የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት በሦስት ዓይነት አሠራሮች እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡
በመንግሥት ምደባ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የወጪ መጋራት ግዴታ እንደሚመለከታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አብዱ ናስር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዓይነት ተማሪዎች እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው፤ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን የሚችሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እና የወጪ መጋራት የሚመለከታቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የተማሪዎች ዝቅተኛው የትምህርት ቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ተማሪ የምግብ ወጪ መጋራት ሲሰላ 120,000 ብር እንደሚሆንና የሰባት ዓመት ቆይታ ያለው የሕክምና ትምህርት ደግሞ 210,000 ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት ተመን በየትምህርት ዘርፍ የዋጋ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ይህም በተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ቆይታ ስሌት መሠረት እንደሚሆን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 5,000 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን፤ 2,500 በራሳቸው ከፍለው የሚማሩና ወጪ መጋራቱ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ የተቀሩት 2,500 ተማሪዎች ደግሞ መደበኛው የመንግሥት ወጪ መጋራት የማይከመለታቸው ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 ብር እንዲሆን ተወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መላኩም ይታወቃል፡፡ #ሪፖርተር
@temhert_bebete