ፋኖነት የጀግንነት መንፈስን የሚያነሳሳ፣ የነፃነት ጥሪን የሚያስተጋባ ልዩ እሴት ነው! ፋኖ ለእኛ ለአማራዎች የኩራታችን ምንጭ ነው። አሁን ላይ ፋኖ ከ80 በላይ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች ያሉት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በጽናትና በጀግንነት የታነጸ ኃይል ነው። ይህ ቁጥር በራሱ የሚናገር ነው፤ ይሄ ሁሉ ክፍለ ጦር የተደራጀው በአመት ከምናምን ብቻ መሆኑ ደግሞ እጅግ አስደናቂ ያደርገዋል።
ይህ ሁሉ ኃይል በአንድ ዓመት ከምናምን ውስጥ መገንባቱ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊም ነው። ያለምንም ማጋነን እንዲህ አይነት ፈጣን እድገት፣ እንዲህ አይነት የህዝብ ድጋፍ በአማራ ፋኖ እንጂ በማንም "ታጋይ ነን" ባዮች ዘንድ አልታየም። ይህም ፋኖ ከህዝብ ለህዝብ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።
ይሁን እንጂ አንድ ነገር ልንዘነጋ አይገባም፤ ይህ ሁሉ ኃይል ገና በአንድ ላይ አልተባበረም። በአንድ ድርጅት በአንድ መዋቅር አልተሰባሰበም። አዎ፣ ፋኖ ሀገር መምራት የሚችሉ ብዙ መሪዎች፣ የውትድርና ጥበብ ባለቤት የሆኑ ብዙ ጀግኖች አሉት፣ ብዙ ክፍለ ጦሮች አሉት፤ ነገር ግን በአንድ ዓላማ አንድ ላይ መቆም አልተቻለም። አንድነታችን ሲጎድል ጥንካሬያችንም ይዳከማልና ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድ መሆን ያስፈልገናል። እንደ አንድ አይደለም አንድ እንጂ!
ታጋይ አምሓራ

ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!