርባ አንድ ለቤተሰቡ እንደ ሻማ እየበራ እራሱን በማቃጠል ለቤቱ ብርሀን ሁኖ የቆመ ሰው አለ። ያ አንድ ሁኖ ብዙ የሆነ ጀግና ያ እናትም አባትም በመሆን ፍቅርን ሳይሰስት እየለገሰ ሁሌም እና በምንም ሁኔታ ከጎኔ ሳይለይ የመከታ ክንዱን የሚዘረጋልኝ ድንቅ ሰው ውድ አባቴ ነው ።
«ሌላውን ተውት ካርድ እንደልብ በማይገኝበት በገጠር ህይወት እየገፋ ለኔ በቀጥታ ስልክ የደወለልኝ ማንም ሳይሆን አባቴ ነው ።»
.....ከእማዬ የዘጠኝ ወር ሸክም በኋላ እስከ አሁኗ ጊዜዬ ድረስ አርግዞ አምጦ ወልዶ አዝሎ ልጄ አንቀልባህኮ ዛሬም ከወገቤ አልተፈታም መቼ ይሆን ከሀሳብ የማርፈው እያለ እንባው በአይኑ ሲያቀር አሁን እየፃፍኩ ከሆሄወቹ ጋር ምስሉ የሚታየኝ ይመስለኛል።
«የኔ አባት ለማንም ክፉ እንዳልመኝ፣የማንም ማግኘት እንዳስደስተኝ፣ምቀኝነትና ክፋት ከውስጤ እንድጠፋ እና የተሰማኝን ነገር ሳልደብቅ በነፃነትና በድፍረት እንድናገር ሳትማር ያስተማርከኝ የኔ ንጉስ አንተ ነህ ዲግር ተሸክመህ ለኔ ድግሪ የምትጨነቅ የገጠር ግዙፍ ካንፓሴ አባ.....!!!
ሁሉም አልፎ በልጅህ ኮርተህ እንደኖርክልኝ እንድኖርልህ አላህ ረጂም ሀያት ይስጥህ አባ ኢንሻ አሏህ ሁሉ ይሳካል አንድ ቀን ሰርፕራይዝ አለህ እሽ የኔ አባት እወድሀለሁ።
.....ኑረዲን አል-አረብ
http://t.me/nuredinal_arebi