ይህ አንቀፅ በየትኛውም ሁኔታ በፍጡራንና በፈጣሪ መካከል መመሳሰል እንደሌለና አላህ ሰሚና ተመልካች መሆኑን ያሳያል፡፡ መስሚያና መመልከቻ የብዙ ፍጡራን መገለጫዎች ቢሆኑም ነገር ግን የአላህ መስሚያና መመልከቻ ከፍጡራኑ ጋር አይመሳሰልም፡፡ በመስሚያና በመመልከቻ አምሳያ እንዳሌለው ሁሉ በሌሎችም ባህሪያቱ አምሳያ የለውም፡፡ ይህ አንቀጽ ሙስሊሞች ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ከመረዳት አንጻር ሊኖራቸው ለሚገባው ትክክለኛ አካሄድ በመርህ መልክ ይቀርጻል። አንቀጹ የጉድለት ባህሪዎችን ጥቅል በሆነ መልኩ ዉድቅ ሲያደርግ ምሉዕ ባህሪዎችን ግን በዝርዝር ያጸድቃል።
አቅጣጫዎች ህዋሳዊ ማነጻጸሪያ reference point በመጠቀም ብቻ የሚታወቁ ናቸው። ማንኛውም ሰው የቂብላን አቅጣጫ ለማወቅ ጸሀይን ማነጻጸሪያ እንደሚያደርገው ማለት ነው። ሰዎች በአዕምሮአቸው የሚቀርጿቸው ማነጻጸሪያዎች ሁሉ በፍጥረተ አለሙ የተገደቡ በመሆናቸው ስለአላህ ለመናገር እነዚህን ፍጡራዊ ማነጻጸሪያዎችን መጠቀም አይገባም።
፨ አህሉሱና ፍልስፍዎችን በቁርአን እና በሱና ላይ አይሾሙም። አላህ ለራሱ ያጸደቃቸውን ባህሪዎች ያጸድቃሉ፤ ለአላህ ተገቢዉን ክብር ስለሚሰጡ ስለባህሪዎቹ የተነገሩ መረጃዎችን የፍጡራንን ባህሪ በሚረዱበት ሁኔታ አይረዱም። ሁልጊዜ መነሻቸው አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጽዳት ስለሆነም እነዚህና መሰል የአስተሳሰብ ግድፈቶች አይገጥሟቸውም ።
አዎን! አላህን በጉድለትም ይሁን ከፍጡራን ጋር በመመሳሰል ከመግለፅ የፀዱ ናቸው።
በአንፃሩ አህባሾችና አርአያዎቻቸው ጀህሚዮች ግን ሁሌም መነሻቸው ስለ አላህ የተነገሩ መረጃዎችን ልክ ፍጡራን ላይ በሚያውቋቸው ባህሪያት መልኩ መረዳት ስለሆነ አላህን ከፍጡራን መለየት ያልቻሉ "ሙመሲላህ" አመሳሳዮች እነሱው ናቸው።
የሰማያትና የምድር ፈጣሪ አምላክ ሰለሆነው አላህ ሲነገር እንዴት ፍጡራዊ የሆኑ ባህሪዎች ይታወሳሉ??
አላህ ከጥመት ይጠብቀን!
አቡጁነይድ
ዙልቂእዳ 17/1436 ዓ.ሂ
www.fb.com/asmaewesifat