የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡
አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official) dan repost
አንድ ሰው ዙሀይር ኢብኑ አቢ ኑዐይም ጋር መጥቶ፦
“አንቱ አቡ አብዲራህማን ሆይ! እስኪ ምከሩኝ!" አላቸው።
እሳቸውም፦ “በተዘናጋህበት ሰዓት አላህ እንዳይወስድህ ተጠንቀቅ።” በማለት መከሩት።
📗ሲፈቱ አስሰፍዋ (4/9)


اللهم أيقِظْنا من رقدات الغفلة، ووفقنا للتزود من التقوى قبل النقلة، وارزقنا اغتنام الأوقات في هذي المهلة، واغفر لنا ولوالدينا ولجميع المسلمين برحمتك يا أرحم الراحمين ..🤲

https://t.me/sultan_54


የፈጅር ሰላት  አላህ የወደደው እና እሱን መገናኘትን የሚወድ ቀልብ  ካልሆነ በቀር አይገጣጠምም። ♥
ከተገጣጠሙት አደርገን!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
"በጭንቅ እና በመከራ ጊዜ ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚፈልግ በድሎት ጊዜ ዱዓ ማድረግ ያብዛ።”
ሰሒሁ አትቲርሚዚ (2382)




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከመሬት መናወጥ የምንማራቸው ቁም ነገሮች




ፈትዋ፦ ለሞተ ሰው ሰደቃ ማውጣት ይቻላልን?
"አንተ በህይወት ያለህ ሰው ሆይ! መልካም ሥራ  ላንተ ያስፈልግሃልና ሥራውን ለራስህ ሥራ፣ ለሞቱት አባቶችህና እናቶችህ ወንድም እህቶችህ እንዲሁም ለሌሎች ሙስሊሞች ዱዓ አድርግላቸው።
በመልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ሱና የተገለፀው ይህ ነው።
ነገር ግን ይህ ሆኖ ሳለ አንድ ሰው ለሞተ ሰው ሰደቃ ቢያደርግ ወይም ስለነሱ ቢጾም ወይም ዱዓ ቢያደርግ ምንዳውን ለሞተው ሰው እንዲሆን አስቦ ማንኛውንም ዒባዳ ቢያደርገው ምንም ችግር የለበትም።"
📚ፈትዋ ኑሩን ዓለ ደርብ
(ሸይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ)


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الزلزال دررس وعبر

❗️
  ከመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት የምንማራቸው 3 ቁም ነገሮች

🎙 በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ረጀብ 09/1446 አ/ሂ

©️ https://t.me/sultan_54

®️ http://t.me/kalityhamzamesjid




ስለ ሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ኹጥባ

የሰማያትና የምድር ንግሥና በእጁ የሆነ አምላካችን አላህ የተመሰገነ ይሁን፣ የሱ ባሪያ እና መልእክተኛ በሆኑት ሙሐመድ  በእሳቸውና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም በባልደረቦቻቸውም ላይ በሙሉ ይስፈን፡-

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ!
እናንተንም ራሴንም ሁሉን የሚችለውን አምላክ እንድትፈሩ እመክራለሁ። እሱን መፍራት(ተቅዋ) በችግር እና በመከራ ጊዜ ጠንካራ ምሽግ እና አስተማማኝ መሸሸጊያ ነው።

የሎስ አንጀለስ ከተማን የተነሳው ሰደድ እሳት፣ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች አውድሟል።
የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።
በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

በዚህም የተሳ ተአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ነወሪዎች ቤት አልባ እና ሀዘን ላይ የጣለውን ሁላችንም አይተናል ሰምተናል። እነዚህ ክስተቶች በአጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ወደ እርሱ ወደ አላህ እንድንመለስና ከእንቅልፋችን እንድንነቃ የሚያስገነዝበን የአላህ ምልክቶች ናቸው።

ምእመናን ሆይ!
አላህ جل جلاله እንዲህ ብሏል፡- “ተአምራቶችንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም።” (አል ኢስራእ 59)።

እነዚህ የተፈጥሮ አደጋዎች ዓለም ጊዜያዊ እንደሆነች እና ኃይል የአላህ ብቻ እንደሆነ ከአላህ ለአገልጋዮቹ ማሳሰቢያ ናቸው። የኛ የቴክኒክ ሃይል እና ሳይንሳዊ እድገታችን ሊያስደንቀን ይችላል ነገርግን ከአላህ ሰራዊቶች ፊት ግን ምንም መቋቋም አይችሉም።

ሙስሊሞች ሆይ!
ተውበት እናድርግ ከሀጡአት ብንመለስ
ፍርሃትን ደኅንነትን፣  ጭንቀም  በብልጽግናን ሊተካ እንደሚችል እናስታውስ። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እንዲህ ይላል።
"የሰዎች እጆች በሠሩት ሥራ ምክንያት በየብስና በባሕር ላይ ፈሳድ ጥፋት ታየ( ተንሰራፋ)። ይመለሱ ዘንድ ይሠሩት ከነበሩት ከፊሉን ይቀምሱ ዘንድ" (አል-ሩም 41)።

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለባሮቿ መሐሪ ነው፣ በተውበታችን  ይደሰታል፣ ​​በንስሐም ወደ እርሱ የተመለሱትን ይቅር ይላልና እነዚህን ክስተቶች ለተጠያቂነት እና ወደ አላህ የመመለሻ ዕድል እናድርጋቸው።

ሙስሊሞች ሆይ!
ይቅርታን እንለምን እና አላህ መከራውን ከእኛ እንዲያርቅልን ደጋግመን እንጸልይ፣ ለተቸገሩትም ሆነ ለተጎዱት የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ፣ ይህ ወደ አላህ የመቃረብ ትልቁ በሮች አንዱ ነውና። ለአላህ በመታዘዝ ጸንተን ለመኖር እንትጋ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም መዳን ነው።

አምላኬ ሆይ መከራውን ከኛ ላይ አስወግድ አገራችንን እና የሙስሊም ሀገራትን ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። አምላኬ ሆይ አንቀጾችህን ከሚያስተውሉ እና ወደ አንተ ከሚመለሱት ጸጸተኞች መድበን።

ይህን እላለሁ አላህንም ለእኔም ለእናንተም ምሕረትን እለምነዋለሁ። ከእርሱም ምሕረትን ለምኑት እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና።


قال تعالى : { حتى إذا أخذت الأرض زخرفها وازينت وظن أهلها أنهم قادرون عليها أتاها أمرنا ليلا أو نهارا فجعلناها حصيدا كأن لم تغن بالأمس ۚ كذلك نفصل الآيات لقوم يتفكرون }


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish








የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة

❗️
  የረጀብ ወር ታላቅነትና በውስጧ የሚሰሩ ቢድዓዎች

🎙 በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ረጀብ 03/1446 አ/ሂ

©️ https://t.me/sultan_54

®️ http://t.me/kalityhamzamesjid


📌" የእግር ኳስ ጨዋታ ቅድም ሁኔታዎች(ሹሩጦች) ⚽
በሸይኽ ናሲሩ አድ-ዲን አል_አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና"✅


1_የጨዋታው አላማ አካልን ማጠናከር ወይም ነፍስን ማዝናናት መሆን አለበት።
2_ሀፍረት ገላ መጋለጥ የለበትም። ለምሳሌ ወንዶች ጉልበታቸውና ከዚያ ከፍ ያለው አካል መታየት የለበትም።
3_ጨዋታው መስጂድ ውስጥ ሶላትን በጀመዓ መስገድን የመሳሰሉ ሸሪዓዊ ተግባራት ላይ መዘንጋትን የሚያስከትል መሆን የለበትም።
4_ጨዋታው ዛሬ  ላይ  ስፖርታዊ ጨዋነት ተብሎ የሚጠራው  አይነት መሆን አለበት፤ ስለዚህም ኳስ መጫወት ቂም ፣ጥላቻ ፣መደባደብ ፣መመታት እና የመሳሰሉትን ሊያመጣ አይገባም።

📚 [ፈታዋ ጂድ_ዳህ ካሴት (ቁጥር 13)]
-


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ዐብዱል ቃዲር አል_ጀይላኒ ማናቸው?

💎“በኢማሙ አሕመድ ረዲየላሁ ዐንሁ የእምነት ጎዳና ላይ ካልሆነ በቀር የአላህ ወልይ መሆን አይቻልም።”
✍ዐብዱል ቃዲር አልጀይላኒ

📚ذيل طبقات الحنابلة لإبن رجب (2-202)

https://t.me/sultan_54


«ፈጅር ሰላትን በመተኛት ያሳለፈ፣እለቱን አውድሟል፤ ቀኑን ያለ ቢላ አርዷል።»
(ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር)

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.