ሲልዐቱላህ(سلعة الله)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


✔ ቻናላችን በውስጡ የሚሰጣቸው ትምህርቶች ፦
ሰኞ―እሁድ ፦ የነብያት፣የሰሀቦች፣የታቢኢዮች ምክር።
For any comment
@Silatubot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
الله لآ إلٰه إلاّ هو الحيُ القيُوم.....
(አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም።ህያው ራሱን ቻይ ነው!!)

የኔ ጌታ አይተኛም አይደክምም!!
ቀናችሁን በአያተል ኩርሲይ ጀምሩት🎁


@mame_ms1




ሴት ልጅ....

ወንድሜ ለሴት ልጅ የምታደርገው መልካም ነገር ሁሉ ለራስህ ነው!

🖋አንዲት ሴት፣ ልክ እንደ ትንሽ ልጅ፣ ደህንነት ይሻታል። ስለዚህ፣ በዙሪያዋ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰማት አድርግ። በራስ መተማመኗን የሚጨምር ሁኔታ ፍጠርላት።

🖋አንዳንዴ እንደ ቀልድ ትወድ ይሆናል፤ ስለዚህ አብራችሁ ጊዜ ስታሳልፉ አታስጨንቃት። ከእሷ ጋር ተጫወት፣ አዝናና፣ ቀልድህን አካፍላት!

🖋ብስለት ሲጨምርባት ደግሞ፣ የምትሰጣት ትኩረትና እንክብካቤ ያስደስታታል። ችላ እንዳትላት፣ ሁሌም ከጎኗ ሁን!

🖋ጠንካራና ፅኑ ብትመስልም፣ ውስጥ ውስጡን የራሷ ሸክም ይኖራታል። ስለዚህ፣ በችግር ጊዜያትዋ ደጀን ሁንላት እንጂ ሸክም አትሁንባት።

🖋ስትወድህ በሙሉ ልቧ ነው፤ ለፍቅርህ ደግሞ ሁሉን ትሠዋለች። አንተም ከእሷ ያነሰ መስዋዕትነት እንዳትከፍል!

🖋ሴት ልጅ ብዙ አትፈልግም – ፍቅር፣ ከልብ የመነጨ እንክብካቤ፣ እውነተኛ ቃል፣ መተማመን፣ እና በምንም ነገር እንዳትፈራ ማድረግ በቂ ነው።

🖋እነዚህን ነገሮች ካሟላህላት፣ አንተን በማየት አለሟን ታያለች፤ አለም ሁሉ በአንተ እጅ እንደሆነ ታስባለች። አንተም ያንን ዓለም እንዳታበላሽባት!

ስለዚህ ወንድሜ ለሴት ልጅ
•  ሁሌም ከጎኗ ሁን፤ ለደህንነቷም ተጨነቅ።
•  አብራችሁ ስትሆኑ ተጫወቱ፤ አታካብድ።
•  በችግርዋ ጊዜ ደጀን ሁን፤ አታማርር።
•  ፍቅርህን ግለጽላት፤ እውነተኛ ሁን።
•  እሷን እንደምትተማመንባት አሳይ፤ ክብር ስጣት።
•  የእርሷ አለም አንተ እንደሆንክ አስታውስ!

በወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሀሰይን


من مغرب يوم الخميس إلى مغرب يوم الجمعه كل ثانيه فيها خزائن من الحسنات فلنُكثر من الصلاة على النبيﷺ ، ونضاعف أجورنا بأحب الأعمال الى الله


ከብዙዎች በላይ ትልቅ ፀጋ እንደተሠጣችሁ አውቃችሁ ደግ ሠርታችሁ የምትውሉበት ቀን ይሁን ።ተመርቃችሁ ዋሉ። መንቁል




በጣም አስደንጋጩ ነገር ሰዎች በእኛ ላይ መልካምነትን እያዩ በሰማይ ላይ ግን ምንም ቦታ የሌለን ባዶ ከሆንን ነው !* 🍁

Husseynfurii


«ከጀርባዬ አንድ ግዙፍ ተራራ!!»
---------------------------

.......✍አባትነት

ግዙፍ ተራራ ነው ስሙ የደመቀ፡
ለልጁ ነፍስ ሰጭ ወኔው የታመቀ፡
በህይወት እስካለ ይደምቃል ልጅነት፡
ጋሻ መከታ ነው ማዕረግ ነው ወንድነት፡
የጥበብ መነሻ ይህ ነው አባትነት፡
ልጄ የሚል ጥሪ አባት ሲያስተጋባ፡
አበጥሮ ሲለይ ምርቱን ከገለባ፡
ልጁን እንዳይደፍረው ዱርየና ሌባ፡
አለኝ ማለት ብቻ ማዕረግ ነው አባ።

«አባት ሳለ አጊጥ ጀንበር ሳለ ሩጥ»

........ ከኔ የበዙ ደስታዎች ጀርባ አንድ የሆዱን በሆዱ አምቆ የያዘ የኔን ሳቅ ብቻ በጉጉት የሚጠብቅ አንድ ግዙፍ ሰው አለ።ከኔ የወጣትነት ውበትና መሽቀርቀር ጀርባ አንድ የተበሳቆለ፣የተንከራተተ፣ያደፈ ልብስ የለበሰ አንድ እምቅ ወኔ ያለው ሰው አለ።
......ከኔ የለሰለሱ እጆች ጀርባ አንድ የሻከሩ መዳፎች ያሉት ሰው አለ።
.......ከኔ በሁለት እግር መቆም እና በራስ መተማመን ጀርባ አንድ ጠንካራ ሰው አለ ።
........ከኔ የመኖር ትርጉም እና ሰው የመሆን ማንነት ጀርባ አንድ ብልህ ሰው አለ ።
.......ከኔ ዛሬና የተስፋ ነገዎቼ ጀርባ አንድ ለኔ ሲል ትናንቱን ያጣ ሰው አለ ።
......ከኔ ሂዎት መቃናት ጀርባ አንድ የጎበጠ ሰው አለ ።

......➢ከኔ ምርጥ አባወራ የመሆን ምኞት እና ለሰው የመኖር ጥበብ ጀርባ አንድ ለቤተሰቡ እንደ ሻማ እየበራ እራሱን በማቃጠል ለቤቱ ብርሀን ሁኖ የቆመ ሰው አለ። ያ አንድ ሁኖ ብዙ የሆነ ጀግና ያ እናትም አባትም በመሆን ፍቅርን ሳይሰስት እየለገሰ ሁሌም እና በምንም ሁኔታ ከጎኔ ሳይለይ የመከታ ክንዱን የሚዘረጋልኝ ድንቅ ሰው ውድ አባቴ ነው ።
«ሌላውን ተውት ካርድ እንደልብ በማይገኝበት በገጠር ህይወት እየገፋ ለኔ በቀጥታ ስልክ የደወለልኝ ማንም ሳይሆን አባቴ ነው ።»

.....ከእማዬ የዘጠኝ ወር ሸክም በኋላ እስከ አሁኗ ጊዜዬ ድረስ አርግዞ አምጦ ወልዶ አዝሎ ልጄ አንቀልባህኮ ዛሬም ከወገቤ አልተፈታም መቼ ይሆን ከሀሳብ የማርፈው እያለ እንባው በአይኑ ሲያቀር አሁን እየፃፍኩ ከሆሄወቹ ጋር ምስሉ የሚታየኝ ይመስለኛል።

«የኔ አባት ለማንም ክፉ እንዳልመኝ፣የማንም ማግኘት እንዳስደስተኝ፣ምቀኝነትና ክፋት ከውስጤ እንድጠፋ እና የተሰማኝን ነገር ሳልደብቅ በነፃነትና በድፍረት እንድናገር ሳትማር ያስተማርከኝ የኔ ንጉስ አንተ ነህ ዲግር ተሸክመህ ለኔ ድግሪ የምትጨነቅ የገጠር ግዙፍ ካንፓሴ አባ.....!!!

ሁሉም አልፎ በልጅህ ኮርተህ እንደኖርክልኝ እንድኖርልህ አላህ ረጂም ሀያት ይስጥህ አባ ኢንሻ አሏህ ሁሉ ይሳካል አንድ ቀን ሰርፕራይዝ አለህ እሽ የኔ አባት እወድሀለሁ።

.....ኑረዲን አል-አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi


.
ዝምታ ድምፅ አለው::
ነገር ግን ሊረዳ የሚችል ነብስ ይፈልጋል::


ዱአ ስታረጉ ያዘል ጀላሊ ወልኢክራም የሚለውን አብዙ






Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


🌹ህፃኗኮ ናት...ሱጁድ ወርዳ ሀምዛ ፈትሃ ኣ..ሀምዛ ከስራ ኢ ....አ፣ኢ፣ ብላ እርፍ🍓ሙሉ ሶላቱን በእንዲህ መልኩ በኑራኒያ ሲታጀብ አሏህዬ.. አስቡት አጠጋቧ እየሰገዳችሁ ቢሆን ......


🛑👉ለራስሽ ቃል ግቢ

ነገሮች በፈለግሺዉ መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ ሰዎች ጀርባቸዉን ሊያዞሩብሽ ይችላሉ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉሽ ነገሮች ሁሉ ልታጪ ትችያለሽ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ዉስጥ አልፈን እናዉቃለን ወደፊትም እናልፋ ይሆናል። ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተስፋ ቆርጠሽ ጥረትሽን እንዳታቆሚ ለራስሽ ቃል መግባት ነዉ !!






"وَمَنْ يَتقِ الله" (هذا شرط)
"አላህን የሚፈራ ሰው" (ይሄ ሸርጥ ነው)

‏"يَجْعَلْ له مَخْرَجًا" (هذا وعد)
"ከጭንቀት መውጫ መንገድ ያበጅለታል"(ይሄ ቃል ነው)

‏"وَيرزقْه مِن حَيثُ لايَحتسِبْ" (هذه مكافأة)
"ሲሳይም ካላሰበው ቦታ ይለግሰዋል" (ይሄ ሽልማት ነው)

‏اللهمَّ اجعلنا من المُتقين♥️.
አላህ ሆይ! አንተን ከሚፈሩህ ሰዎች መሃል አድርገን❣.

=======≥=======
join
👇👇👇👇
t.me/silatullah_4u


አዳማዎች ወንጂዎች ከፊፍ የጥቁር ልብስ ሳሙና ገብቷል
በ 1ሊትረ
በ ግማሽ ሊትረ
የተወሰነ ብቻ ስለገባ ሳያልቅባችሁ ቶሎ ውሰዱ
ይዘዙን
📞0962536736
@hani6736


IM Etcare dan repost
ውድ ደንበኞቻችን በግማሽ ብቻ የነበረው ከፊፍ የጥቁር ልብስ ሳሙና
በ 1ሊትር እና በግማሽ ሊትር መቷል መውሰድ ይቻላል
አዳማዎች አላህ ካለ በቅርብ ስለምንልንክ ምትፈልጉ አሳውቁን
አዲሥ አበባዎች አናግሩን

👇👇
አድራሻ ወደ ካራ አጃምባ መውጫ ረጲ አንሳር መስጂድ ጋር
ግሩፓችንን👇👇👇
👉👉👉 @kitab000👌👌




@eka1824

📞0941331589/0912930524

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.