ከፓስፖርት ቅጣት የተሰበሰበው ወደ 18 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በግለሰብ አካዉንት ገቢ ሲደረግ እንደነበር በኦዲት ተረጋገጠ
ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት ቅጣት ክፍያን የመሰብሰብ ፍቃድ ሳይሰጠዉ የራሱን የመመሪያ ተመን በማዉጣት ሲሰራ እንደነበር ተገልጿል ።
ስልጣን ሳይሰጠዉ ከፓስፖርት የሚገኝ የቅጣት ገንዘብን እየሰበሰበ ይገኛል የተባለው አገልግሎቱ የገንዘብ ሚኒስትርን ሳያስፈቅድ የራሱን አካዉንት በመክፈት 17 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ አድርጓል ተብሏል።
በራሱ የተመን መመሪያ ቅጣት ሲጥል የነበረዉ ተቋሙ ከ 1 ሺህ እስከ 1500 ብር እያስከፍል እንደነበር ካፒታል ከኦዲት ሪፖርቱ ተመልክቷል።
ይህ ገንዘብ ገቢ ሲደረግ የነበረዉ በግለሰቦች አካዉንት ተከፍቶ ነበር ያለዉ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የተከፈተው " የባንክ አካዉንት ወደ ሰራተኞች መረዳጃ እድር ተቀይሯል ብሏል" ።
በዚህ ባልተፈቀደ አካዉንት ገቢ ተደርጓል ከተባለው ገንዘብ ዉስጥ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆነው ለትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ለበዓል ወጪ መደረጉን እና 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ደግሞ በአካዉንቱ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ በቅጣት የተገኘው ገቢ ወደ መንግስት መተላለፍ የነበረበት ያለ ሲሆን ይህ ባለመሆኑ ህጉ መጣሱና ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል ብሏል።
ይህ የተገለፀዉ ቋሚ ኮሚቴው የ2015 እና 2016 በጀት ዓመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የክዋኔ የኦዲት ሪፖርት ላይ ዉይይት ባደረገበት ወቀት ነዉ።
የኦዲት ግኝቱን በሚመለከት አሁን በአመራር ላይ የሚገኙ ኃላፊዎች አዲስ መሆናቸዉን ከመግለፅ ዉጪ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ምላሽ ያልሰጠው ተቋሙ ያሉበትን የአሰራር ክፍተቶች ማሻሻል ማድረግ እንደሚገባው ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል ።
©️Capital
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete