በየቦታው ኢማሞች ይባረራሉ, ይሳደዳሉ, ይታሰራሉ:: መከራው ያላንኳኳው መንደር የለም:: ይህ ወቅት በሀገረ ሐበሻ ኢማሞች በጥጋበኛ ጎረምሶች የተሳደዱበት ዘመን ተብሎ መመዝገቡ አይቀርም:: ያሲኖ እንኳ ባቅሟ ኢማም አባርራ ፊጥ ብላለች:: የገለበጣቸው ኢማም ሸይኽ ሙሐመድ ኑር ሁለቴ ታስረው ነበር:: ኢማም አሳስሮና ገልብጦ ሚንበር ላይ ስለምን ይሆን የሚያስተምረን? ምን ሁኑ ሊለን ነው? ያ ኢላሂ ይህንን ወቅት አሳልፈፎ ያሳየን::